Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • February 2020
    M T W T F S S
     12
    3456789
    10111213141516
    17181920212223
    242526272829  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for February 12th, 2020

በደቡብ ኢትዮጵያ እሳት ከሰማይ ዘነበ | ነብያት ሙሴና ዮናስ አስተምረውናል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 12, 2020

ዘነበ ለዘንባራተቤራ

ይህ አካባቢ የተጠለፉት እህቶቻችን አሳዛኝ ጉዳይ የተፈጸመበት አካባቢ ነው፤ ለጅማ ቅርብ ነው፤ አጋቻቸው አብዮት አህመድ “ሰበርናቸው/ የተሰረቁት ሃያ አበቦች (ልጃገርድ ተማሪዎችን በማለት እንደለመደው መሳለቁ ይሆናል)” ትናንታና ወደ ጂሃድ ጅማ በማምራት የድል አቀባበል እንዲደረግለት አዘጋጅቶ ነበር። ነገ ደግሞ አረብ ሞግዚቶቹ ፊት ለመምበርከክ ወደ ጂሃድ አረቢያ ያመራል። በደቡብ የወረደው እሳት በሄደበት ይከተለው!

የእግዚአብሔርም እሳት በመካከላቸው ስለነደደች የዚያን ስፍራ ስም “ተቤራ” ብሎ ጠራው”

[ኦሪት ዘኍልቍ ምዕራፍ ፲፩,፥፩፡፫]

ሕዝቡም ክፉ ሆነው በእግዚአብሔር ላይ አጕረመረሙ፤ እግዚአብሔርም ሰምቶ ተቈጣ፤ የእግዚአብሔርም እሳት በመካከላቸው ነደደች፥ የሰፈሩንም ዳር በላች። ሕዝቡም ወደ ሙሴ ጮኹ፤ ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ እሳቲቱም ጠፋች። የእግዚአብሔርም እሳት በመካከላቸው ስለነደደች የዚያን ስፍራ ስም ተቤራ ብሎ ጠራው።”

በደቡብ ኢትዮጵያ በከምባታ ጠምባሮ ዞን ዱሬ፣ ሲገዞ፣ “ለዘንባራ” እና ሆዶ ቀበሌዎች ዓርብ ለቅዳሜ አጥቢያ ከሰማይ ወረደ በተባለ እሳት ሰላሳ በላይ የሳር ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን ስድስት ከብቶች እና የጢርፍ ክምርም የጉዳቱ ሰለባ ሆኗል።

የእሳቱ መንስዔ በግልጽ ባይታወቅም የአካባቢው ኅብረተሰብ በተመሳሳይ ሰዓት ከሰማይ ወርዶ ጉዳት እንዳደረስ እና ተፍጥሯዊ ነው ብለዋል።

______________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

እንግሊዛውያን | አይሁድ እና ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ይምጡ፤ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ግን አይምጡ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 12, 2020

ጀግናው ክርስቲያን ቦብ ከአንድ እንግሊዛዊ ብሔርተኛ ጋር በለንደኑ ሃይድ ፓርክ

የቦብ ሃሳብ በጥቂቱ፦

አንድ ሕዝብ አኗኗሩን በክርስቶስ ላይ ካልመሠረተና እንደ ክርስቲያን መኖር ያለበትን ሕይወት ካልኖረ በውስጡ ባዶ ስለሚሆን ከምድር ተጠርጎ ቢጠፋ ብዙም ሊያሳስብን አይገባም።

ብሪታናውያን ከክርስቲያናዊ ህይወት በመራቃቸው ከዚህ ምድር ተጠርገው ቢሄዱ እንባ አላነባላቸውም፤

መንፈሳዊ ሞት ስጋዊ ሞትንም ያስከትላልና ነው።

የሀገር መሰረቱ ቤተሰብ ነው። የትውልድ ምሰሶው ቤተሰብ ነው። ይህ የማህበረሰብ መሰረት ጠንካራ ሲሆን ጠንካራ ሀገር መፍጠር ይቻላል። ይህ የማህበረሰብ መሰረት ሲናጋ የሀገር ህልውና አደጋ ውስጥ ይገባል።

የክርስቲያናዊ ቤተሰብ የቤት ራስ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ክርስቶስ የሌለበት ሕይወት ባዶ ነው፡፡ ያለ ክርስቶስ አንዳች ልናደርግ አንችልም፡፡ ሕይወት ያለ ክርስቶስ ሞት ነው፡፡ ሠላምና እውነተኛ መንገድም እርሱ ብቻ ነው፡፡ (ኤፌ.፮፥፲)(ዮሐ.፲፬፥፮)፡፡ ያለ ክርስቶስ ክርስትና የለም፡፡ እርሱ የሌለበት ትዳር፣ ቤትና ኑሮ ትርጉም የለውም፡፡ የመልካም ቤተሰባዊ ሕይወት መሰረቱ ክርስቶስ ነው፡፡ ክርስቶስን መሰረት ያላደረገ ትዳርና ጎጆ ውጤቱ ጭቅጭቅ፣ ሁከት፣ስቃይ፣ መለያየትና አድመኝነት ነው፡፡ ክርስቶስን ራስ ያላደረ ቤተሰባዊ ሕይወት ጅራት (ኋለኛ) ነው የሚሆነው፡፡ ክርስቶስን ራስ ያደረገ ቤተሰባዊ ሕይወት የመፈቃቀር፣ የደስታ፣ የሠላም የተስፋና የእምነት ምንጭ ነው፡፡

