Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • May 2020
  M T W T F S S
   123
  45678910
  11121314151617
  18192021222324
  25262728293031
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

አህዛብ እስላም ፖሊሶች ምዕመናኑን ቤተ ክርስቲያን ገብተው ሲተናኮሉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 14, 2020

👉 ይህ ሁሉ ጉድ በዛሬይቷ ኢትዮጵያ እየተፈጸመ ነው፦

ፖሊስ፣ አስቸኳይ ዐዋጁን በማስፈጸም ሰበብ እናቶችንና አረጋውያንን በመገፍተር እና በመደብደብ፣ የተመደቡ ልዑካን እንዳይገቡ በመከልከል፣ አልፎም የቤተ ክርስቲያኒቱን ሥርዐተ አምልኮ በማጥላላትም የፈጸማቸው ድርጊቶች በስፋት ያነጋገረ፣

መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካወጀበት እና ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ማንም እገዛ ሳይጠይቃቸው የፖሊስ ኃይሎች በቤተ ክርስቲያን በር ላይ በመቆም የቤተ ክርስቲያኒቱ ሃይማኖታዊ ሥርዓተ አምልኮ በሚጻረር መልኩ ጥንቃቄ አድርገው የሚያገለግሉ የዘወትር ልዑካን ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተው በተወሰነው ቁጥር መጠን አገልግሎት እንዳያከናውኑ፣ ምእመናንም በአጸደ ቤተ ክርስቲያን ተገኘው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከምትሠጠው ምሥጢረ ቁርባን እንዳይሳተፉ፣ የክርስትና (ጥምቀተ ክርስትና)፣ ሌሎች ምሥጢራት፣ ሥርዓተ ፍትሐት እንዳያገኙ ከፍተኛ የሆነ የኃይል እርምጃዎች እየወሰዱ፣ እየተሳደቡ፣ እየደበደቡ ምእመናኑን እያስቸገሩ ይገኛሉ፡፡ ይህንንም የሚያደርጉት በራሳቸው ተነሳሽነት እና ቤተ ክርስቲያናችንን ዝቅ ያደረጉ በመሰላቸው የሌላ እምነት ተከታዮች ነው፡፡ ለማሳያ ያህል ከጸሎተ ሐሙስ እስከ ትንሣኤ ባሉት ሦስት ቀናት ብቻ በአንዳንድ አጥቢያዎች የተፈጠሩ አግባብነት የሌላቸውን ድርጊቶች እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡

👉 ላፍቶ ደ//ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን

09/08/2012

የደብሩን ዋና ጸሐፊ መጋቤ ሥርዓት ሀብቱ መረሳ በዋናው በር ላይ የተመደበው ፌደራል ፖሊስ አላስገባም ብሎ መልሷቸዋል። አስቸኳይ መውጣት ያለበት ደብዳቤ እንዳለ ቢያስረዱም በዱላ እጃቸውን መቶ አባሯል።

👉 በዕለቱ ሌሎች ብዙ የተደበደቡ ምእመናንም አሉ

10/08/2012

ከቤተ ክርስቲያን ቅጽር ውጪ ቄጤማ የሰጡ ቄሰ ገበዝ ኪዳነ ማርያም ለምን እንዲህ ታደርጋላችሁ በሚል በፖሊስ በመኪና ተጭነው ከወሰዷቸው ከተወሰነ ሰዓት በኋላ በማስጠንቀቂያ ተለቀዋል። እንዲሁም በዕለቱ የተደበደቡ እና የተገፈተሩ እናቶችም እንዳሉ የዐይን እማኞች አሉ።

በደብሩ በር ላይ ሱቅ ውስጥ የሚሠራ ዲ/ን ኤፍሬም የተባለ ልጅ ለምን እንዲህ ታደርጋላችሁ በማለቱ በዕለቱ እንደታሰረ እስከ አሁን አልተፈታም (ላፍቶ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ይገኛል)

እንዲሁም በዚያኑ ዕለት ለፍትሐት የመጣ አስክሬን ሁሉ አናስገባም ባሉ የፖሊስ ኃይሎች ተመልሷል።

12/08/2012

ምንም ምእመን ወደ ቅጽረ ቤተ ክርስቲያን አልገባም፤ ነገር ግን እየተሳለመ የሚመለሰውን ሰው መባዕ እና ስእለት ለመቀበል የወጡ ቄስ ብርሌ የሚባሉ አባት ሲሆኑ በሰዓቱ የመጡት ፖሊሶች በር ላይ ያገኙትን ሰው በከፊል ደብድበው ካባረሩ በኋላ አንዱ ሳጅን (የዕለቱ ሺፍት ኃላፊ ሳይሆን አይቀርም) የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል በዱላው ይመታዋል በቦታው የነበሩት ቄስም “ተው እባክህ እንዲህ አታድርግ” ቢሉትም ድጋሚ በዱላው ወደ መሬት ወርውሮታል።

ይህ ሲሆን ያዩ ምእመና በለቅሶ እና ዋይታ ሐዘናቸው ሲገልጡ ጭራሽ ቄሱን “አንተ ነህ ሕዝቡን የምታሳምፅ፣ ገና አለቅህም” ብሎ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወስዷቸዋል። በመቀጠልም ሕዝበ ምእመኑ በብዛት ወደ ፖሊስ ጣቢያው በመሄድ አስፈትተዋቸዋል።

በወቅቱ ሥዕሉን የደበደበው ፖሊስ በጣም ጠጥቶ እንደነበር አፉ ሁሉ ይተሳሰር እንደነበር በወቅቱ ያናገሩት ሰዎች ገልጸዋል።

በአጠቃላይ በደብሩ አካባቢ እየተደረገ ያለው ጉዳይ ሕግ ከማስከበር በላይ ወደ መብት ጥሰት የገባ ተግባር ነው።

👉 ሐመረ ኖኅ እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን

10/08/12

በእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ማታ ለመቁረብ የመጡ ምእመናንን ላይ አላስፈላጊ በሆነ ውክቢያና ግፍተራ ከመፈጸሙ ባሻገር ወደ ቅጽሩ አትገቡም በማለት ከአዋጁ ውጪ ተጽዕኖ በማሳደራቸው ምእመናን እንዳይቆርቡ ተከልክለዋል። በተጨማሪም አገልጋይ መነኮሳትና ዲያቆናት እንዲሁም ክርስትና የሚያስነሡ ምእመናንን ወደ ውስጥ እንዳይገቡ ተደርጓል።

15/08/12

በዚሁ ገዳም እናትና ልጅ ላይ ከፍተኛ ወከባ ከመፈጸሙም በላይ አገልጋዮችን እንዳይገቡ አግደዋል የተስፋ ግብረ ኃይሉን ባለመስማት ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ጫና ፈጥረዋል።

👉 መንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስና ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን

09/08/12

ቀዳሽ አገልጋዮችን ወደ ቅጽረ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ ከልክለዋል። በወቅቱ ከቤተ ክርስቲያኑ በር ላይ ለጥበቃ የቆመው አንደኛው ፖሊስ የፕሮቴስታንት መዝሙር በስልኩ እያደመጠ ምእመናንን አትገቡም በማለቱ በምእመናን ዘንድ ከፍተኛ ተቃውሞ የተነሣ ሲሆን በወቅቱ ኮሚሽነር ጌጡ ጋር ተደውሎ ሁኔታውን በቦታው የነበሩ የተስፋ ልኡክ ግብረ ኃይሉ እንዲረግብ አድርገውታል። ሆኖም በነጋታው ወደ ጣቢያ በመሄድ በአዳር ላይ የነበሩ ፖሊሶችን አስቀርበው ጥፋት የፈጸመውን ፖሊስ ጠቁመው ፖሊሳዊ እርምጃ እንደሚወሰድበት ተነግሯቸው ተመልሰዋል። እስካሁን በፖሊሱ ላይ የተወሰደ ርምጃ ስለ መኖር አለመኖሩ በጉዳዩ ላይ ይፋ የወጣ መረጃ አልደረሰንም።

👉 ማኅደረ ስብሐት ቅድስት ልደታና መድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን

08/08/12

በተፈጠረው አላስፈላጊ ሁካታ አንድ የፌዴራል ፖሊስ እስከ ጫማው ወደ ቤተ መቅደስ በመግባት ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን መናቁን በግልጽ አሳይቷል።

👉 ላፍቶ ፈለገ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን

08/08/2012 .

በቦታው የተመደቡት ፖሊሶች ለቁርባን የመጡ ምእመናን ወደ ቅጽረ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ በመከልከልና ድብደባም ለመፈጸም በመነሣሣት ሕዝበ ክርስቲያኑ ላይ ጫና ሲፈጥሩ ነበር።

👉 አያት ጣፎ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን

08/08/2012 .

