የአባይ ጦስ | መለስን ካስገደሉት ነገሮች አንዱ ይህ ኢንተርቪው ነበር | የእስራኤል ቴሌቪዥን እንዳየው
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 4, 2020
ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር ምንም ዓይነት ድርድር ማድረግ የለባትም፤ ለምን? ኢትዮጵያዊ መንግስት በሚኒሊክ ቤተ መንግስት ቢኖር ኖሮ ለግብጽ፡ “እኔ የምልሽን ተቀበይ፤ የአባይን ውሃ ከፈልግሽ አንድ ትሪሊየን ዶላር በዓመት ክፈይ” የማለት ተገቢ ድረት ይኖረው ነበር።
ብዙ “ኢ–አማንያን አብዮተኞችን” ካፈራው የጄነራል ዊንጌት ትምህርት ቤት የተመረቀው መለስ ዜናዊ ብዙ ስህተቶች ሰርቷል፤ ነገር ግን ከስህተቱ ተምሮ ለሃገራችን ጠቃሚ አስተዋጽዖዎችን ሊያበረክት የሚችል ፖለቲከኛ ነበር፤ ለዚህም ነው ነቃ ሲል የተገደለው። ጠላቶቻችን፡ በተለይ ነጮች ለነርሱ ይሰራ የነበረውንና ከስህተቱ የሚማረውን አፍሪቃዊ መሪ በጣም ይፈሩታልና። ኢትዮጵያን የጎዳው መንግስቱ ኃይለ ማርያምና ኢትዮጵያን እየጎዷት ያሉት እነ ኢሳያስ አፈወርቂ እና አብዮት አህመድማ ያው ምንም ሳይሆኑ እየተሸለሙ በሕይወት አሉ። ምንም ዓይነት ኢትዮጵያዊነትን የማያንጸባርቀው፤ አብዮት አህመድ ሳይሆን ሙሴ መባል የነበረበት፤ ዛሬ ቢኖር ኖሮ መለስ ነበር ሙሴ ወይንም ከስህተቱ የተማረው ሙሴ ጸሊም ሊባል የሚገባው።
Leave a Reply