Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • February 2020
  M T W T F S S
   12
  3456789
  10111213141516
  17181920212223
  242526272829  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

በፈረንጆቹ FEB 24 — በ124ኛ ዓመት የአድዋ ድል መታሰቢያ ኮሮና ቫይረስ ጣልያን ገባ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 24, 2020

አውሮፓዊ ወይም ካውኬዢያ ዝርያ የሌለውን የዓለማችንን ነዋሪ ሕዝብ ቁጥር ለመቀነስ ያዘጋጁት ቫይረስ በእራሳቸው ላይ እየመጣባቸው ይሆን?

ለማንም ክፉን አንመኝም፤ ነገር ግን መሆን ያለበት ይፈጸም ዘንድ ግድ ነው።

ከስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አንስቶ በተለይ በአውሮፓ እና አረቢያ በብዙ መቶ ሚሊየን ሰዎችን ሕይወት ሲቀጥፉ የነበሩት የወረርሽኝ መቅሰፍቶች የመጡት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከኢትዮጵያ (አባይ ወንዝ) ተነስተው እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁሙናል።

ለምሳሌ፦

1. የጁስቲያን ወረርሽኝ ( 527 እስከ 565 .)

የጁስቲያን ወረርሽኝ በመባል የሚታወቅ ሲሆን ከ ዓመታት ድረስ ለ 60 ዓመታት ያህል ቆይቷል።

ግብፅ እና የምሥራቅ የሮማ ግዛት (ባይዛንታይን) እንዲሁ ከከባድ በሽታ አላመለጡም ፡፡ ወረርሽኙ ከፍ ብሎ ፣ ወረርሽኙ በሰፊው ህዝብ ላይ በቆመበት ጊዜ 5000 ሰዎች በየቀኑ በከተማ ውስጥ ይሞቱ ነበር ፣ ጊዜ የሟቾች ቁጥር ወደ 10 ሺህ ሰዎች ደርሶ ነበር። ወረርሽኙ በምሥራቅ ሃገራት100 ሚሊዮን ሰዎች እና በአውሮፓ 25 ሚሊዮን ሰዎች ሕይወትን ቀጥፎ ነበር፡፡

2. ጥቁር ሞት

በጣም ዝነኛ ከሆኑት ቸነፈር ወረርሽኞች መካከል ጥቁር ሞት ተብሎ የሚጠራው አንዱ ነው። ይህ ወረርሽኝ የአየር ንብረት ቅዝቀዛ ውጤት ነበር ፡፡ ጉንፋን እና ረሃብ የመቅሰፍቱ መገለጫዎች ነበሩ፡፡ በ 1320 .ም የበሽታው የመጀመሪያ ጉዳዮች ተመዝግበዋል ፡፡ በመጀመሪያ ፣ ወረርሽኙ ቻይናንና ህንድን ካራቆተ በኋላ ፣ እ..አበ 1341 በታላቁ የሐር መንገድን ተከትሎ ወደ ዶን እና የታችኛው ቮልጋ ወንዞች ጫፍ ላይ ደረሰ ፡፡ በሽታው ወደ ካውካሰስ ተራሮች እና ወደ ክራይሚያ አካባቢ ሄዶ ከዚያም በመርከቦች መጀመሪያ በጣሊያኗ ጄኖዋ ወደብ ከዚያም ወደ መላው አውሮፓ፤ በቆስጥንጥንያ ፣ በባልካን ሃገራት፣ በቆጵሮስ እና በመካከለኛው ምስራቅ ተሰራጨ፡፡

በጥቁር ሞት ወረርሽኝ ሳቢያ የሟቾች ቁጥር 60 ሚሊዮን ህዝብ እንደሚገመት ይታወቃል፡፡

3. የስፔን ጉንፋን የሚል ስያሜ የተሰጠው ወረረሽኝ በፈረንጆቹ ከ በ 1918 እስከ1919 .ም በመላው ዓለም ወደ 50 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎችን ገድሎ ነበር።

የብዙዎቹ የእነዚህ ቸነፈር ወረርሽኞች መነሻዎች ኢትዮጵያ (አባይ ወንዝ) እንደሆነች ተመራማሪዎች ይጠቁማሉ።

እግዚአብሔር የጥንታውያኑን እስራኤላውያን ልምድ በመጨረሻ ዘመን ላይ የሚኖሩ ሕዝቦቹ እንደ ምሳሌ አድርገው እንዲጠቀሙበት ሰጥቷቸዋል፡፡ ግብፃውያኑ በባርነት ይዘዋቸው የነበሩትን እስራኤላውያን ለመልቀቅ አሻፈረኝ ባሉ ጊዜ መቅሰፍት ወረደባቸው፡፡ መቅሰፍቱ በምድረ ግብፅ ቢወርድም እስራኤላውያኑን ግን አልነካቸውም ነበር ፡፡ እናም ሳይወዱ በግድ ለቀቋቸው፡፡ በመጨረሻው ዘመን የምትገኘው ቤተ ክርስቲያን ከሚወርደው ቁጣና መቅሰፍት የተጠበቀች ናት፡፡

መቅሰፍቶቹ ወርደው ከማብቃታቸው በፊት ወደ ሰማያዊው መቅደስ የሚገባ ሰው አይኖርም።[ራዕ ፲፭፥፰]

ከእግዚአብሔርም ክብርና ከኃይሉ ጢስ በመቅደሱ ሞላበት፥ የሰባቱ መላእክት ሰባቱ መቅሰፍት እስኪፈጸሙ ድረስ አንድ እንኳ ወደ መቅደሱ ይገባ ዘንድ አልቻለም። [2፪ ተሰ ፪፥፩፡፪]

ምዕራባውያኑ የልደት በዓል በመጣ ቁጥር „Do They Know it’s Christmas?“ / “የገና በዓል እንደሆነ ያውቃሉን?“ ብለው በመዝፈን የኢትዮጵያን ክብር ዝቅ ለማድረግ ሲሞክሩ 36 አመት ሞላቸው። ታዲያ አሁን እኛም “የካቲት ፳፫ ቀን ፲፰፻፹፰ ዓ. እና ‎አድዋን ያውቃሉን?” እያልን ብንዘምር አይገባንምን?

ጣልያኖችና አውሮፓውያን በጣም ተደናግጠዋል? እስክ አሁን በጣልያን ብቻ አምስት ሰዎች መሞታቸው ታውቋል። ታሪካዊዎቹ የጣልያን ከተሞች የሙት ከተሞች መስለዋል፤ 11 ከተሞች ተዘግተዋል።

የሁዳዴ ጾም ከመግባቱ በፊት ለዘመናት ሲካሄድ የነበረው ዝነኛው የቬኒስ ከተማ ካርነቫል በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዲሠረዝ ተደርጓል፤ ባዶ መንገዶች፣ ባዶ ሱቆች ባዶ ባቡር ጣቢያዎች

______________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: