ከጥቂት ቀናት በፊት ዝነኛው የድሬስደን ከተማ የኦፔራ ቤት የቅዱስ ጊዮርጊስ ሽልማትን ለግብጹ ፕሬዚደንት አብዱል–ፋታህ አል–ሲሲ ለመስጠት ወሰነ፤ ይህም ብዙ ተቃውሞዎችን ቀሰቀሰበት። በተለይ ፕሬዚደንቱን እንዲሸልሙት የተጋበዙት ታዋቂ የጀርመን ሜዲያ ሰዎች “አምባገነኑን አል–ሲሲን በፍጹም አንሸልምም” ብለው በሽልማት ስነ ሥርዓቱ ላይ ለመገኘት ፈቃደኞች አልነበሩም።
እባብ አብዮትን የሰላም ሽልማት፤ ዘንዶ አል–ሲሲን የቅዱስ ጊዮርጊስ የሰላም ሽልማት ሰጧቸው። ዋው! እንግዲህ ይህ ሽልማት ግብጽ የባንዲራዋን ቀለማት ያዋሰቻቸውን ቅጥረኞቿን ኦሮሞዎችን እየደገፈች እንዳቀዱት ኢትዮጵያን ስላወከችላቸው መሆኑ ነው። አውሬው ኢትዮጵያን በእጁ ለማስገባት አመቺ ይሆንለት ዘንድ ከእንቁላሉ የፈለፈላቸውን ልጆቹን በየወሩ ይሸልማቸዋል። አላጋጮቹ ሉሲፈራውያን እንዲህ ነው እርስበርስ የሚሸላለሙት።
ከሐዲውና ጣዖት አምላኪው ዱድያኖስ በአምልኮ ጣዖት የፀና፣ እውነተኛውን አምላክ እግዚአብሔርንም የካደ ከመሆኑ የተነሣ የክቡር ጊዮርጊስን ራስ በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ፡፡ ድል አድራጊ ጊዮርጊስም እጅግ ደስ አለው፡፡ እሳት ከሰማይ አውርዶ ሰባውን ነገሥት ያቃጥላቸው ዘንድ መከራውም ከክርስቲያን ወገን ጸጥ ይል ዘንድ ጌታችንን ለመነው፡፡ ወዲያው እሳት ወርዶ ከሠራዊታቸው ጋር ሰባውን ነገሥታት አቃጠላቸው፡፡
የኢትዮጵያ ጠባቂ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆይ! ሀገራችንን በማተራመስ ላይ ያሉት ጣዖት–አምላኪ የዘመኑ ዱድያኖሶች ከያዙት እርኩስ ዓላማ ኢትዮጵያን ጠብቅልን ፣ እኛን ልጆቿንም በበረከት ጎብኘን አትለየን አሜን!