በቤተ ክርስቲያን ፍቅር ተውጠው፣ ለትንሣኤው ቤተ ክርስቲያንን የመረጧት ፯ ተዋሕዷውያን አረፈው ተገኙ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 20, 2020
በቤተክርስቲያን ፍቅር ተውጠው፣ ቤታችን አናድርም እናስቀድስ ብለው በትንሣኤው ዋዜማ ማምሻውን ከመኖሪያ ቤታቸው ወጥተው ህይወታቸውን ያጡት ስድስት ሴት እህቶች እና አንድ ታዳጊ ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ተተኪ አባላት በናዝሬት ወረዳ የዲቢቢሳና ዋጩላፋ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ልጆች መሆናቸው ታውቋል፡፡ ልብ በሉ፤ መጀመሪያ ላይ ስድስት ወንዶች እና አንዲት ሴት ተብሎ ነበር።
ቪዲዮው ላይ የሚታየው የቀብር ስነስርዓታቸው በዲቢቢሳ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን የምስራቅ ሸዋ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አባ ጎርጎርዮስ እና የሃገር ስብከቱ ሰራተኞችና አገልጋይ ካህናት እንዲሁም በርካታ የቀበሌ ገበሬ ማህበሩ ነዋሪዎች ፣ የናዝሬት ከተማ ክርስቲያኖች በተገኙበት ተፈጽሟል።
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ህፃናቱን አስባቸው፤ በእቅፍህ አስቀምጣቸው፡፡
Leave a Reply