Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2020
    M T W T F S S
     123
    45678910
    11121314151617
    18192021222324
    25262728293031
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for May 15th, 2020

France24 | አብዮት አህመድ ሰሜን ኢትዮጵያውያንን እንደ አፄ ኃይለ ሥላሴ በርሃብ ሊቀጣ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 15, 2020

The Last Emperor of Ethiopia: Haile Selassie’s Legacy Remains Divisive

ሰሜን ኢትዮጵያውያንን በረሃብ የመጨረሱ ሤራ ዛሬም ቀጥሏል እያለን ነው ይህ ዛሬ በፈረንሳዩ የቲቪ ጣቢያ የተሰራጨው ቪዲዮ።

እነዚህ አውሬዎች እኮ በመፈንሳውያኑ ሰሜን ኢትዮጵያውያን ላይ ያላቸው ጥላቻ ተወዳዳሪ የለውም፤ ከእረኛው እስከ ተማሪው ፣ ከጋዜጠኛው እስከ ጠቅላይ ሚንስትሩ ያላቸውን ጥላቻ ከጦርና ጋሻ በቀር ሌላ ሊያስወግደው የሚችል ነገር የለም።

ላለፉት 150 ዓመታት ስጋውያኑ ደቡብ ኢትዮያውያን(አፄ ሚኒልክና ኦሮሞ አማካሪዎቻቸው፣ አፄ ኃይለ ሥላሴና ኦሮሞ አማካሪዎቻቸው፣ መንግስቱ ኃይለ ማርያም እና ኦሮሞ መንግስቱ፣ ህዋሀት እና ኦሮሞ አጋሮቹ፣ ዛሬ ደግሞ አብዮት አህመድና የዋቄዮአላህ አህዛብ መንግስቱ መንፈሳውያኑን ሰሜን ኢትዮጵያውያንን (ቤተ አምሓራን እና ትግራይን) በረሃብ ሲጨፈጭፏቸውና ለመጨፍጨፍ በመዘጋጀት ላይ ናቸው። አልመኝላቸውም፤ ነገር ግን ስጋውያኑ ደቡብ ኢትዮጵያውያን ላለፍቱ 150 ዓመታት አንዴም በረሃብ ያልተጠቁበት ምስጢር ይሄ ነው። በዚህ ዘመን እያንዳንዱ መንግስት መንፈሳውያን ኢትዮጵያውያንን በጣም የሚጎዳ ነበር። በዚህ ዘመን እንኳን ከሰሜን መጡ የተባሉት ህዋሃቶች ያው ስልጣኑን ለመንፈሳዊቷ ኢትዮጵያ ጠላቶች አስረክበው ሄደዋል። በዚህ ድርጊታቸው በጣም ተጠያቂዎች ይሆናሉ! ወገን ልብ በል፤ ከታሪክ ተማር!ጠላት መጥፎው የታሪክ ሂደት እንዲደገም ይሻል፤ የተዋሕዶ ክርስቲያኑ በረሃብ ተገርፎ፣ ወኔው፣ ሃሞትና ነፍጡ ሲኮላሽ ማየቱን በጣም ይመኘዋል፤ ጣቢያውም ይህን ማቅረቡ ያለምክኒያት አይደለም ፥ በደንብ ያውቁታል፤ መንፈሳውያን ኢትዮጵያውያንን በጦርነት ሳይሆን በረሃብ ብቻ ማንበርከክ እንደሚቻል አይተውታል።

_______________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos, Life | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አውሬው መንግስት የተመረዙ ጭንብሎችን መልበስ የሚያስገድደው ኢትዮጵያውያንን ለማድከም ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 15, 2020

አዎ! ለምርምራቸው ሆነ ለሌላ ብዙ ጉዳይ እንደ አዲስ አበባ ባሉ ከፍተኛ ቦታዎች ላይ የሚኖሩ ሕዝቦችን እጅግ በጣም ይፈልጓቸዋል!

