የክትባት ባለ እናት መሊንዳ ጌትስ | አፍሪቃን ቶሎ ካልከተብናት ሬሳዎች መንገድ ላይ ተጥለው ይታያሉ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 14, 2020
የቢል ጌትስ ባለቤት መሊንዳ ጌትስ፤ ስለ በሽታና ሞት እያወራች ትስቃለች፤ እንዲህም ትላለች፦
ክትባት፣ ክትባት፣ ክትባት ሌላ መፍትሔ የለም!!!“አፍሪቃውያንን” እኛ መርፌ ካልወጋናቸው ተስፋ የላቸውም። ልክ እንደ ኤኩዋዶር በቅርቡ በአፍሪካም ሬሳዎች በመንገድ ላይ እንደ ቆሻሻ ይወረወራሉ። የአፍሪቃ ወላጆች ጭንቀት እንቅልፍ ይነሳኛል።
“ማማ አፍሪቃ” መሆኗ ነው። ባሏ ቢል ከማይክሮሶፍት ኃላፊነቱ የተሰናበተው ያለ ምክኒያት አልነበረም። ተመልከቱ፤ በአፍሪቃ 54 አገራት አሉ፤ እነዚህ አገራት በመልክ ዓምድር፣ በአየር ጸባይ፣ በታሪክ፣ በባሕል፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በምጣኔ ሃብት እጅግ በጣም የተለያዩ አገራት ናቸው፤ ነገር ግን ሁሉም እንደ አንድ ሃገር “አፍሪቃ” እያሉ መጥራቱን ይመርጣሉ፤ እንደነርሱ፤ አፍሪቃ አህጉር ሳትሆን አንድ አገር ናት።
የሚገርመው ግን አፍሪቃ በኮሮና እምብዛም ያልተጠቃችው ብቸኛዋ አህጉር መሆኗ ነው። ይህ ደግሞ በጣም ያንገፈግፋቸዋል። ሁሉም የሚጠይቁት “ኮሮና በአፍሪቃ የኛን ያህል ለምን አልተስፋፋም?” የሚለውን ቅናትና ጥላቻ የተሞላበትን ጥያቄ ነው። እግዚአብሔር የአፍሪቃ ሃገራትን ይጠብቃቸው እንጂ ከዚህ በፊትም እንዳወሳሁት በአፍሪቃ ኮሮናን የመሰለ ወረርሽኝ ከተቀሰቀስ(ማድረጋቸውም አይቀርም) እነዚህ አረመኔዎች ለጉብኝትና አደን የሚቋምጡላቸውን የዱር አራዊቱን አስቀርተው መላውን አህጉር ከመጨፍጨፍ እንደማያመነቱ እርግጠኛ መሆን ይቻላል። ሰሞኑን በዶ/ር ቴዎድሮስ ላይ የተቀሰቀሰው የጥቃት ዘመቻ ይህንን ነው የሚጠቁመን።
Leave a Reply