አብዮት አህመድ አንድ ትውልድ የቀጠፈውን ኦሮሞውን መንግስቱን ለመመለስ “ካራማራን” አነሳ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 6, 2020
ያውም በአድዋ መታሰቢያ በዓል ማግስት። እያየን ነው? እባቡ አብዮት የመስቀል ደመራን በዓል በኢሬቻ፣ የአድዋን ደግሞ በካራማራ ለመተካት ሰውን ቀስ በቀስ በማለማመድ ላይ ይገኛል።
ሞኙ ኢትዮጲያዊ ባለፈው ታሪክ ሂደት ላይ እንዲጠመድና ያለፉት ነገሥታት ስለሠሩት እንዲጨቃጨቅ ይደረጋል፤ እነዚህ የኢትዮጵያ ጠላቶች ግን በጀት ፍጥነት ሃገራችንን በመሸጥ እና በመቋረስ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ታሪክ የሌላቸው ወሮበሎች ታሪክህን በመስረቅ ታሪክ ለመስራት ቆርጠው ተነስተዋል። ወጣቱ ያለቸው አንዲት ሃገ ር ኢትዮጵያ ብቻ ናት፤ ነገር ግን አባቶቹ ያቆዩለትን ይህችን ሃገር ከጥፋት ከማዳንና እራሱንም ከመከላከል ይልቅ እንደተመቸው ድብ የሦስት ወር እንቅልፍን መርጧል፤ ይህን ወጣት ምን እንዳደረጉት፣ በምን በክለው እንዳስተኙት ለማወቅ ከባድ ነው። ዲያስፐራ ባለው ሃገር–ወዳድ ከበስተጀርባ አንድ ኢትዮጵያዊ የጥላ መንግስት (Shadow Government) በይፋ ተመሥርቶ ህዝቡና ኢትዮጵያዊ የሆነው የሠራዊቱ አባል ለአመፅ እስካልተቀሰቀሰ ድረስ እንደምናየው የኢትዮጵያ ልጆች የወሮበሎቹ የጠላት ቅጥረኞች መጫወቻ መሆኑን ይቀጥላሉ።
እስኪ ተመልከቱ ወገኖቼ 20 ልጃገረድ ተማሪዎች ለ80 ቀናት ያህል ታግተዋል፤ የነርሱን ጉዳይ በማስመልከት ተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ የማይገባቸውና ብቃት የሌላቸው፤ ወይንም ህን ተብለው የተመረጡ የግራኝ አህመድ ደጋፊዎች አንድ የዝግጅት ኮሜቴ እንዲያቋቁሙ ተደረጉ፤ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ የተቃውሞ ሰልፉ እንዳይካሄድ ተወሰነ፤ ልክ እንደ መስከረም ፬ቱ። በሌላ በኩል ግን ወጣቱ ልክ ሆዱ እንደሞላና እንቅልፍ እንደጠገበ ሰው በአደባባይ ወጥቶ እንዲጨፍርና በዓላትን ጸጥ ብሎ እንዲያከብር ፈቅደውለታል፤ በዚህም አንገብጋቢ የሆኑት ጉዳዮች እንዲረሱና ሁሉም ነገር ኖርማል እንደሆነ ተደርጎ እንዲቆጠር ለማድረግ እየተሞከረ ነው። በአደዋ መታሰቢያ ሆነ በካራማራው በዓላት ላይ የታገቱትን ምናልባትም የተገደሉትን እህቶቻችንን የሚያስታውስ
አንድ መፈክር እንኳን ይዞ የወጣ ሰው የለም። በየጎዳናው እየዞሩ የበዓሉን ተሳታፊዎች ሲጠይቁ የነበሩት “ገለልተኛ” የሚባሉት ሜዲያዎች እንኳን በዓላትን ለማክበር እድሉን ያላገኙትን የታገቱት እህቶቻችን ጉዳይ አስመልክቶ ጥያቄዎችን ሲጠይቁ አልተሰሙም? ይህ ምን ዓይነት ደካማ ትውልድ ቢሆን ነው?
Leave a Reply