Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • February 2020
    M T W T F S S
     12
    3456789
    10111213141516
    17181920212223
    242526272829  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

ብርሃናዊ የማንቂያ ደወል ዘመን | አህመድ፣ ዑማ እና ዲያብሎስ አባታቸው በጧፉ ተቃጠሉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 15, 2020

[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲፰፥፳፯፡፳፰]

አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህና፥ የትዕቢተኞችን ዓይን ግን ታዋርዳለህ። አንተ መብራቴን ታበራለህና፤ እግዚአብሔር አምላኬ ጨለማዬን ያበራል።

ጨለማን ተገን አድርጎ ምዕመናን በቤተክርስቲያን የሚገድለው የግራኝ አህመድ ሰራዊት ምን ይውጠው?

በእውነት ዕጹብ ድንቅ ነው! ይህ ቀላል ነገር አይደለም! እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!

በጤናማው ዓለም ይሄንን አስደናቂ ክስተት የዓለም ሚዲያዎች ሁሉ ሊያሳዩት በተገባ ነበር። ግን እነርሱም የእኛን ፀጋና ውበት ማየት ሰለማይሹና በጎውንም ነገር ስለማይመኙልን ካሜራዎቻቸውን መደበቅ ይመርጣሉ። ኢትዮጵያንና ቤተ ክርስቲያኗን የሚያጠለሽ ነገር ሲያገኙ ግን የሚቀድማቸው ሰው የለም። እናስታውሳለን፤ በጎንደር የጥምቀት በዓል ምዕመናን በአሳዛኝ ሁኔታ ሲሞቱ፤ ወኪላቱ ዜናውን ወዲያው ነበር በመላው ዓለም እየተቀባበሉ እንዲሰራጩ የተደረጉት። ለነገሩማ አዲስ አበባ ብዙ የውጭ ሰዎች አሉ፤ ኤማባሲዎቹና ዓለም አቀፍ ተቋማቱ በከተማችን ስለሚካሄዱት ነገሮች አንድም የሚያመልጣቸው ነገር የለም፤ ሆኖም ትንሽም እንኳን ቢሆን የሰብዓዊነት፣ ሃቀኝነትና ሚዛናዊነት መንፈስ ቢኖራቸው ኖሮ ይህ የማንቂያ ደወል ለምን እየተደወለ እንደሆነ ተከታትለው ለዓለም የማሳወቅ ኃላፊነት ነበረባቸው። ግን ከንቱ፣ ውዳቂዎችና የሀሰት ቋሚ ሸማቾቿ ናቸውና ወደ ብርሃናማው መንገድ መውጣቱን ይፈራሉ። እንግዲህ አሁን ሌላ ምን አማራጭ አላቸው? ከእነ አብዮት አህመድ ጋር አብረው በተኙበት አልጋ ላይ ቅጥል ይበሉ እንጂ እኛ ቴሌቪዥኑን አጥፍተን ጧፋችንን ከዳር እስከዳር እንዲህ ማቀጣጠሉን እንቀጥልበታለን።

__________________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: