Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • February 2020
    M T W T F S S
     12
    3456789
    10111213141516
    17181920212223
    242526272829  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for February 18th, 2020

የካቶሊኩ ካርዲናል ብርሃነየሱስ | መጤ ሙስሊሞች በኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ላይ ግፍና በደል እየፈጸሙ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 18, 2020

የሚገርመው፤ መንግስቱ ኃይለ ማርያም የተዋሕዶ ጳጳስን አቡነ ቴዎፍሎስን በአረመኔያዊ መልክ በሲባጎ አንቆ ገደላቸው፣ አንድ የተዋሕዶ ትውልድንም በጭካኔ ጨፈጨፈ፣ የካቶሊኩን ቄስ እና የ ፕሮቴስታንቱን ፓስተር አሠራቸው፤ የዋቄዮአላህ ተከታዮችን ግን የቀበሌና ከፍተኛዎች መሪዎች፣ አሳሪዎች፣ ገዳዮች፣ ሰሜኑንም በጦርነትና በረሃብ የሚቀጩ ባለ ሥልጣናት እንዲሆኑ አደረጋቸው፤ ከዚያም የራሴ የሚለውን ሕዝቡንም እየወለደ እንዲባዛና መላዋን ኢትዮጵያንም እንዲወርር “የመሠረተ ትምህርት ዘመቻ” ጀመረለት።

____________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

መለኮታዊ ክስተት | “ኦሮሞዎች” ፀረ-ተዋሕዶ ዘመቻቸውን ከጀመሩ 44 ዓመታት ሆኗቸዋል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 18, 2020

በመካሄድ ላይ ያለው ውጊያ በእግዚአብሔር አምላክና በዲያብሎስ ዋቄዮአላህ መካከል ነው። የዋቄዮአላህ ሕዝቦች በእግዚአብሔርና በእግዚአብሔር ሕዝቦች ላይ ተነስተዋል። ከማን ጋር ናችሁ?

የኢሬቻ ጋንግ ኦሮሞዎቹእነ ግራኝ አብዮት አህመድ፣ ፓስተር ታከለ ዑማና ኡስታዝ በላይ በኢትዮጵያ እና ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያኗ ላይ የሚያካሄዱትን የጥቃት ዘመቻ አስመልክቶ በትናንትናው የካቲት ፱ ዕለት የተጠራው የቅዱስ ሲኖዶሱ ስብሰባ ልክ በዚሁ ዕለት ከ44 ዓመታት በፊት ኦሮሞዎች አቡነ ቴዎፍሎስን ከመንበራቸው አውርደው ለሰይፍ ያመቻቹበት ዕለት መሆኑ በአጋጣሚ አይደለም።

በሀገራችን የፖለቲካ ሥርዓት ለውጥ ግርግር የሁልጊዜ ተጠቂ የሆነችው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለዘመናት መከራ በመቀበል ኖራለች። የሩቁን ትተን የቅርቡን እንኳን ብናነሳ በኢጣልያ ወረራ ወቅት ስለሀገር ሉዓላዊነት የመሰከሩና ህዝቡ ለወራሪው እንዳይገዛ ያወገዙ ሁለት ብጹዓን ኣባቶች (ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ እና ብፁዕ አቡነ ሚካኤል) በመትረየስ ጥይት ተደብደበው ተገደሉ። እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ መነኮሳትና ካህናት በየገዳማቱና አድባራቱ በግፍ ተጨፈጨፉ። በ1966ቱ አብዮት ማግስት ፓትርያርኳ በግፍ እና በአረመኔያዊ ጭካኔ በሲባጎ ታንቀው በደርግ ኮማንዶዎች ተገደሉ።

ኤዶማውያኑ ምዕራባውያን እና እስማኤላውያኑ ምስራቃውያን አፄ ቴዎድሮስን እና አፄ ዮሐንስን ከገደሉባቸው ጊዜ አንስቶ በሃገረ ኢትዮጵያ የሰፈነውና ባዕዳዊ የሆነው እርኩሱ የዋቄዮአላህ መንፈስ ነው። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ነው የኢትዮጵያና አምላኳ የጠለቀ ጥላቻ ያላቸው ኦሮሞዎች በመላው ሃገራችን ተስፋፍተው በመደበላለቅ በሰሜን ኢትዮጵያውያን ደካማ ልሂቃን ድጋፍ የቦታ መጠሪያ ስሞችን እየቀየሩ በተዋሐዶ ኢትዮጵያ ላይ እስከ ዛሬ ድረስ የዘለቀ ውድቀትን ሊያመጡ የበቁት።

ግራኝ አህመድና ጣልያኖች የጀመሩትን የፀረቤተ ክርስቲያን ዘመቻ፣ የካሃናት፣ ቀሳውስትና ምዕመናን ጭፍጨፋ በዚህ ዘመን ኦሮሞዎች በቀጥታ ተረክበው የጀመሩበት ዕለት የትናንትነው የካቲት የካቲት ፱ / 9 ፲፱፻፷፰/1968 .ም ዕለት ነው። ልክ ከስ ፵፬/44 ዓመታት በፊት። በዚህ ዓመት በኦሮሞው መንግስቱ ኃይለ ማርያም የሚመራው የኦሮሞ መንግስት ስልጣን ላይ በወጣ በሁለተኛው ዓመት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሁለተኛው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳ የሆኑትን አቡነ ቴዎፍሎስን (፲፱፻፪ ፲፱፻፷፹)ከመንበራቸው አውርዶ እስር ቤት ውስጥ ለሦስት ዓመታት እንዲማቅቁ አደረገ።

እዚያም ብዙ ሳይቆዩ ሐምሌ ፯/7 ቀን ፲፱፻፸፩ / 1971/ም፡ ኢትዮጵያ ትቅደም!” እያለ በኤዶማውያኑ ፈቃድ ስልጣን ላይ የወጣው አረመኔው መንግስቱ ኃይለ ማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሁለተኛ ፓትርያርክን አቡነ ቴዎፍሎስን በግፍ እና በአረመኔያዊ ጭካኔ በሲባጎ አንቆ ገደላቸው።

የሚከተለው ሰቆቃወ ቴዎፍሎስ በ! ትውልድመካከል … ሞትህ ደጅ አደረከሚለው ጽሑፍ የተወሰደ፦

አቡነ ቴዎፍሎስ በሌ/ኰ ዳንኤል ተይዘው ወደ እስር ቤት ሲገቡ የነበራቸውን ሁኔታና የእስረኛውን ትካዜ አቶ አበራ ጀምበሬ ተርከውልናል፡፡ ትረካቸውን ልዋስ፡

በታላቁ ቤተ መንግሥት ባለሥልጣናት ንጹሕ አየር ለማግኘት፣ በፀሐይ አካላቸውን ለማሞቅ፣ የተሳሰሩ እግሮቻቸውን ለማፍታታት በዙፋን አዳራሽ አጠገብ በሚገኝ በሽቦ በታጠረ ጠባብ ክፍል ውስጥ ይንከላወሳሉ፡፡ ቀኑ መጋቢት 3 ቀን 1968 .ም ከእኩለ ቀን በኋላ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት ታላቁ መንፈሳዊ አባት ሁለት እጆቻቸው በአንድ ላይ በሰንሰለት ታስረው እየተገፈተሩ ያለመጫሚያ በባዶ እግራቸው ሲመጡ የተመለከቱት እነዚያ እስረኞች ባሉበት ክው ብለው ቀሩ፡፡ በዚህ ወቅት ነበር አንዱ እስረኛ ልቡ ተነክቶ ‹አዲዮስ! የኢትዮጵያውያን ሰብአዊነትና መንፈሳዊነት! › ያለው፡፡ ‹…የኢትዮጵያ ሕዝብ ግብረ ገብነትና መንፈሳዊነት በእነዚህ ጋጠ ወጦች አይለካም› አለ ሌላውበድርጊቱ መብገኑን ሁኔታው እየነገረበት፡፡ …ያደፈ ሽሮአማ ቀሚስ እንደለበሱ ከቀኝም፣ ከግራም፣ ከኋላም ሳንጃ የተሰካበት ጠብመንጃ ተደግኖባቸው ወደዚያች የፖለቲካ እስረኞች መቀየጃ ቅጥር ሲገቡ መንፈሳዊው አባት ‹የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው› በማለት የሚጸልዩ እንጂ የተበሳጩና የተሸበሩ አይመስሉም ነበር፡፡ እስረኛው ከድንጋጤው ገና ሳይላቀቅ፣ ምን እንደሚልና እንደሚናገር አሰላስሎ ሳይጨርስ፣ ከቆመበት ሳይላወስ ነበር ከአንድ ትንሽ ክፍል ውስጥ አስገብተው የቆለፉባቸውና እግራቸውን በእግረ ሙቅ፣ እጃቸውን በሰንሰለት ጠፍረው ካልጋ ጋር ያሠሯቸው፡፡ ‹ይሕን አዚመኛ ቄስ ተጠንቅቃችሁ ጠብቁ› በማለት ለወታደሮች ጥብቅ ትእዛዝ ሰጥቶ የዘቡ አዛዥ ከአጥሩ ወጥቶ ሄደ“(የአቶ አበራ ጀምበሬ የእስር ቤቱ አበሳበዜና ጳጳሳት መጽሐፍ እንደተጠቀሰው፡ (.58-59)

ፓትርያርኩ በዚህ መልኩ በጾምና በቀኖና ተወስነው ለ3 ዓመታት በእስራት ከቆዩ በኋላ ሐምሌ 7 ቀን 1971 .ም ከሌሎች 33 ታሳሪዎች ጋር በሞት መልእክተኞች ተጠሩ፡፡ ተሰለፉ፡፡ በተራቸው ገቡ፡፡ ወደ ጨለማው ቤት ውስጥ ገቡ፡፡ የተለያዩ ኮሪደሮች ባሉት የጨለማ ቤት ውስጥ ጥግ ላይ ያለው ሰው ‹ና› አላቸው፡፡ ወደሱ አተኩረው ሲራመዱ በጨለማው ኮሪደር ለግድያ ካሸመቁ ሰልጣኝ ኮማንዶዎች አንዱ ሳያስቡት በሲባጎ አነቃቸው፡፡ ኮማንዶው ሲባጎውን በሁለት እጆቹ ጠምጥሞ አጥብቆ በአንገታቸው ላይ ካጠለቀ በኋላ ገመዱን በመሸረብና በማሳጠር በስተመጨረሻ ፓትርያርኩን በገመዱ እንደታነቁ የእንግላሊት ጀርባው ላይ አውጥቶ በአንገታቸው የገባውን ገመድ በእጁ እየጠቀለለ በማሳጠርና በማጥበቅ ትንፋሻውን ቋጨ፡፡ አስከሬናቸውን ጎትቶ ከሌሎች እስረኞች ጋር ሸራ አለበሰው፡፡ ማታ ሦስት ሰዓት ኖራ ተነስንሶባቸው ከ33ቱ እስረኞች ጋር በጅምላ በአንድ ጉድጓድ ተቀበሩ፡፡ ከፓትርያርኩ ጋር አብረው ከተቀበሩት ሰዎች አንዱ የመኢሶኑ የአመራር አባል ኃይሌ ፊዳ ነበር፡፡ አብዮተኛው ባለብሩህ ጭንቅላት ወጣትና ባለራዕይው አረጋዊ ፓትርያርክ በአንድ ጉድጓድ ተጣሉ፡፡ (ርዕዮተ ዓለሙ ዛሬ ባያማልለንም! ) እሱ ከአውሮፓ ለአዲስ ሥርዓት ለውጥ መጥቶ እሳቸው ከነበሩበት መንበር በግፍ ተገፍተው ባንድ ጉድጓድ ተቀበሩ፡፡

ታዋቂው ገጣሚና መፍቀሬመኢሶን የሚባለው ዮሐንስ አድማሱ ዕንባሽበሚለው ግጥሙ፡

ዘመን ቢያርቃችሁ፣

ሥፍራ ቢለያችሁ፣

ዕንባ አገናኛችሁ፡፡

ያለው በዚያ ዘመን ልጆቿ ከቤተ ክህነትና ከቤተ መንግሥት እየተነዱ በገዳዮቻቸው ለተፈጁባት ኢትዮጵያና ለግፉዓን ልጆቿ ሙሾ ሆኖ ይሰማናል!

አቡነ ቴዎፍሎስ 2/ ፪ኛው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ናቸው፡፡ ሀገር ውስጥ በራሳችን አባቶች በመሾም ግን የመጀመሪያ ናቸው፡፡ የጀመሩት ነገር የመብዛቱን ያህል ሰቆቃቸውም በብዙ መልኩ የመጀመሪያ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ምድር በራሳቸው ወንድሞች ተላልፈው ተሰጥተው በገዛ ወንድሞቻቸው ታንቀው የተገደሉ ቀዳሚ ፓትርያርክ ናቸው፡፡

ኦሮሞው መንግስቱ ኃይለ ማርያም ኢትዮጵያ ትቅደም!” ብሎ ብዙ ወጣቶችን በማታለል የተዋሕዶ ልጆችን ጨፈጨፈ፤ ኦሮሞው አብዮት አህመድም ኢትዮጵያ ሱሴ!” እያለ የዘመኑን ትውልድ በማምታታት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለመከፋፈልና ለማፍረስ ቆርጦ ተነስቷል፣ ልጆቿን በማሰር፣ በማረድና በመረሸንም ቀዳማዊ ግራኝ አህመድን፣ ፋሺስቶች ሙሶሊኒን እና መንግስቱ ኃይለ ማርያምን የሚያስንቅ እርኩስ ተግባር በመፈጸም ላይ ይገኛል።

የአባታችን ረድኤት በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን፡፡ አሜን!!!

___________________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ገዳዮቹ አህመድና ዑማ የወንድሞቻችንን ደም ያፈሰሰብትን ቦታ ለመናፍቅ ዮናታን ሊሰጡት ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 18, 2020

ልክ የሃገራችን እና የአምላካችን ጠላቶች ለሆኑት ለምዕራባውያኑ ኤዶማውያን እና ምስራቃውያኑ እስማኤላውያን የሃገራችንን በር ብርግድ አድርገው በመክፈት እርስታችንን አስላፈው ለመስጠት በመጣደፍ ላይ እንዳሉት ሁሉ አባቶችና ወንድሞች ደማቸውን ያፈሰሱበትን ቦታም ለክርስቶስ ጠላቶች ሊሸልሟቸው በመድፈር ላይ ናቸው። ይህች ቁራሽ ቦታ የኢትዮጵያ መስተዋት ናት። ግን አቤት ድፍረት! አቤት ንቀት! አቤት ክህደት! አቤት እብደት! እነዚህ ወንበዴዎች በአፋጣኝ መጠረግ አለባቸው!

_______________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: