Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2020
    M T W T F S S
     123
    45678910
    11121314151617
    18192021222324
    25262728293031
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for May 20th, 2020

ሰቆቃወ ደብረ ሊባኖስ | ልክ እንደ ግራኝ አህመድ ፋሺስት ጣልያንም ፈጸመችው ፥ ዳግማዊ ግራኝስ?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 20, 2020

፹፫ /83 ዓመታት በፊት በዝነኛው የደብረ ሊባኖስ ገዳም ቀደም ሲል ግራኝ አህመድ ፈጽሞት የነበረው ዓይነት ጭፍጨፋ ሮማውያኑ ጣልያኖችም አውሬነት በተሞላበት አረመኔነት በመንፈሳውያን ኢትዮጵያውያን ላይ አካሄዱ።

ይህ በሃገራችንና በመላው ዓለም በአግባቡ የማይታወቅና ብዙ ጊዜ የማይነገርለት ክስተት ነው። ይኼ የሮማውያኑ የጣልያን ፋሽዝም ከፈጸማቸው ጆሮ ጭው የሚያደርጉ የጭካኔ ሥራዎች አንዱ ነው።

ፋሺስቶች የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ፍልሰተ ዐጽም የተከናወነበትን በዓል ለማክበር የተሰበሰቡትን ምዕመናንንና መነኮሳትን ነበር በጭካኔ የጨፈጨፉት፡፡ በጫጋል፣ በውሻ ገደል፣ በሥጋ ወደሙ ሸለቆና በደብረ ብርሃን አጠገብ በእንግጫ በተከናወነው ጭፍጨፋ ገና ነፍስ ያላወቁ ሕጻናት የቆሎ ተማሪዎችን ጨምሮ ከ1801 እስከ 2201 የሚደርሱ ምእመናንና መነኮሳት በግፍ ተረሽነዋል፡፡ አውሬ እንዲበላቸውም የትም ተወርውረው ነበር፡፡

በዚህም አላበቃም፡፡ በገዳሙ የነበሩ መጻሕፍት፣ የከበሩ ዕቃዎች፣ ንዋያተ ቅድሳት፣ ገንዘብና ሌሎች ንረቶች ተዘረፉ፡፡ ገዳሙም ነጻነት እስኪመለስ ድረስ በመከራ ውስጥ ኖረ፡፡

አስገራሚው ነገር ከ500 ዓመታት በፊት ግራኝ አሕመድ ገዳሙን ሲያቃጥል የሞቱት መነኮሳት ቁጥር 450 ነበር፡፡ ፋሽስት ኢጣልያ የጨፈጨፈቺው ከእርሱ አምስት ጊዜ እጥፍ የሚበልጥ መሆኑን ስናስበው የጭካኔውን መጠን ያመለክተናል፡፡

ሕጻናት፣ ወጣቶች፣ ጎልማሶችና አረጋውያን በሃይማኖታቸውና በኢትዮጵያዊነታቸው ምክንያት ብቻ የደረሰባቸውን ግፍ ስናስበው ልባችን በኀዘን ፍላጻ ይወጋል፡፡ በተለይ ዛሬም ኦሮሞ ነንየሚሉት የፋሺስት ኢጣልያ የግብር ልጆችም በዚህ ታሪካዊ ገዳም ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ለመፈጸም ያዙን ልቀቁን እያሉ ሲፎክሩ ስንሰማ ሁሉም ዲያብሎስ ከተከለው ዛፍ የተገኙ ኢትዮጵያንና እግዚአብሔር አምላኳን የሚጠሉ ሥጋዊ ፍጥረታት መሆናቸውን እንረዳለን።

__________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

ግብጻውያን ክርስቲያኖች | ሙስሊሙ አብይ አህመድ ኢትዮጵያን እስላማዊት እያደረጋት ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 20, 2020

  • 👉 በሁዳዴ ቤተ ክርስቲያን ያቃጥላሉ፣ ክርስቲያኖችን ይገድላሉ፥
  • 👉 ለረመዳን መስጊድ ይሠራሉ ሙስሊሞችን ይቀልባሉ!

ሞኝ ሰው እራሱ ከሠራው ልምድ ብቻ ለመማር ይሻል፤ ብልህ ሰው ግን ከሌሎች ልምድ ይማራል!

