የሳጥናኤል መንገዱን ከፍተው እኛ ላይ እንዲዘመትብን ያደረጉት “ኢትዮጵያ ሃገር ናት” ያሉን መሪዎቻችን ናቸው
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 4, 2020
“ያልተነገሩት የ24 ቀበሌ ኦርቶዶክሳውያን ጉዳቶች” በሚል ርዕስ በግሩም መልክ በተዋሕዶ ቴሌቪዥን የተቀነባበረና የቀረበ ቪዲዮ ነው። ወይዘሮ የሽን በጥሞና እናዳምጣቸው፤ ዓይኖቻቸውን ተመልከቱ … የኔ እናት…
ቤተ ክህነት ገዳዩን መንግስትንና ህገ-ወጡን የአዲስ አበባ መስተዳደርን ማክበር፣ መለመንና መማጸን ማቆም አለባት…. ደም የፈሰሰበትን ቦታ ወደዱም ጠሉም ለቤተ ክርስቲያን እንደሚሰጧት አትጠራጠሩ… ግን እንዲከበሩ፣ እንዲመሰገኑ፣ እንዲወደዱና እንዲመረጡ ገና የክርስቲያኑን ልብ ማንጠልጠል አለባቸው… አባቶችና ህፃናት አሁንም ተመርዘው እየታመሙ ነው፣ የተዋሕዶ ልጆች በሃገራቸው እንደ ሁለተኛና ሦስተኛ ዜጋ እንዲኖሩ እየተደረጉ ነው፤ ወጣት ሴት ተማሪዎች እየታገቱ፣ እየተደፈሩና እየተገደሉ ነው… ስለዚህ እነዚህን ገዳዮች ካባ ለማልበስ እንደቸኮላችሁት አህንም በስሜት ቀድማችሁ ለማመስገን እንዳትቸኩሉ…ይቅርታ የማይደረግለት ከፍተኛ ሃጢዓትና ወንጀል ሠርተዋልና፣ ለመስራትም በመዘጋጀት ላይ ናቸውና!
ቀደም ሲል ሉሲፈራውያኑ እንዲ ብለው ነበር፦
“ኢትዮጵያውያን “ዶክተር” የተባለውን ማዕረግ ያክብሩታል ፤ ኢትዮጵያን ከፍ እያደረገ የሚያወራውንና የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ የሚጠራውን ወሬኛም ያደንቁታል ስለዚህ አንድ ተዋሕዶ ያልሆነና የማይታወቅ ቆለኛ “ኦሮሞ” ስልጣን ላይ እናውጣ እና እዚህ በእኛ እጅ የገቡትን የቀድሞውን ፓትርያርክና አዲስ አበባ የሚገኙትን ፓትርያርክ “እንዲያስታርቅ” የመጀመሪያው ሥራው እንዲሆን አድርገን እንስጠው፣ እመኑን ሙሴ ተመልሶ መጣ ብለው ካባ ያለብሱታል…”
Leave a Reply