Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • February 2020
    M T W T F S S
     12
    3456789
    10111213141516
    17181920212223
    242526272829  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

እንግሊዛውያን | አይሁድ እና ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ይምጡ፤ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ግን አይምጡ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 12, 2020

ጀግናው ክርስቲያን ቦብ ከአንድ እንግሊዛዊ ብሔርተኛ ጋር በለንደኑ ሃይድ ፓርክ

የቦብ ሃሳብ በጥቂቱ፦

አንድ ሕዝብ አኗኗሩን በክርስቶስ ላይ ካልመሠረተና እንደ ክርስቲያን መኖር ያለበትን ሕይወት ካልኖረ በውስጡ ባዶ ስለሚሆን ከምድር ተጠርጎ ቢጠፋ ብዙም ሊያሳስብን አይገባም።

ብሪታናውያን ከክርስቲያናዊ ህይወት በመራቃቸው ከዚህ ምድር ተጠርገው ቢሄዱ እንባ አላነባላቸውም፤

መንፈሳዊ ሞት ስጋዊ ሞትንም ያስከትላልና ነው።

የሀገር መሰረቱ ቤተሰብ ነው። የትውልድ ምሰሶው ቤተሰብ ነው። ይህ የማህበረሰብ መሰረት ጠንካራ ሲሆን ጠንካራ ሀገር መፍጠር ይቻላል። ይህ የማህበረሰብ መሰረት ሲናጋ የሀገር ህልውና አደጋ ውስጥ ይገባል።

የክርስቲያናዊ ቤተሰብ የቤት ራስ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ክርስቶስ የሌለበት ሕይወት ባዶ ነው፡፡ ያለ ክርስቶስ አንዳች ልናደርግ አንችልም፡፡ ሕይወት ያለ ክርስቶስ ሞት ነው፡፡ ሠላምና እውነተኛ መንገድም እርሱ ብቻ ነው፡፡ (ኤፌ.፮፥፲)(ዮሐ.፲፬፥፮)፡፡ ያለ ክርስቶስ ክርስትና የለም፡፡ እርሱ የሌለበት ትዳር፣ ቤትና ኑሮ ትርጉም የለውም፡፡ የመልካም ቤተሰባዊ ሕይወት መሰረቱ ክርስቶስ ነው፡፡ ክርስቶስን መሰረት ያላደረገ ትዳርና ጎጆ ውጤቱ ጭቅጭቅ፣ ሁከት፣ስቃይ፣ መለያየትና አድመኝነት ነው፡፡ ክርስቶስን ራስ ያላደረ ቤተሰባዊ ሕይወት ጅራት (ኋለኛ) ነው የሚሆነው፡፡ ክርስቶስን ራስ ያደረገ ቤተሰባዊ ሕይወት የመፈቃቀር፣ የደስታ፣ የሠላም የተስፋና የእምነት ምንጭ ነው፡፡

እንግሊዞች ክርስቲያናዊ ማንነታቸውን ክደዋል፣ ቤተሰባዊ አኗኗራቸውን እየተውና ልጆችንም ከመውልድ እየተቆጠቡ ስለሆነ እንደ ሕዝብ እየሞቱ ቢያልቁ አያስገርመኝም።

ክርስትና የሞራል መምሪያ እምነት ብቻ አየደለም ለመንፈሳዊ ሕይወት ትልቅ ቦታ ያለው ሃይማኖት እንጂ።

ዘረኞችና የዘውግ ብሔርተኞች ግን የክርስትና ጠላቶች ስለሆኑ መንፈሳዊውን ክርስትናን ለመሸርሸር ሲሉ ክርስትናን የባሕል፣ የወግና የበዓላት ባሕርይ ብቻ ይዞ እንዲጓዝ ይሻሉ ፥ ይህ ክርስትና አይደለም።

የዘውግ ብሔርተኞች ዋንኛው ችግራቸው በጥላቻ የተሞሉ መሆናቸው ነው። አንድ ብሔር በራሱ ብቻ መኩራራት የሚጀመር ከሆነ ሌሎች ብሔሮችን በቀላሉ ወደ መጥላት ያመራል፤ ይህም ከክርስትና አስተምህሮ ጋር እንዲጻረር ያደርገዋል። ክርስትና ሁሉንም ብሔሮች የሚያቅፍ በክርስቶስ ሁሉም አንድ የሚሆኑበት እምነት ነውና።

ብሔርተኛው፦

የዘር ጥላቻ ጉዳይ አይደለም፤ እኔ ለምሳሌ ሶማሌዎችን አልወዳቸውም፤ ግን ይህ ዘረኛ በመሆኔ ሳይሆን በእነርሱ ዘንድ የማየው ነገር ከእኔ አኗኗር ጋር ስለማይጣጣም ነው

ቦብ፦ እሺ፡ ኢትዮጵያውያንስ?

ብሔርተኛው፦

ከአይሁድ እና ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ጋር ምንም ችግር የለኝም እዚህ መጥተው ቢሰፍሩ አልቃወምም፤ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ግን ወደ ብሪታኒያ መጥተው እንዲሠፍሩ አልሻም።

ቦብ፦

ስለዚህ ያንተ ችግር/ ጉዳይ ብሔርተኮር ሳይሆን እምነትና ሃይማኖትተኮር ነው ማለት ነው።

አዎ! ስለዚህ ችግሩ፤ አንዳንድ ብሔሮች አብረው መኖር አይችሉም ሳይሆን ፥ አንዳንድ እምነቶች ጎን ለጎን አብረው መኖር አይችሉም ፥ በዚህ እኔም እስማማለሁ።

___________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: