ኮሮና ዜና | ኢትዮጵያ ወደብ የላትም ፥ አሜሪካ ያሏትን ወደቦች በመዝጋት ላይ ነች
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 5, 2020
ግብጾቹም ሆኑ ሌሎች አረቦች የተቀረውን ዓለም ሁሉ በተለይ አሜሪካን በጣም እንደሚጠሏቸው የታወቀ ነው፤ ነገር ግን ጠላቶቻቸው እንደሆኑ የሚያውቁት ፕሬዚደንት ትራምፕ ሳይቀሩ አረቦቹን እንደ ህፃን እያባበሉ ሲያስጠጓቸው ሳይ ሁሌ ይገርመኛል፤ አዎ! “ለእስራኤል ሲሉ ወይም Real Politics ቅብርጥሴ” እያሉ እራሳቸውን ሊያታልሉ ይችላሉ፤ ነገር ግን ከመለኮታዊው እውነት ፎቀቅ ብለው ማምለጥ አይቻላቸውም።
ግዮን አሜሪካን ዛሬም ወደ እባቧ ግብጽ እይጠራት ነው፤ ከግዮንና ኢትዮጵያ ጋር በተያያዘ የምትከተለው ትዕቢት የተሞላበት አካሄዷ ብዙ መስዋዕት ያስከፍላታል። ኢትዮጵያ ወደብ የለሽ ተደርጋለች፤ ሶስት መቶ ስልሣ አንድ የባሕር በሮች ያሏት አሜሪካም ወደ የለሽ መሆን ጀምራለች።
[ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፴፩፥፩፡፫]
“ስለ እርዳታ ወደ ግብጽ ለሚወርዱ በፈረሶችም ለሚደገፉ፥ ስለ ብዛታቸውም በሰረገሎች፥ እጅግ ብርቱዎችም ስለ ሆኑ በፈረሰኞች ለሚታመኑ፥ ወደ እስራኤልም ቅዱስ ለማይመለከቱ
እግዚአብሔርንም ለማይፈልጉ ወዮላቸው! እርሱ ግን ደግሞ ጠቢብ ነው፥ ክፉንም ነገር ያመጣል፥ ቃሉንም አይመልስም፥ በክፉም አድራጊዎች ቤት ላይ በደልንም በሚሠሩ ረዳት ላይ ይነሣል።
ግብጻውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፥ ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም፤ እግዚአብሔርም እጁን በዘረጋ ጊዜ፥ ረጂው ይሰናከላል ተረጂውም ይወድቃል፥ ሁሉም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።“
Tahir Kasim said
ጤና ይስጥልኝ!
ዛሬ አንድ ሀሳብ ልስጣችሁ ለዚህ ገፅ ፀሃፊውና ተከታዮች ፦ ጭፍን ጥላቻው ለሃረቦቹ ሰይሆን ለኢስልምና እምነት እንደ ሆነ ያሳብቅባቸዋል። ትልቅነት ሌላውን በመጥላትና በመናቅ አይደለም…