እንዴት ደስ ይላል፤ የኔ ውድ ንጉሥ ዳዊት ከ፲፭ ዓመታት በፊት ወደ አዲስና ልዩ ወደሆነ የሕይወት ጎዳና መራኝ። ለተሰወሩት እህቶቻችንና ቤተሰቦቻቸውም ተመሳሳይ ፀጋ ይስጥልን!
[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፳፪/፳፫]
፩ እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።
፪ በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።
፫ ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።
፬ በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።
፭ በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተትረፈረፈ ነው።
፮ ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።