ፈረንሳዮች ለደሞዝ ጭማሪ vs. ኢትዮጵያውያን ለታገቱትና ለደሙት ዜጎች | ልዩነቱን እያየን ነው?
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 22, 2020
ፈረንሳዮቹ የወስላታውን ፕሬዚደንታቸውንና የአብዮት አህመድ ሞግዚትን ኢማኑኤል ማክሮንን መኖሪያ ያለማቋረጥ በመክበብና ከፖሊስ ጋር በጽኑ በመፋለም ለጠየቋቸው ጥያቄዎች ሁሉ መልስ እንዲያገኙና ደሞዝም እንዲጨመረላቸው መንግስቱን አስገድደውታል። የኛዎቹ ግን ከአንድ ሳምንት ያልዘለቀ የአደባባይ ጩኸት ካሰሙ በኋላ ወደ መኝታ ቤታቸው ተመልሰው ገብተዋል። በዚህ የተደፋፈረው ገዳይ አብዮት አህመድም የተለያዩ አጀንዳዎችን እየሰጠ የታገቱትን እህቶችና የተገደሉትን ኢትዮጵያውያን ጉዳይ በማስረሳት ዙፋኑ ላይ ተደላድሎ ማላገጡን ቀጥሎበታል። ግንባሩን የሚለው አንድ ጀግና የጠፋበት ልፍስፍስ ትውልድ!
Leave a Reply