አዎ! ተራራዎቿ እና ሜዳዎቿ ፣ አፈሮቿ እና ውሃዎቿ ፣ ደኖቿ እና አታክልቶቿ ሁሉም የተዋሕዶ ኢትዮጵያውያን ደም የፈሰሰባቸው ውድ የቤተ ክርስቲያን ንብርቶች ናቸው። ስለዚህ ለማረስ፣ ሕንፃ፣ መንገድና አደባባይ ለመሥራት ዓለማዊው መንግስት ነው የቤተ ክርስቲያን ፈቃድ ማግኘት ያለበት። እስኪ በአዲስ አበባ ብቻ ተመልከቱት፤ የት ነው አንድ ዜጋ ንጹሕ አየር፣ ንጹህ ውሃ፣ ንጹህ ፍቅርና ደስታን የሚያገኘው? ልክ እንደዚህች በሚያምር ደን እንደተከበበችው እንደ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ባሉት የተቀደሱ ሥፍራዎች አየደለምን? ግን አደራ! የሠፈሮቹንም ስም “ፈረንሳይ”፣ “ጀርመን” ፣ “ፒኮክ” ፣ “ቼችኒያ” ወዘተ በማለት ጠላትን ለወረራ አንጋብዝ!
ተአምር ሠሪው ሰማዕት ሆይ ፤ ፈዋሴ ዱያን እንደመሆንህ ከወፍ በሽታ ፈውሰህ የምታድን ነህና ልምናችንን ጸሎታችንን ዘወትር ቸል ሳትል ስማን ከሱ በኢ የሚቆጠሩ ልዩ ልዩ ነገሮች ይተላለፋሉና።
ኃያሉ ጊዮርጊስ ሆይ፤ ድካም የማይሰማህ ትጉህ ገበሬ ነህና ዳግመኛ እንዳያጣሉንና እንዳይተናኮሉን ጠላቶቻችን እንደ ጢስ አጥነህ፤ እንደ ጉም አብነህ ፈጥነህ አጥፋቸው። በአንተ ዘንድ ባለሟልነትን በመናፍቃንና በአላውያን ዘንድ የመፈራትን ግርማ እንዳጎናጸፍከው ከእኛ የተዋሕዶ ልጆችም በግዙፍ አካልና በረቂቅ መንፈስ ሊተናኰሉን በሚመጡ ጠላቶቻችን ላይ ድል የመንሣትን አክሊል አቀዳጀን። አሜን።
የፈረሰኛው ሰማእት የቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤትና ምልጃ አይለየን!
_________________________________
Like this:
Like Loading...