እንግሊዞች ክርስቲያናዊ ማንነታቸውን ክደዋል፣ ቤተሰባዊ አኗኗራቸውን እየተውና ልጆችንም ከመውልድ እየተቆጠቡ ስለሆነ እንደ ሕዝብ እየሞቱ ቢያልቁ አያስገርመኝም።

ክርስትና የሞራል መምሪያ እምነት ብቻ አየደለም ለመንፈሳዊ ሕይወት ትልቅ ቦታ ያለው ሃይማኖት እንጂ።

ዘረኞችና የዘውግ ብሔርተኞች ግን የክርስትና ጠላቶች ስለሆኑ መንፈሳዊውን ክርስትናን ለመሸርሸር ሲሉ ክርስትናን የባሕል፣ የወግና የበዓላት ባሕርይ ብቻ ይዞ እንዲጓዝ ይሻሉ ፥ ይህ ክርስትና አይደለም።

የዘውግ ብሔርተኞች ዋንኛው ችግራቸው በጥላቻ የተሞሉ መሆናቸው ነው። አንድ ብሔር በራሱ ብቻ መኩራራት የሚጀመር ከሆነ ሌሎች ብሔሮችን በቀላሉ ወደ መጥላት ያመራል፤ ይህም ከክርስትና አስተምህሮ ጋር እንዲጻረር ያደርገዋል። ክርስትና ሁሉንም ብሔሮች የሚያቅፍ በክርስቶስ ሁሉም አንድ የሚሆኑበት እምነት ነውና።

ብሔርተኛው፦

የዘር ጥላቻ ጉዳይ አይደለም፤ እኔ ለምሳሌ ሶማሌዎችን አልወዳቸውም፤ ግን ይህ ዘረኛ በመሆኔ ሳይሆን በእነርሱ ዘንድ የማየው ነገር ከእኔ አኗኗር ጋር ስለማይጣጣም ነው

ቦብ፦ እሺ፡ ኢትዮጵያውያንስ?

ብሔርተኛው፦

ከአይሁድ እና ክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ጋር ምንም ችግር የለኝም እዚህ መጥተው ቢሰፍሩ አልቃወምም፤ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ግን ወደ ብሪታኒያ መጥተው እንዲሠፍሩ አልሻም።

ቦብ፦

ስለዚህ ያንተ ችግር/ ጉዳይ ብሔርተኮር ሳይሆን እምነትና ሃይማኖትተኮር ነው ማለት ነው።

አዎ! ስለዚህ ችግሩ፤ አንዳንድ ብሔሮች አብረው መኖር አይችሉም ሳይሆን ፥ አንዳንድ እምነቶች ጎን ለጎን አብረው መኖር አይችሉም ፥ በዚህ እኔም እስማማለሁ።

___________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ነብዩ ዮናስ አይደለሁም ሆኖም ይህ ትናንት የታየኝ ሌላ አስገራሚ ክስተት ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 12, 2020

ጾመ ነነዌ (የኢትዮጵያ ጾም) ዘመነ ዮሐንስ፤ ዛሬ ረቡዕ ፬ – ፪ሺ፲፪ ዓ.ም ነው፤ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ነው።

ነቢዩ ዮናስ ነነዌ መሬት ላይ እንደደረሰ ባወቀ ጊዜ ከእግዚአብሔር መሸሽ አለመቻሉን ተረዳ። የነነዌ ሰዎችንም ንስሐ ግቡ እያለ መስበክ ማስተማር ጀመረ፡፡ የነነዌ ሰዎችን የዮናስን ትምህርት ሰምተው ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር አምላክ ይቅር ብሎ ከጥፋት አድኗቸዋል፡፡ነቢዩ ዮናስም ሐሰተኛ እንዳይባል እሳቱ እንደ ደመና ሆኖ ከላይ ታይቷል።

ዮናስ ማለት የስሙ ትርጉም ርግብ ማለት ነው።

በጾማችን እግዚእብሔር አምላክ መዓቱን በምሕረቱ ቁጣውን በትዕግስቱ መልሶ በኃጢአት ለጠፋው ዓለም ይቅርታውን ይላክልን፡፡

___________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

ትንኮሳ በመምህር ምህረተአብ ላይ | አይደለም መፈረም ሞት ተዘጋጅቷል ቢባል ለመታረድ ዝግጁ ነን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 12, 2020

ቦሌ ቅዱስ ሚካኤል ፥ ማክሰኞ የካቲት ፫ / ፪ሺ፲፪ ዓ./ በዓታ

አሁን ሁላችንም እንዘጋጅ፣ ሁላችንም እንቁረጥ፣ እንጨክን! እኔ ብታሠር ወንጌል አይታሠር፣ ካህናቱ ሁሉ ቢገደሉ ክህነቱ አይሞት፣ ቤተ ክርስቲያን አትጠፋ.…

እምንሞትም እኛ ፥ እምንበዛም እኛ ፥ እሚገሉም እነሱ ፥ እሚያለቅሱም እነሱ ፥ እሚገፉም እነሱ ፥ እሚወድቁም እነሱ ፥ እሚነቅሉም እነሱ ፥ እሚነቀሉም እነሱ ፤ ግን ማድረግ ያለብንን ድርሻችንን ማድረግ አለብን።

____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: