Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 27, 2020
ጳጳስ ፍራንሲስኮ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁትን በትናንትናው ዕለት ህመምተኞች በጎበኙ ማግስት “በጉንፋን ነገር” መታመማቸው ተዘገበ።
የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ካርዲናል ብርሃነ ኢየሱስ ሱራፌል የኢሳያስ አፈወርቂ ቫይረስ በአስመራ አውሮፕላን ማረፊያ አገታቸው፤ ባለፈው ሳምንት ካርዲናሉ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረገ ስላለው ፀረ–ክርስትና ዘመቻ ማሳሰቢያ ነገር በመስጠታቸው ኢሳያስና አብዮት አህመድ የጠነሰሱት-እሳቻውን-የማሳፈሪያ ሤራ ይመስላል። ያሳዝናል!
ፍራንሲስኮስ ደግሞ ባለፈው መስከረም የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት መግቢያ ሰሞን በቫቲካን የደቡብ አሜሪካ “ህንዶች” የኢሬቻ ጣዖት አምልኮ ዛፍ ከተከሉበት ዕለት ጀምሮ ቀንድ በማብቀል ላይ ናቸው (በሌላ ቪዲዮ አቀርበዋለሁ)። ታዲያ አሁን የዚህ የኮሮና መቅሰፍት ሰለባ ሆነው ይሆን? ለማንኛውም ሁሉም እየተከሰተ ያለው ሃገራችን በቅዱስ ጊዮርጊስ እየተመራች በፋሺስት የጣልያን ሠራዊት ላይ ድል የተቀዳጀችበት ፩፻፳፬/124ኛውን የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል ለማክበር በምንዘጋጅበት ወቅት ነው። ኢትዮጵያ ስታነጥስ መላዋ ዓለም ጉንፋን / ኮሮና ይይዛታል!
____________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith, Health | Tagged: anti-Ethiopia Conspiracy, ሕዝብ ቁጥር ቅነሳ Vaccines, ቫቲካን, ተላላፊ በሽታዎች, ቸነፈር ወረርሽኝ, ቻይና, አድዋ, ኢትዮጵያ, ካቶሊክ, ኮሮናቫይረስ, ጣልያን, ጳጳስ ፍራንሲስኮ, ፀረ-ኢትዮጵያ ሤራ, Depopulation Agenda, Ethiopia, Italy | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 27, 2020
የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሬክስት ቴለርሰን ህዋሀት መንግስቱን ለኦሮሞዎች አስረክባ ወደ መቀሌ እንድትሄድ አዘዟት፤ ዛሬ ደግሞ የጣልያን ዝርያ ያላቸው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዮ ኢትዮጵያ አባይን ለግብጽ እንድትሰጥ፣ አብዮት ደግሞ እስረኞችን እንዲፈታ ትዕዛዝ ሰጥተው ሳውዲ ገቡ።
መንፈሳዊ ወኔያቸው ተወዳዳሪ ባልነበረው በቀደሙት አባቶቻችን መስዋዕት ነፃነቷንና ማንነቷን ጠብቃ ለአምስት ሺህ ዓመታት የቆየችው ሀገራችን ኢትዮጵያ እውነት ዛሬ ሉዓላዊ ግዛት ናትን? እንዴት ነው፤ እግዚአብሔር በሰጠን ግዛት እኮ ማንኛውም ምድራዊ ኃይል “እንዲህ አድርጉ! አሊያ…” ብሎ ሊያዘን አይችልም። ሥልጣን ላይ የተቀመጡት ወንበዴዎች እኮ በታሪክ ተወዳዳሪ የሌለውን የክህደት ተግባር እየፈጸሙ ነው። ላለፉት 150 ዓመታት ከተፈጸሙት በመዋዕለ ሕፃናት ደረጃ የሚፈጸሙ ስህተቶች እንዴት መማር አቃተን?
እስኪ ተመልከቱ፦
ጠላቶቻችን መላዋን ኢትዮጵያን እንደ በሬ ቅርጫ ከዳር እስከ ዳር እየተከፋፈሏት ኢትዮጵያውያን ግን አትኩሮታቸውን፣ ጊዚያቸውን፣ ጉልበታቸውን እና ገንዘባቸውን መጀመሪያ “በትንሿ” አዲስ አበባ ላይ ብቻ ከዚያም በአንድ የአዲስ አበባ ክፍለ ከተማ ላይ፣ ቀጥሎም የክርስቲያኖች ደም በፈሰሰባት አንዲት ለአንድ በሬ የግጦሽ ቦታ እንኳን የማትበቃ ቦታ ላይ ብቻ እንዲያውሏቸው ኋላ–ቀር የሆነ ዲያብሎሳዊ ተንኮል ተጠቀሙ። በበታችነት ስሜት የተሞሉት ጉረኞቹ የኢትዮጵያ ጠላቶች፤ “እንኳን ኢትዮጵያን መላዋ አፍሪቃን መምራት እንችላለን!” የሚል ከንቱ መፈክር በማሰማት ልክ በሬ ለመሆን ብላ ሰውነቷን ስትነፋ በመጨረሻ ፈንድታ እንደ ሞተችው እንቁራሪት በመነፋፋት ላይ ናቸው ፤ መንደርተኛ እንዲሆን የተደረገውና የተዳከመው ኢትዮጵያዊው ግን ለቁራጭ ቦታ እንኳን ከጠላቶቹ ፈቃድ እንዲሰጠው ደጅ በመጽናት ላይ ይገኛል። እግዚአብሔር በሰጠው ሃገር!
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመንግስት በላይ ናት፤ ስለዚህ በክርስቶስ ደም ላይ የተመሠረተችው ይህች ሐዋርያዊትና ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፡ በቀራንዮ የፈሰሰው የጌታችን ደም አቅጣጫውን እንደጠቆማት፣ መንፈስ ቅዱስ እንደመራት በየትኛውም የኢትዮጵያ ግዛት፤ ከደቡብ ግብጽ እስከ ሞቃዲሾ ቤተ ክርስቲያን የመሥራት ሙሉ መብት አላትና የማንንም ፈቃድ መጠየቅ የለባትም። በ22/24 ስህተት የተፈጸመው፤ ልክ ቤተ መንግስት ቤተ ክርስቲያኑን ሲያፈርስና ሰማዕታቱ ወንደሞቻችንም በአብይ አህመድና ታከል ዑማ ትዕዛዝ ሲገደሉ ሕዝቡ ዶማና አካፋ፣ ሲሚንቶና ጡብ ይዞ ወደቦታው በማምራት የቤተ ክርስቲያን ህንጻ ግንባታውን ወዲያው መጀመር ነበረበት። አምስት ሚሊየን የአዲስ አበባ የተዋሕዶ ልጅ ወደዚያ ቢያመራ የትኛው ምድራዊ መንግስት ነው
ሊመክተው የሚደፍረው?!
ይህ አሁን መታየት የጀመረው የመንግስት መለሳለስ የተለመደው እባባዊ መለሳለስ ነው።
ምክኒያቱም፦
1ኛ. እንዲለሳለስ ትዕዛዙ የመጣው ከአሜሪካ ነው።
2ኛ. ኢንጂነር ስመኘውን፣ ጄነራሎቹንና ክርስቲያኖቹን የገደላቸው፣ እህቶቻችንን ያገታቸው/የገደላቸው
እርሱ መሆኑን እስራኤልና አሜሪካ በማወቃቸው “ይሄን ካላደረግክ፤ ዋ!” እያሉ ስላስፈራሩት ነው።
3ኛ. ሰሜናውያኑ/ ደገኞቹ የተዋሕዶ ልጆች “በመጭው የይስሙላ ምርጫ” እንደማይመርጡት ስላወቀ በመደናገጡ ነው።
ስለዚህ፤ ወገን ኧረ በቃህ! ኧረ አትታለል!ኧረ ከእባብ እንቁላል የዶሮ ጫጩት አትጠብቅ! ይህ መንግስት ስልጣኑን ሳይወድ በግድ አስረክቦ ለፍርድ እስካለቀረበ ድረስ ወደኋላ አትበል!ፍላጎቱንና ዕቅዱን ነግሮሃል፣ ተግባሩና ዓላማውም ቁልጭ ብለው እየታዩ ነው።
___________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: ሉሲፈር, ሉዓላዊነት, መንፍቅለ መንግስት, ማይክ ፖምፔዮ, ሬክስ ቴለርሰን, ሲ.አይ.ኤ., ብልጽግና ፓርቲ, አሜሪካ, አባይ, ኢትዮጵያ, እስላም መንግስት, እስረኞች መፈታት, የሳጥናኤል ሴራ, ዶ/ር አብይ አህመድ, ጆን ቦልተን, ግራኝ አህመድ, ግብጽ, ጣልቃ ገብነት | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 27, 2020
[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፳፱]
፩ የአምላክ ልጆች ሆይ፥ ለእግዚአብሔር አምጡ። ክብርንና ምስጋናን ለእግዚአብሔር አምጡ።
፪ የስሙን ክብር ለእግዚአብሔር አምጡ፥ በቅድስናው ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ።
፫ የእግዚአብሔር ድምፅ በውኆች ላይ፥ የክብር አምላክ አንጐደጐደ፥ እግዚአብሔር በብዙ ውኆች ላይ።
፬ የእግዚአብሔር ድምፅ በኃይል ነው፤ የእግዚአብሔር ድምፅ በታላቅ ክብር ነው።
፭ የእግዚአብሔር ድምፅ ዝግባን ይሰብራል፤ እግዚአብሔር የሊባኖስን ዝግባ ይቀጠቅጣል።
፮ እንደ ጥጃ ሊባኖስን፥ አንድ ቀን እንዳለው አውሬ ልጅ ስርዮንን ያዘልላቸዋል።
፯ የእግዚአብሔር ድምፅ የእሳቱን ነበልባል ይቈርጣል።
፰ የእግዚአብሔር ድምፅ ምድረ በዳውን ያናውጣል፥ እግዚአብሔር የቃዴስን ምድረ በዳ ያናውጣል።
፱ የእግዚአብሔር ድምፅ ዋላዎችን ያጠነክራቸዋል፥ ጫካዎቹንም ይገልጣል፤ ሁሉም በመቅደሱ። ምስጋና ይላል።
፲ እግዚአብሔር የጥፋት ውኃን ሰብስቦአል፤ እግዚአብሔር ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ ይቀመጣል።
፲፩ እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኃይልን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን በሰላም ይባርካል።
+_________________________________+
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: ማዕበል, ሳውዲ አረቢያ, ሳዑዲ አረቢያ, ጂዳ | Leave a Comment »