አብዮት አህመድና ሉሲፈራውያኑ ሞግዚቶቹ እንዳቀዱት ኢትዮጵያውያንን በኮሮና ወረርሽኝ መሰባበር አልተቻላቸውም፤ ስለዚህ አሁን አካሄዳቸውን ትንሽ ቀየር አድርገው በእንጭብል በኩል፣ ቀጥሎም በመድኃኒት፣ በምግብና መጠጥ በኩል ይመጡብናል።

የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል አደገኛ ነው፤ ከባድ የኦክስጅን እጥረት ያስከትላል።

እንዳውም ጭንብሉን ያጠለቁት ሰዎች ካላጠለቁት በቫይረሱ በይበልጥ ሊጠቁ እንደሚችሉ የህክምና ተመራማሪዎች በማሳወቅ ላይ ናቸው። በዚያ ላይ ጭንብሎቹ መርዛማ ኬሚካሎችን ከያዙ ነገሮች እንደሚመረቱና እንደ አዲስ አበባ የኦክስጅን መጠን በጣም ዝቅተኛ በሆነባቸው ከፍተኛ ቦታዎች ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች በዚህ በይበልጥ ሊጠቁ እንደሚችሉ መታወቅ ይኖርበታል።

ቪዲዮው ላይ እንደሚታየው በደቡብ አሜሪክዋ ፔሩ ከፍተኛ በሆኑ ቦታዎች ላይ የሚኖሩ ሰዎች ጭንብሉ በፈጠረው የኦክስጅን እጥረት የተነሳ ክፉኛ እየታመሙና እየሞቱ ነው።

እንደ አዲስ አበባ ከፍተኛ በሆኑ ቦታዎች ላይ የሚገኙ ከተሞች የኦክስጅን መጠን በባሕር ጠለል ላይ ከሚገኙ ቦታዎች በ 30 – 60 % ያነሰ ነው። አየሩ ላይ ብዙ ኦክስጅን የለም ማለት ነው። እንደ አዲስ አበባ በመኪና ናፍጣ አየሩ በተበከለባቸው ከፍተኛ ቦታዎች ላይ በሚገኙ ከተማዎች ላይ ጭምብል ማድረግ፤ የሚገኘው የኦክስጅን መጠን ምናልባት በ80% ያነሰ ይሆናል። ሰው ያንቀላፋል፣ ጤንነቱ ክፉኛ ይታወካል፣ እንደ አስማ የመሳሰሉ የጤና ችግሮች ያሉበት ይሞታል ማለት ነው። ኦክስጅን አየር አልቆ በካርቦን ዳይኦክሳይድ ብቻ ይጥለቀለቃል ማለት ነው። መርዝ!

አውሬው ይህን ያውቃል፤ ኢትዮጵያውያን የህክምና ባለሙያዎችም ይህን በሚገባ ያውቁታል፤ ነገር ግን ቡዙዎቹ የአውሬው አገልጋይ ስለሆኑ ይህን በጣም አስፈላጊ የሆነ መረጃ ላስተማራቸው ድሃሕዝብ እንዳያካሉት አፋቸው በዘዴ ተለጉሟል።

ኮሮና ኢትዮጵያ ውስጥ የለም፤ ገብቶም ከሆነ የግራኝ አህመድ መንግስት ነው በሻንጣና በአውሮፕላን ያስገባት። እንደተመኙትና እንደጠበቁት ቫይረሱ ኢትዮጵያውያንን አልገደለላቸውም፤ ስለዚህ አሁን አውሬው መንገስት ማንኛውም ሰው የፊት መሸፈኛ (ጭንብል) መልበስ እንዳለበት አስገዳጅ መመሪያ አውጥቶ ያልለበሱትን ምስኪን ኢትዮጵይይ እያሳደደ በማሰር ላይ ነው። ቤተ ክርስቲያን ገብቶ የሚገድል መንግስት ለሕዝቡ ጤና ሊያስብ?

እስኪ እንታዘበው በብዙ ሺህ ነዋሪዎቻቸውን በኮሮና ቫይረስ ባጡት የአውሮፓ ሃገራት እንኳን ጭንብል የመልበስ ግዴታ የለም። እንዲያውም በተቃራኒው አሁን ከቤተ ክርስቲያን እስከ ቡና ቤቶች ሁሉም በሮቻቸውን ለምዕመናን እና ለጎብኝዎች በመክፈት ላይ ናቸው።

👉 በከፍተኛ ቦታ ላይ የሚገኙ ፲ /አሥሩ የዓለማችን ዋና ከተማዎች (ሁሉም በአፍሪቃ፣ እስያ እና ላቲን አሜሪካ ብቻ ነው የሚገኙት)

ከባህር ጠለል በላይ፦

  • ፩ኛ. ላ ፓዝ ፥ ቦሊቪያ ፤ 3,640 ሜትሮች ከፍታ
  • ፪ኛ. ኪቶ ፥ ኤኳዶር ፤ 2,580 ሜትሮች ከፍታ
  • ፫ኛ. ቦጎታ ፥ ኮሎምቢያ ፤ 2,625 ሜትሮች ከፍታ
  • ፬ኛ. አዲስ አበባ ፥ ኢትዮጵያ ፤ 2,355 ሜትሮች ከፍታ
  • ፭ኛ. ቲምፉ ፥ ቡታን ፤ 2,334 ሜትሮች ከፍታ
  • ፮ኛ. አስመራ ፥ ኤርትራ ፤ 2,325 ሜትሮች ከፍታ
  • ፯ኛ. ሳናአ ፥ የመን ፤ 2,250 ሜትሮች ከፍታ
  • ፰ኛ. ሜክሲኮ ከተማ ፥ ሜክሲኮ ፤ 2,240 ሜትሮች ከፍታ
  • ፱ኛ. ቴህራን ፥ ኢራን ፤ 1,830 ሜትሮች ከፍታ
  • ፲ኛ. ናይሮቢ ፥ ኬኒያ ፤ 1,795 ሜትሮች ከፍታ

👉 የሚከተለውን ከወር በፊት በጦማሬ ጽፌ ነበር፦

ኮሮና ቫይረስ – አውሮፕላን – ኦክስጅን – እስትንፋስ – እጣን

5ጂ ቴክኖሎጂ ገና ያልገባባት ኢትዮጵያ ደግሞ ለዚህ ቫይረስ ስርጭት ጥናት በጣም አመቺ በመሆኗ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቻይና የሚያደርገውን በረራ እንዳያቋርጥ ተደረገ። በአለማችን እንደ አዲስ አበባ ከባህር በላይ በ2500 ሜትር ከፍታ ላይ በብዙ ሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚኖሩባቸው ቦታዎች ጥቂት ናቸው። እናስታውስ ከሆነ እ..አ በ2006 .ም ላይ የአውሮፓውያኑ ግዙፍ አውሮፕላን ኤርበስ 380 የከፍተኛ ቦታ ሙከራ በረራውን በአዲስ አበባ ነበር ያካሄደው

የኢትዮጵያ ከተሞች ከፍተኛ ቦታዎች ላይ ስለሚገኙ ለምሳሌ በአዲስ አበባ የሚገኘው የኦክስጂን (ጽሩህ አየር) መጠን በአውሮፓ፣ አሜሪካ ወይም አረቢያ ከሚገኘው የኦክስጂን መጠን በ30% ያነሰ ነው። ብዙ ኦክስጅን ባለመኖርና አየሩም ቀጭን በመሆኑ የደገኛ ኢትዮጵያውያን ሳንባዎች ትልልቅና ቀይ የደም ሕዋሳታቸውም የበዛ፤ ባጭሩ በጣም ጤናማ የሆነ አካል አላቸው። የኢትዮጵያውያኑ አካላዊ ጤናማነት ከመንፈሳዊው ብርታት ጋር መደመሩ ሉሲፈራውያኑን ያስፈራቸዋል፣ ያስቀናቸዋል፣ ያስጠላቸዋል። ስለዚህ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ይህን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለመዋጋት ብዙ ሲደክሙ ይታያሉ።

ባለፈው ዓመት ልክ በዚህ ዕለት፤(መገጣጠሙ የሚገርም ነው!)መጋቢት 252011 ላይ በባህር ዳር ከተማ የሚገኘው የፈለገ ሕይወት ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል የሜዲካል ኦክስጅን ማምረቻና ማከፋፈያ ማዕከል ተመረቆ ነበር። በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በኢትዮጵያ ደረጃውን የጠበቀ የኦክስጅን አገልግሎት መስጠት ከተቻለ በእርግዝና ወቅት የሚሞቱ 11 ሺህ ሴቶች፣ በተወለዱ የመጀመሪያ ወራቶች የሚሞቱ 60 ሺህ ህፃናትንና በየዓመቱ በሳንባ ምች የተነሳ የሚሞቱ 30 ሺህ ህፃናትን መታደግ ይቻላልብለው ነበር።

በወቅቱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የነበሩት ዶክተር አንባቸው መኮንን ደግሞ፦ ማዕከሉ በኦክስጅን አገልግሎት እጥረት ምክንያት ረጅም ዕድሜ መኖር እየቻሉ በአጭር የሚቀጩ ኢትዮጵያውያንን ህይወት ለመታደግ የሚያስችል ነውሲሉ ተናግረው ነበር። ከሁለት ወር በኋላ ዶ/ር አንባቸው ኦክስጅኑን ሳይስቡ በገዳይ አብይ ተረሸኑ። በወቅቱ የጤና ሚኒስትር የነበሩትም ዶክተር አሚር አማን የአማራ ክልል ጤና ቢሮ፣ ሳልትስ ፕሮጀክት፣ ጂኢ ፋውንዴሽንና ግራንድ ቻሌንጅ ካናዳን ለዚህ ፕሮጀክት መሳካት ላደረጉት ጥረት ምስጋናቸውን በማቅረብ ብዙም ሳይቆዩ ከስልጣናቸው ተሰናብተዋል። ምን የሚይውቁት ነገር ይኖር ይሆን?

ለማንኛውም፤ ይህ ሉሲፈራውያኑ ያስቀመጡት መንግስት 100% የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ጠላት ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቻይና በረራውን አሁንም ቀጥሏል፣ የቱርክ አየር መንገድ ወደ አዲስ አበባ የሚበር ሌላው ብቸኛ አየር መንገድ ነው። ቅሌታማ በሆነ መልክ አላግባብ እስር ቤት ውስጥ እንዲገባ የተደረገው ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ፤ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የሚያመጣውን 200 ሺህ መቃብሮች እንዲቆፈሩ መንግስት ትዕዛዝ ሰጥቷል” ማለቱ በሰሜን ኢትዮጵያውያን ላይ ምን እየተዘጋጀ እንደሆነ በመንደርተኝነት ቫይረስ ላልተጠቃነው ዜጎች ብዙ የሚጠቁመን ነገር አለ። አብይ አህመድ አማራእና ትግሬየተባሉትን ኢትዮጵያውያንንን በወረርሽና እና ጥይት ሳይጨፈጭፍ እንቅልፍ አይወስደውም። አውሬው በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ላይ ከፍተኛ ጥላቻ ነው ያለው፤ ለዚህም ነው ሉሲፈራውያኑ ስልጣን ላይ አስቀምጠው የሚሸልሙት። ይህን ሁሌ እናስታውስ!

ባለፈው ጊዜ የአሜሪካ ባለሥልጣናት በቨርጂኒያ አካባቢ ያሉትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናትን በየመንገዱ ጸሎተ ዕጣን በማድረስ ማዕጠንት እንዲፈጽሙ መጠየቃቸውንም ያለ ምክኒያት አለመሆኑን እናስታውሰው። እንደሚታወቀው የአሜሪካ ስለላ ተቋም ሲ.አይ.ኤ ዋና መሥሪያ ቤት በቨርጂኒያ ግዛት ነው የሚገኘው።

ለማንኛውም አጋንንቱን እና ጨረሩን ሁሉ ከእኛ የሚያርቁልን ክቡር መስቀሉ፣ ጸበሉ እና እጣኑ ናቸው!

_______________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Health, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: