የመንግስት ሠራዊት ወደ ቤተክርስቲያን ሄዶ በክርስቲያኖች ላይ ለሦስት ሰዓት ያህል ተኩስ እየከፈተ ንጹሐንን ለመግደል የተሠማራባት አንዲትም የዓለማችን ሃገር የለችም፤ ያውም አፍሪቃውያን መሪዎች እየጎረፉባት ባለችው የአፍሪቃ ዋና ከተማ። ይህ ወንጀል፤ ከጠፉት እህቶቻችን ጉዳይ ጎን እንዲሁ በቀላሉ በዝምታ መታለፍ የለበትም፤ በጭራሽ!በሌላው ዓለም እንደነዚህ ለመሳሰሉት ወንጀለኛ መሪዎች የሞት ፍርድ ይሰጣቸው ነበር። ይህን ያህል ወንጀል ያልሰራው የቀድሞው የፓኪስታን ፕሬዚደንት ሙሻራፍ እንኳን የሞት ፍርድ ተሰጥቶታል። በፕሬዚደንት ትራምፕ ላይም ለማይረባ ነገር ስንት ድራማ እንደተሠራ እንደሆነ እያየን ነው። አብዮት አህመድ፣ ሽመልስ አብዲሳ፣ ታከለ ኡማና ለማ መገርሳ በፍጥነት እስካልተጠረጉ ድረስ የሕዝቡ ሰቆቃ ይቀጥላል።