መቅሰፍቱን ያመጡት ሦስቱ የዋቄዮ-አላህ ሴት ልጆች ናቸው
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 25, 2020
የመሀመድ ሦስት የሴት አማልክት
ከእስልምና መምጣት በፊት ዐረቦች ብዙ ወንድና ሴት አማልክትን ያመልኩ ነበር፡፡ እያንዳንዱ ጎሳም የራሱ “አምላክ” ነበረው፡፡ በዛን ዘመን “አላህ” የሚታወቀው የጨረቃ አምላክ ተብሎ የነበረ ሲሆን፣ ሕዝቡን ከአላህ ጋር የሚያማልዱ ናቸው ተብለው ይታመኑ የነበሩ ሦስት ልጆች ነበሩት፡፡ እነዚህ የጨረቃው አምላክ አላህ–ከፀሐይዋ አምላክ ጋር ተጋብቶ ያስገኛቸው ልጆች በአንድነትም “የአላህ (ሴት) ልጆች” የተባሉ ሦስት አማልክት ስምም፦
👉 አል–ላት፤
👉 አል–ኡዛ
👉 አል–መናት
ነበር፡፡
እንግዲህ መኮረጅና መስራቅ ተግባሩ የሆነው ዲያብሎስ የእግዚአብሔር የሆነውን ሁሉ ለመዋጋት የማይፈጠረው ነገር የለምና፣ ምስጢረ ሥላሴንም በመኮረጅ የራሱ የሆኑ ሥላሴዎችን በየሃገሩ በመፍጠር ተቀባይነትን ለማግኘት ይሞክራል።
ዋቄዮ–አላህ የፈጠራቸው ሴት አማልክት በአፍሪቃ /በኦሮሞዎቹ “አቴቴ፣ በደቡብ አሜሪካ አማዞናስ ዙሪያ “ፓቻማማ” በህንድ “ሺቫ ከእነ ሦስት ልጆቿ/ቹ፤ ሳትቫ፣ ራጃስ፣ ታማስ“። ሁሉም የአል–ላት፣ አል–ኡዛ እና አል–ማናት አቻዎች መሆናቸው ነው። ኮፒ፣ ኮፒ፣ ኮፒ!
የመሀመዳውያኑ ቍርአን “ክርስቲያኖች በሦስት አማልክት ነው የሚያምኑት፤ እነሱም አብ፣ ኢሳ እና መርያም/ማርያም” በማለት ትልቅ ቅጥፈት ቀጥፏል። እርኩሱ መጽሐፉ ከዲያብሎስ ነውና ጣዖት አምላኪዎች ሁሉ በተመሳሳይ መልክ እየተንቀሳቀሱ ነፍሳትን የመግደል ዲያብሎሳዊ ተልዕኮ አላቸው። ኦሮሞዎች “አቴቴ” እና የደቡብ አሜሪካ ህንዶች “ፓቻማማ” “መርያም/ማርያም” ቦታ በማስያዝ፡ “ተመሳሳይ እምነት እኮ ነው ያለን” በማለት ለማወናበድ ይደፍራሉ ማለት ነው።
እግዚአብሔር አምላክ የዋቄዮ–አላህን መቅሰፍት ከሃገራችን ያርቅልን!
Leave a Reply