በቦታው የተመደቡት ፖሊሶች ለቁርባን የመጡ ምእመናን ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ በመከልከላቸው በአንዳንዶችም ላይ የመገፍተርና የማባረር ድርጊቶችን በመፈጸማቸው ምእመናን ቅዱስ ቁርባን በሰንበት ት/ቤት አዳራሽ ለመቀበል ተገደዋል።

በአጠቃላይ በጥበቃነት የተመደቡት አንዳንድ የፖሊስ አካላት የታዘዙበትን ዓላማ በመተው ምእመናን ለቁጣ የሚጋብዙ ድርጊቶችን ሲፈጽሙ እንደነበር ከላይ በተጠቀሱት አጥቢያዎች የተከሰቱት ሁነቶች ማሳያዎች ናቸው። ስለሆነም የፖሊስ ኃይልን የሚያሰማራው አካል ከመጣብን ወረርሽኝ በተጨማሪ ተጨማሪ ችግር የሚሆኑ ጉዳዮች ከመከሰታቸው በፊት በአግባቡ ማጤን ያለበት ጉዳዮች አሉ። የሚመደቡበት ቦታ ቤተ ክርስቲያን እንደመሆኑ መጠን ሌላ እምነት ያላቸው ፖሊሶች መመደባቸው እንኳን በምእመናን ዘንድ ትልቅ ቅሬታን ሊፈጥርና ሆን ተብሎ እኛን ለመጉዳት እየተሠራ ነው የሚል አንድምታ እየተሰጠው ስለሆነ ከዚህ ጀምሮ ጥንቃቄ የሚያሻቸውን ጉዳዮች በአጽንዖት ተመልክቶ መፍትሔ መሻት ያስፈልጋል።

ምንጭ፦ ሐራ ዘተዋሕዶ

👉 ይህን በየካ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የተቀረጸ ቪዲዮ ከሦስት ዓመታት በፊት ነበር ያዘጋጀሁት። አውሬው የአህዛብ መንግስት እና አጋሮቹ በጣም ተዳፍረዋል፤ ፀረተዋሕዶ የሆነውን ዘመቻቸውን ቀስ በቀስ፣ አንድ በአንድና በቅደም ተከተል እያክሄዱ ነው። ዓላማቸውን በተግባር ሲፈጽሙ በግልጽ አሳይተውናል። ማታ ላይ ቤቶችን ያፈርሳሉ፣ የተዋሕዶ እናቶችን ያፈናቅላሉ፣ ቤተ ክርስቲያን ገብተው ይገድላሉ(አዲስ አበባ 22 + ናዝሬት) ቀን ላይ ደግሞ “ሰይጣን ከቤተ ክርስቲያን አይረቅም” የሚለውን አባባል በማስመስከርና የሾለ ጥርሳቸውን በማሳየት ዓብያተ ክርስቲያናትን በመክበብ ተዋሕዷውያንን በገዛ ቤተ ክርስቲያናቸው ይተናኮላሉ፣ ይሳደባሉ፣ ያንቋሽሻሉ። በግብጽ፣ በኢራቅ እና በሶሪያ ኦርቶዶክስ ወገኖቻችን ቀስበቀስ ጨፍጭፈው አገሮቻቸውን የነጠቋቸው ልክ በዚህ ዓይነት አካሄድ ነበር። አንዳንዶቻችን ለዘመናት ስንጠቁም የነበርነው ይህን ነበር ፥ ለመማር አሻፈፈረን ብለን ነው እንጅ ለነገሩማ ከፀሐይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም! ጥፋቱ የቤተ ክህነት፣ የመምህራን እና የምዕመናን ነው። ሁሉም ተለሳልሰው ቀጥተኛና ተባዕታይ የነበረችውን ቤተ ክርስቲያን አነስታይ አድርገዋታልና።

እግዚአብሔር አምላካችን ለስሙና ለክብሩ ህዝብን ከአህዛብ መካከል የለየው በህግ ነው። በዚህም ፈቃድ ደግሞ ያህዝብ በህግ የሆነን የመንፈስ ስምና ክብር ተቀብሏል። ያም ህግ ደግሞ ከማያምኑ ማለትም ስጋዊ ከሆኑት ጋር ምንም ዓይነት አንድነትና ግንኙነት እንዲፈጥር አያዝም። አይደለም እንደ መንግስታን እንደ አገር እንዲሁም እንደ ህዝብ አንድ መሆንን ይቅርና። የህይወትና የነጻነት ማለትም የጽድቅ መንግስት የሚመሰረተው በመንፈስ አካል ላይ ሲሆን ይህም ደግሞ ሰለ ስጋ ሞት ይናገራል። በዚህም ደግሞ ከስጋ ጋር አንድነትና ህብረት የለም። ምክኒያቱም የመንፈስ ማንነትና ምንነት ከስጋ ጋር በአንድነት ከተቀመጠና ህብረት ካደረግ ያ መንፈሳዊ አካል ስለሚሞት የስጋ ማንነትና ምንነት ግዥና የበላይ ይሆናልና ነው። “ሕዝብ” የተባለው መንፈሳዊ አካል “ስጋ” ከተባሉት ከአህዛብ ጋር ምንም ዓይነት ህብረትና አንድነት እንዲሁም ኪዳን እንዳያደርግ በህግ የታዘዘውም ስለዚህ የተፈጥሩ እውነት ነው። መንፈስና ስጋ አብረው ውለው ማደር ከጀመሩ ያ መንፈሳዊ አካል ከመሞት አይድንም፤ ይሞታልም።