ህገወጦቹ ግራኝ አህመድ አሊና አጋሩ ታከለ ኡማ በቅዱስ ሚካኤል ዕለት አዲስ አበባ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ጎን የሰይጣን አምልኮ የሚውል አንጋፋ መስጊድ ለመገንባት ወስነዋል። ሰይጣን ከቤተ ክርስቲያን አይርቅምእንዲሉ።

እነዚህ ሁለት ውርንጭላዎች ሃይማኖታችን ጴንጤ ነውይላሉ ታዲያ አሁን ማን ፈቅዶላቸው ነዉ ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጎን መስጊድ የሚያሰሩት? እነዚህ የዲያብሎስ የግብር ልጆች ለተዋሕዶ ምን ያህል ሥር የሰደደ ትልቅ ጥላቻ እና ንቀት እንዳላቸው ነው የሚያሳየው።

እግዚአብሔር የሰጠውን አንዷንና ብቸኛዋን ሃገሩን ለጠላት አስላፎ በሰጠው በዚህ ከንቱ ትውልድ ይህን ያህል ያፈርኩበት ወቅት አልነበረም።

ለመሆኑ፤ “በዘመነ ኮሮና ከአራት በላይ ሰው መሰብሰብ የለበትምሲል አልነበረምን? የእነ ታከለ ጭንብል የታለ? አሁን ይህ የረመዳን ጋኔን ወር ልክ ሲገባደድ ቤተ ክርስቲያንን እንደገና ለመዝጋት የኮሮና ታማሚውን ቁጥር ከፍ ያደርጉታል።

አብዮት አህመድን እና ታከለ ዑማን ቅዱስ ሚካኤል በእሳት ይጠራርጋቸው።

ግብጻውያን ክርስቲያኖች ይህን ዓይነት አስከፊ ጂሃድ አይተውታል። በትውልድ አገራቸው ለዘመናት እንደ ሁለተኛ ዜጋ የሚቆጠሩትና የእስልምናን ሜንጫ ላለፉት 1400 ዓመታት በመመከት ላይ ያሉት ኮፕት ወገኖቻችን የእስልምናን ሰይጣናዊ አካሄድ በደንብ ነው የሚያውቁት።
ኮፕት ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ላይ እየደረሰ ስላለው ጥቃት ከመገረም ጋር ሃዘኖቻቸውን እንደሚከተለው ይገልጻሉ፦
+ 👉 “
የክርስትና ሃገርና መቀመጫ በሆነችው ኢትዮጵያ ውስጥ እንኳን ክርስቲያኖች እየተበደሉ ነው፤ በርግጥም በፍጻሜ ዘመን ላይ ነን፡፡
+👉 
መላዋ የኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ መንግስት ናት እናም ሙስሊሙ መሪ አቢይ አህመድ ይህን አይወድም
+👉 
ሶማሊያውያኑ ስደተኞች የአመፅ መቅሰፍትን ይዘው ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል፤ በአራት ዓመት ውስጥ ማንም ሳይመክታቸው ወረራውን በደንብ ጀምረዋል፤ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ነበር ተስፋችን፤ ኦርቶዶክስ ሁልጊዜ ደካማ ናት
+ 👉
እስልምና አደገኛ ነቀርሳ/ ካንሰር ነው

__________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ድንቁ አባታችን ቅዱስ ያሬድ እዚህ ነው የተሠወረው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 20, 2020

በሰሜን ኢትዮጵያ በጠለምት ደብረ ሐዊ የሚገኘውና ቅዱስ ያሬድ የተሰወረበት ድንቅ ገዳም ይህ ነው።

  • ቅዱስ ያሬድ የዜማ ሊቅ ብቻ አይደለም። አቡነ ያሬድ የቅድስት ቤተክርስቲያን ጌጧና መሠረቷ ሕይወቷና እስትንፋሷ ነው።
  • አቡነ ያሬድ የመጽሐፍ መምህር(ብሉያትንና ሐዲሳትን የሊቃውንትንም መጻሕፍት አስማምቶ የተረጐመ) ነው።
  • አቡነ ያሬድ ባለቅኔ (የቅኔ ጀማሪ) ነው።
  • አቡነ ያሬድ ልዑለ ስብከት ነው።
  • አቡነ ያሬድ ሰማዕት ነው።
  • አቡነ ያሬድ ባሕታዊ ነው።
  • አቡነ ያሬድ መናኝ ነው።
  • አቡነ ያሬድ የሱራፌል አምሳያ ነው።
  • አቡነ ያሬድ ጥዑመ ልሳን ነው።
  • ቅዱስ ያሬድ የቤተ ክርስቲያን እንዚራ ነው።
  • ቅዱስ ያሬድ የቤተ ክርስቲያን ብርሃን ነው።
  • ቅዱስ ያሬድ መዓርዒረ ዜማ ነው።
  • አቡነ ያሬድ ካህን (ካህነ ስብሐት) ነው።
  • ቅዱስ ያሬድ ማኅሌታይ ነው።
  • ቅዱስ ያሬድ መዘምር ዘበድርሳን
  • ቅዱስ ያሬድ ሊቅ (ርእሰ ሊቃውንት)
  • ቅዱስ ያሬድ ዓርከ ሊቃውንት
  • አቡነ ያሬድ መንፈሳዊ ደራሲ ነው።
  • ቅዱስ ያሬድ የኢትዮጵያ ብርሃን ነው።
  • አንደበቱ ጣፋጭ (ጥዑም) የኾነ
  • እግሮቹ በመልካም መንገድ የሚጓዙና ወደ መልካም መንገድ የሚያስጕዙ
  • ልቡናው የቅድስና ማኅደር የኾነ
  • ሕሊናው የምሥጢራት ሠረገላ የኾነ
  • አእምሮው የመጠቀ
  • ድርሰቱ የተራቀቀ
  • እስከ አርያም ተነጥቆ ዕፁብ ድንቅ ምሥጢራትን የተመገበ የሱራፌል አምሳያቸው ነው።

ለዚህም ነው ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ቅዱስ ያሬድን እንዲህ ሲል ያመሰገነው፦

የመንፈስ ቅዱስ ምግብን የጠገበ፤ ከመጻሕፍት ኹሉ ትርጓሜያተ ድርሰትን ያሰባሰበ፤ ሃሌ ሉያ በሚል ምስጋና የኢትዮጵያ ሀገርን በጥዑም ማሕሌትና በሚያምር ምስጋና ያስጌጠ፤ የመለኮት ቃልን በላይዋ ላይ እንደ ንጹሕ የወርቅ ሻሻቴ ያፈሰሰ ለኾነ ለካህኑ ያሬድ ሰላምታ ይገባል

ሰላም ለያሬድ ቀሲስ ዘጽጉብ እክለ መንፈስ ቅዱስ፤ ዘአስተጋብአ ምድራሳተ እምኲሎሙ መጻሕፍት

ወአሰርገዋ በሐዋዝ ስብሐት ወበጥዑም ማሕሌት ለብሔረ ኢትዮጵያ በስብሐት ሃሌ ሉያ ዘከዐወ ቃለ መለኮት ዲቤሃ ከመ አስራበ ወርቅ ንጹሐ።

ቅዱስ ያሬድ አክሱም ጽዮንን እየተሳለማት ሣለ ክብርት እመቤታችን ለቅዱስ ያሬድ ተገልጣለት ቅዱስ ኤፍሬምንና ቅዱስ አባ ሕርያቆስን በአካለ ነፍስ አምጥታ ድርሰታቸውንና ቅዳሴያቸውን እንዲያሰሙት በማድረግ ቅዱስ ያሬድንም ዜማውን እንዲደርስ እረድታዋለች፡፡ ኹለቱንም ታላላቅ ቅዱሳን ነጥቃ ወደ ቅዱስ ያሬድ ካመጣቻቸው በኃላ “አንተ ውዳሴዬን፣ አንተ ቅዳሴዬን ነግራችሁት በዜማ ያድርስ” ብላቸው እነርሱም ለቅዱስ ያሬድ ነግረውት በዜማ አድርሶታል፡፡ ቅዱስ ያሬድም በመልክ በመልኩ እያደረገ ዜማውን ደረሰው፡፡ ዜማውንም ሲጨርስ የብርሃን እናቱ እመ አምላክ በያዘችው የብርሃን ባርካው ተስፋውን ነግራው ዐርጋለች፡፡

ይኽም የቅዱስ ያሬድ ድርሰቱ መነሻውም ሆነ መድረሻው ፍጹም መንፈሳዊ እንደሆነ ያሳያል። አባቶቻችንም ይኽን መንፈሳዊ መገለጥ በሥዕልም ጭምር ገልጠውታል። (ሽሬ መድኃኔዓለም ቤ/ክ ይኽ ዓይነት ሥዕል ከሚገኙበት ገዳማት ውስጥ የሚገኘው አንዱ ነው።)

አቡነ ያሬድ ይባርክበት የነበረው የእጅ መስቀሉ በ1985 .ም በሆድ አደር ሌቦች አማካኝነት ተሰርቆ ከሀገር ወጥቶ ነበር። በፈረንሳይ ሀገር ለጨረታ ቀርቦ በ15 ሚሊዮን ዶላር ተሸጦ ነበር። ነገር ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ተሰርቆ ከወጣ ከ18 ዓመት በኃላ በ2003 ወደ አገራችን ተመልሶ መጥቷል። ሊመለስ የቻለውም ሚስተር ዣክየተባሉ በጎ አሳቢ ሰው “…ይህን መስቀል ኢትዮጵያ ውስጥ ጎብኝቼዋለሁ፣ የኢትዮጵያ ንብረት ነውበማለት ወደ ሀገራችን እንዲመለስ ከሌሎች አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ልጆች ጋር በተደረገ ርብርብ ጨረታውን በ15 ሚሊዮን ዶላር አሸንፈው የአቡነ ያሬድን የእጅ መስቀል ወደ አገራችን መልሰውታል። አምላከ ቅዱስ ያሬድ ክብር ያድልልን በእውነት!

አቡነ ያሬድ በምናኔ በኖረበት ቅዱስ ቦታ ላይ በስሙ ገዳም ተገድሞ መናንያን አሰረ ፍኖቱን ተከትለው ጤዛ ልሰው ድንጋይ ተንተርሰው፣ በረዶውንና ውርጩን ታግሠው በስሙ እየተማጸኑ ይኖራሉ፡፡ በቦታው እሁድ እሁድ ከመሬት ውስጥ የከበሮ ድምጽ ይሰማል፣ ቅዱስ ያሬድ መቋሚያውን ወርውሮ ያፈለቀው ፀበል ዛሬም አለ፡፡ ጻድቁ በተሰወረበት በደብረ ሐዊ ተራራ ላይ ብርድ በእጅጉ በጸናበትና በረዶ በሚፈላበት በዚያ አስቸጋሪ ቦታ ላይ እጅግ አስቸጋሪውን የአየር ጠባይ ተቋቁሞ በቦታው ላይ ቢያንስ 7 ቀን ሱባዔ የሚይዝ ካለ ራሱ ቅዱስ ያሬድ እንደሚገለጥለት በቦታው ላይ የሚገኙ አባቶች ይናገራሉ።

አክሱም አቅራቢያ ቁጭ ብሎ ከትሏ ምሳሌ ወስዶ በተማረበት ቦታ ላይ አንዲት እናት ብቻዋን ለቅዱስ ያሬድ አስደናቂ ቤ/ክ በ2010 .ም አሠርታለታለች። ይኽም ለጻድቁ ለአቡነ ያሬድ ተስላ ስለቷ ደርሶላት እንደሆነ በቦታው ላይ ተነግሮናል። ይኽም ድንቅ ምስክርነት አቡነ ያሬድ ከዜማ ደራሲም በላይ መሆኑን አንድ ማሳያ ነው። በጸሎቱ ሀገርን የሚጠብቅ ባሕታዊ፣ በስሙ ለሚማጸኑት ሁሉ ከአምላኩ ዘንድ ምሕረትን የሚለምን ደገኛ ጻድቅ መሆኑን አንድ ማሳያ ነው።

የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሙሉ አካሏና ብርሃኗ የኾነው አቡነ ያሬድ እንደነ ሄኖክና ኤልያስ ሞትን ሳያይ የተሰወረው በዛሬዋ ዕለት ነው። የከበረች በረከቱ ትደርብን! በጸሎቱ ይማረን!!!

___________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: