ዓርብ ስቅለት | ተፈጸመ! | ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ ወጣን
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 17, 2020
ዓርብ ስቅለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ ‹የድኅነት ቀን› ይባላል፡
👉 ጌታችን ሲሰቅል የሚከተሉት ሰባት ተአምራት ተፈጽመዋል፤
- ፩. ፀሐይ ጨለመ፤
- ፪. ጨረቃ ደም ኾነ፤
- ፫. ከዋክብት ረገፉ፤
- ፬. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ተቀደደ፤
- ፭. አለቶች ተፈረካከሱ፤
- ፮. መቃብራት ተከፈቱ፤
- ፯. ሙታን ተነሡ (ማቴ. ፳፯፥፶፩–፶፬)
👉 ጌታችን በመስቀል ላይ ሳለ የሚከተሉትን ሰባት ዐበይት ቃላት አሰምቶ ተናግሯል፤
- ፩. “ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ (አምላኪየ አምላኪየ ለምን ተውኸኝ?)”፤
- ፪. “እውነት እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትኖራለህ“፤
- ፫. “አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁትምና ይቅር በላቸው“፤
- ፬. እመቤታችንን “ሴትዮ ሆይ፣ እነሆ ልጅሽ“፤ ደቀ መዝሙሩንም “እናትህ እነኋት” በማለት የቃል ኪዳን እናትነትና ልጅነት ማከናወኑ፤
- ፭. “አባት ሆይ በአንተ እጅ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ“
- ፮. “ተጠማሁ“፤
- ፯. “ዅሉ ተፈጸመ“ (ማቴ. ፳፯፥፵፭–፵፮፤ ሉቃ. ፳፫፥፵፫–፵፮፤ ዮሐ. ፲፱፥፲–፴)፡፡
Leave a Reply