እነዚህ የመንፈስ እና የስጋ ህጎች አንዱ አንዱን በማጥፋት ነው የሚነግሱት። በተለይም የስጋ አካል (አህዛብ) ህልውናውን የሚያስቀጥለውም ይሁን ምጣኔሃብታዊ ተጠቃሚነቱን የሚያስጠብቀውና ፓኦለቲክዊ የበላይነቱን የሚያረጋግጠው “መንፈስ” በተባ/ንለው ማህበራዊ ክፍል ኪሳራ ብቻ ነው። “እኩልነት”፣ “መቻቻል” ቅብርጥሴ የሚባሉትም የአውሬው ንድፈ ሃሳቦች ናቸው። እነዚህ ሁለት በተቃርኖ ላይ የተመሠረቱ ህግጋት እኩል ሊሆኑ በጭራሽ አይችሉም። አንዱ አንዱን ለማጥፋትና ለመግደል የተፈጠር ከሆነ “የበላይነት” እንጅ “እኩልነት” ሊኖር አይችልም።

ዛሬም ሆነ ላለፉት 150 ዓመታት ኢትዮጵያን እያስተዳደሯት ያሉት ጠላቶቿ ናቸው። ከመቶ ዓመታት በፊት የነበሩት “አጥፊ መሪዎቿ” ሳያውቁት ነበር፤ የዛሬዎቹ ግን በደንብ እያወቁት ነው ለጠላትነት የበቁት። መንግስታቱ በስጋ አካል ላይ የተመሰረቱ ስለሆኑ የሃገሪቱ ህዝብም በስጋ ህግ የተዘጋጀ ማንነትና ምንንነት ነው ያለው። ስለዚህ ሃገሪቱ ለሞትና ለባርነት ተላልፋ ለመሰጠት በቅታለች ማለት ነው። ስጋ ሲነግስ ሞትና ባርነት እንደሚነግስ ያው እያየነው ነው።

ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን ተቀዳሚ ዓላማና ተግባር ሊሆን የሚገባው ይህን የአህዛብ ስጋዊ መንፈስ በግልጽ መዋጋት ብቸኛ አማራጭ ነው። ተለሳላሽነት ወይም ለብ ለብነት ብልህነት አይደልም። “የግራኝ አህመድ መንግስት ኢትዮጵያን በስጋ ህግ የሚገዛ የአህዛብ መንግስት ነው፣ የመንፈሳዊ ኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላት ነው፤ ምድሪቱን ለሞትና ባርነት እንዲሁም ለጠላት አሳልፎ በመስጠት ላይ ያለ ጠላት ነው፤ በፍጥነት መወገድና መጠረግ አለበት።” የሚለው መርሆ የእያንዳንዱ ተዋሕዶ ልጅ መርሆ መሆን አለበት። በሃገር እግዚአብሔር አህዛብ ባለሥልጣን መሆን የለባቸውም! እውነቱን እውነት ፥ ሀሰትን ሀሰት ፥ ብርኃንን ብርኃን ፥ ጨለማን ጨለማ ፥ ጥቁሩን ጥቁር ፥ ነጩን ነጭ ማለት የክርስቲያኖች ግዴታ ነው፤ ሌላ “ቆዩ!” እየተባለ ጊዜን በስፍና ለመግዛት ወለም ዘለም ማለት አያስፈልግም።

ይህን ቪዲዮ ከሦስት ዓመታት በፊት ነበር የቀረጽኩት። አውሬው የአህዛብ መንግስት እና አጋሮቹ ፀረተዋሕዶ የሆነውን ዘመቻቸውን ቀስ በቀስ፣ አንድ በአንድና በቅደም ተከተል ነው እያክሄዱ ያሉት። ዓላማቸውን በተግባር ሲፈጽሙ በግልጽ አሳይተውናል። ማታ ላይ ቤተ ክርስቲያን ገብተው ይገድላሉ (አዲስ አበባ 22 + ናዝሬት) ቀን ቀን ደግሞ “ሰይጣን ከቤተ ክርስቲያን አይረቅም” የሚለውን አባባል በማስመስከርና ዓብያተ ክርስቲያናትን በመክበብ ተዋሕዷውያንን ይተናኮላሉ፣ ይሳደባሉ፣ ያንቋሽሻሉ። ጥፋቱ የቤተ ክህነት፣ የመምህራን እና የምዕመናን ነው። ሁሉም ተለሳልሰው ቀጥተኛና ተባዕታይ የነበረችውን ቤተ ክርስቲያን አነስታይ አድርገዋታልና።

________________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: