ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 14, 2020
በእኛ ላይም የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ላከ፤ የቅድስት ቢተ ክርስቲያንህንም ደጆች በምሕረትና በሃይማኖት እንዲከፈቱ አድርግልን። እስከ መጨረሻዪቱ ሕቅታም ድረስ ልዩ ሦስትነትህን ማመንን ፈጽምልን።
የቤተክርስቲያን ሸምጋይ እና አስታራቂ ሆኖ የመጣው ልወደድ–ባይ የአውሬው መንግስት ኮሮናን ተገን አድርጎ ሕዝበ ክርስቲያኑን ከቤተ ክርስቲያን ለማራቅ ከፍተኛ ሥራ እየሠራ እንደሆነ እያየነው ነው። የክርስቶስ ተቃዋሚው የቤተ ክርስቲያንን ቦታ ለመውረስ ተወዳጅነት እያጡ የመጡትን ቴሌቪዥን እና ኢንተርኔት ጣቢያዎች (ኢቢሲ፣ ፋና)የሰሙነ ሕማማት ሥርዓተ ጸሎት በቀጥታ በማስተላለፍ ላይ ይገኛል። የቤተ ክርስቲያንን እና ሜዲያዎቿን ኃላፊነት በመንጠቅ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፎች ይመታል ማለት ነው።
ሲጀመር ዲያብሎስ አስታራቂ ሆኖ እንዲገባብን መደረግ አልነበረበትም፤ ካሜራዎቹንም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንዲያስገባ መፈቀድ አልነበረበትም። መንግስትና ሜዲያዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ እየሠሩት ያሉት ወንጀል ለይቅርታ፣ ለዕርቅና ለንስሐ የሚያበቃ አይደለምና።
በደመራ ዕለት መስቀል አደባባይ አጥር ላይ የተላተመችውን የኢቢሲ ድሮን ካሜራ እናስታውሳለን? በሬውንስ? እነዚህ ነገሮች ያለምክኒያት አልተከሰቱም! ዛሬ ግራኝ አህመድ በክቡር መስቀሉ የተሰየመውን አደባባይ እና የጃን ሜዳን ጥምቀተ ባሕር ለመውረስና ያለመውንም አንጋፋ መስጊድ በቅርቡ ለመሥራት በመንቀሳቀስ ላይ ነው። በኮሮና ድራማ ተጠምደን ጸጥ ብለናል፤ አይደል! አዎ! የበሬውን አንጀት ለሞኙ ኢትዮጵያዊ ሰጥቶ አፉን ይዘጋና ሰንጋውን ለራሱ በማግበስበስ ላይ ነው። ትንሽ ከፊት ሲሆን ሀገር ያሳንሳል!
“….ሰዎች ጥቅም ወዳድ ናቸውና በጥቅም ሂድባቸው…የሚፈልጉትን እያሳየህ ወደምትፈልገው ስፍራ ውሰድ እና ጣላቸው… ከዚያም በሬ ሆይ! ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ… ብለህ ተርትባቸው” ብሎን የለ ተሳላቂው አብዮት። በመስቀል አደባባይ ደመራ ዕለት በሬው የተላከውም በቤተ ክርስቲያን እና ክቡር መስቀሉ ላይ ለመሳለቅ ታስቦ ነበር። አንርሳው!
ወገኖቼ መታለሉ ይብቃ! ይብቃ! ይብቃ! ንቁ! እንንቃ! ነፍሱ እንዳይታወክበት የሚሻ የተዋሕዶ ልጅ ይህን የቀጥታ ስርጭት በዚህ ሰሙነ ሕማማት ከመከታተል መቆጠብ ይኖርበታል።
Leave a Reply