Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • February 2020
    M T W T F S S
     12
    3456789
    10111213141516
    17181920212223
    242526272829  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

አሜሪካ ከ፪ ዓመታት በፊት መፈንቅለ መንግስት አካሄደች፤ አሁን ደግሞ እስረኞችን አስፈታች | ሉዓላዊነት?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 27, 2020

የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሬክስት ቴለርሰን ህዋሀት መንግስቱን ለኦሮሞዎች አስረክባ ወደ መቀሌ እንድትሄድ አዘዟት፤ ዛሬ ደግሞ የጣልያን ዝርያ ያላቸው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዮ ኢትዮጵያ አባይን ለግብጽ እንድትሰጥ፣ አብዮት ደግሞ እስረኞችን እንዲፈታ ትዕዛዝ ሰጥተው ሳውዲ ገቡ።

መንፈሳዊ ወኔያቸው ተወዳዳሪ ባልነበረው በቀደሙት አባቶቻችን መስዋዕት ነፃነቷንና ማንነቷን ጠብቃ ለአምስት ሺህ ዓመታት የቆየችው ሀገራችን ኢትዮጵያ እውነት ዛሬ ሉዓላዊ ግዛት ናትን? እንዴት ነው፤ እግዚአብሔር በሰጠን ግዛት እኮ ማንኛውም ምድራዊ ኃይል እንዲህ አድርጉ! አሊያ…” ብሎ ሊያዘን አይችልም። ሥልጣን ላይ የተቀመጡት ወንበዴዎች እኮ በታሪክ ተወዳዳሪ የሌለውን የክህደት ተግባር እየፈጸሙ ነው። ላለፉት 150 ዓመታት ከተፈጸሙት በመዋዕለ ሕፃናት ደረጃ የሚፈጸሙ ስህተቶች እንዴት መማር አቃተን?

እስኪ ተመልከቱ፦

ጠላቶቻችን መላዋን ኢትዮጵያን እንደ በሬ ቅርጫ ከዳር እስከ ዳር እየተከፋፈሏት ኢትዮጵያውያን ግን አትኩሮታቸውን፣ ጊዚያቸውን፣ ጉልበታቸውን እና ገንዘባቸውን መጀመሪያ በትንሿአዲስ አበባ ላይ ብቻ ከዚያም በአንድ የአዲስ አበባ ክፍለ ከተማ ላይ፣ ቀጥሎም የክርስቲያኖች ደም በፈሰሰባት አንዲት ለአንድ በሬ የግጦሽ ቦታ እንኳን የማትበቃ ቦታ ላይ ብቻ እንዲያውሏቸው ኋላቀር የሆነ ዲያብሎሳዊ ተንኮል ተጠቀሙ። በበታችነት ስሜት የተሞሉት ጉረኞቹ የኢትዮጵያ ጠላቶች፤ እንኳን ኢትዮጵያን መላዋ አፍሪቃን መምራት እንችላለን!” የሚል ከንቱ መፈክር በማሰማት ልክ በሬ ለመሆን ብላ ሰውነቷን ስትነፋ በመጨረሻ ፈንድታ እንደ ሞተችው እንቁራሪት በመነፋፋት ላይ ናቸው ፤ መንደርተኛ እንዲሆን የተደረገውና የተዳከመው ኢትዮጵያዊው ግን ለቁራጭ ቦታ እንኳን ከጠላቶቹ ፈቃድ እንዲሰጠው ደጅ በመጽናት ላይ ይገኛል። እግዚአብሔር በሰጠው ሃገር!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመንግስት በላይ ናት፤ ስለዚህ በክርስቶስ ደም ላይ የተመሠረተችው ይህች ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፡ በቀራንዮ የፈሰሰው የጌታችን ደም አቅጣጫውን እንደጠቆማት፣ መንፈስ ቅዱስ እንደመራት በየትኛውም የኢትዮጵያ ግዛት፤ ከደቡብ ግብጽ እስከ ሞቃዲሾ ቤተ ክርስቲያን የመሥራት ሙሉ መብት አላትና የማንንም ፈቃድ መጠየቅ የለባትም። በ22/24 ስህተት የተፈጸመው፤ ልክ ቤተ መንግስት ቤተ ክርስቲያኑን ሲያፈርስና ሰማዕታቱ ወንደሞቻችንም በአብይ አህመድና ታከል ዑማ ትዕዛዝ ሲገደሉ ሕዝቡ ዶማና አካፋ፣ ሲሚንቶና ጡብ ይዞ ወደቦታው በማምራት የቤተ ክርስቲያን ህንጻ ግንባታውን ወዲያው መጀመር ነበረበት። አምስት ሚሊየን የአዲስ አበባ የተዋሕዶ ልጅ ወደዚያ ቢያመራ የትኛው ምድራዊ መንግስት ነው

ሊመክተው የሚደፍረው?!

ይህ አሁን መታየት የጀመረው የመንግስት መለሳለስ የተለመደው እባባዊ መለሳለስ ነው።

ምክኒያቱም፦

1. እንዲለሳለስ ትዕዛዙ የመጣው ከአሜሪካ ነው።

2. ኢንጂነር ስመኘውን፣ ጄነራሎቹንና ክርስቲያኖቹን የገደላቸው፣ እህቶቻችንን ያገታቸው/የገደላቸው

እርሱ መሆኑን እስራኤልና አሜሪካ በማወቃቸው ይሄን ካላደረግክ፤ ዋ!” እያሉ ስላስፈራሩት ነው።

3. ሰሜናውያኑ/ ደገኞቹ የተዋሕዶ ልጆች በመጭው የይስሙላ ምርጫእንደማይመርጡት ስላወቀ በመደናገጡ ነው።

ስለዚህ፤ ወገን ኧረ በቃህ! ኧረ አትታለል!ኧረ ከእባብ እንቁላል የዶሮ ጫጩት አትጠብቅ! ይህ መንግስት ስልጣኑን ሳይወድ በግድ አስረክቦ ለፍርድ እስካለቀረበ ድረስ ወደኋላ አትበል!ፍላጎቱንና ዕቅዱን ነግሮሃል፣ ተግባሩና ዓላማውም ቁልጭ ብለው እየታዩ ነው።

___________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: