ኢትዮጵያውያን በዱባይ ለ40 ቀናት ታግተዋል ፥ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን ጃፓናውያንና አሜሪካውያንን ያመላልሳል
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 22, 2020
እስኪ ይታየን፤ ኢትዮጵያውያን በሃገራቸው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይገደላሉ፣ ከቤታቸው ይፈናቀላሉ፣ ይሰደዳሉ ፥ በውጭ ሃገር ደግሞ በየአውሮፕላን ማረፊያው እየተጉላሉ የድርሱልን ጪኸት ያሰማሉ ፥ በሌላ በኩል ግን አብዮት አህመድ ለአረቦች፣ ለጃፓናውያንና ለአሜሪካውያን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖችን በፍጥነት ከች ያደርግላቸዋል።
ላለፉት ሁለት ዓመታት ይህን ያህል እየቀለደብህ ያለውን ይህን ህገ–ወጥ የወሮበሎች ስብስብ መንግስት የምትታገስ ደካማ ትውልድ አንቀላፋ፣ ገና ሌላ ጉድ ይጠብቀሃል። ደግሞ ትግሬ ስለሆነ በአቶ ተወልደ አሳብ፤ አቶ ተውለደ ገብረ ማርያም ይህን አውቆ ከሃላፊነቱ አስቀድሞ በፈቃዱ መውረድ ነበረበት። ሤራው ሆን ተብሎ የተጠነሰሰ ነው። በኢትዮጵያ አየር መንገድ እየታየ ላለው እራስን የመግደል አካሄድና ጥልቅ ውርደት ሙሉ ሃላፊነቱን የሚወስደው ግራኝ አህመድ አሊ ነው። ዛሬ የኢትዮጵያ አየር መንገድ CEO አብዮት አህመድ አሊ ነው። በዚህ ባልተለመደ የወረርሽኝ ዘመን በረራዎቹን መፍቀድና መላክ ፣ ማቆምና ማገድ የሚችለው እሱ ብቻ ነው። ከጃፓን እና አሜሪካ ፖለቲከኞች ጋር የሚያደርገው የስልክ ልውውጥም ለዚህ በቂ ማስረጃ ነው።
Leave a Reply