ቅድስት ሥላሴ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያውያንን ይባርኩ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 16, 2020
እንኳን ለአግዓዚተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን። የአብርሃሙ ሥላሴ ሀገራችንን ኢትዮጵያን ይጠብቅልን። ሕዝባችንንም በሰላም በፍቅር በአንድነት ያኑርልን።
ወደ መጨረሻ ላይ ያለውን መልዕክት እናዳምጥና እራሳችንን እንጠይቅ፤ “እንደው በዚህች ዓለም ላይ እንደ ኢትዮጵያ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ወደ ቤተክርስቲያን አዘውትሮ የሚሄድ፣ በጾምና በጸሎት የሚተገባ ሕዝብ ይኖራልን? እኔ መመስከር እችላለሁ፤ የለም! የትም ሃገር የለም። ሃጢአተኞች ሁላችንም ሃጢአተኞች ነን፤ ነገር ግን ቤተክርስቲያን እየተቃጠለ ያለው እኛ ከዓለም ሁሉ የከፋ ሃጢአት ሰርተን ሳይሆን ክርስቲያን ወገናችንን እና ቤተክርስቲያናቱን ለመከላከል ዝግጁ ባለመሆናቻን፣ የእኛና የአምላካችን ጠላት ከሆኑት አህዛብ ጋር በመደባለቃችን፣ የሃገር ጠላት ከሆነው መንግስት ጋር በመደመራችን ብሎም እንደ ቀደሙት አባቶቻችን መንግስትን በቁጣ ለመገሰጽና ለማስጠንቀቅ ባለመድፈራችንና በራድ ወይ ትኩስ ስላልሆንን ነው። ስለዚህ መንግስትን ለመቃወም “ሰልፍ አትውጡ፡ እኛ እንደራደራለን!” ቅብርጥሴ የሚለው መልዕክት የትም አያደርሰንም። እንዲያውም የተዋሕዶ አርበኞች በቁጣ ወደ አራት ኪሎ ቤተመንግስት አምርተው ባለሥልጣናቱ ሁሉ እንዲወገዱ መጮኽና አጥሩን መነቅነቅ ይኖርባቸዋል። ለሁሉም ጊዜ አለው፤
“ከወዳጆችህ ጋር ብቻ ሳይሆን ከጠላቶችህም ጋር እንኳ ሳይቀር በሰላም ኑር፤ ነገር ግን እንዲህ የምልህ ካንተ ከግል ጠላቶችህ ጋር እንጂ ከእግዚአብሔርና ከቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ጋር አይደለም፡፡”አንድ ገዳማዊ አባት
“ሰውን ከእግዚአብሔር ከሚለየው አጉል ሰላም ይልቅ ከእግዚአብሔር የማይለየው ጦርነት ይሻላል፤ ስሜታዊ ከሆነና ለቤተ ክርስቲያን ዘለቄታዊ ጉዳት ከሚኖረው ስምምነትና አንድነት ይልቅ ስለ ሐይማኖት መጠበቅ ዘለቄታዊ ጠቀሜታ የሚኖረውና ለዚህ ሲባል የሚሆን አለመስማማት ይሻላል፡፡” ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ
በዚህ የጥምቀት በዓል ከአባቶች የምጠብቀው መልዕክት፦
“ሴት ልጆቼ በደምቢዶሎ ጫካ ውስጥ የጥምቀት በዓልን እንዲያሳልፉ አልሻም፤ ስለዚህ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ በቃህ፡ ስልጣኑን አስረክብና በሥላሴ ስም ተጠመቅ!”
የሚለውን መልዕክት ነው።
እስኪ እናስበው፤ አቡነ ማትያስ ይህን ቢናገሩ፤ ምንም ጥርጥር የለኝም ብዙ እንቅስቃሴ ሊታይ ይችል ነበር።
የቤተክርስቲያን አገልጋዮች፡ በቃን! “ስሜታዊ አትሁኑ!” እያላችሁ ሰውን አታስተኙት፤ ወኔውን አትንጠቁት! እንዲያውም “ምርጫ” የተባለው ነገር የሚካሄድ ከሆነ በመጭዎቹ ሳምንታት ምእመናኑን ለእነ አብዮት አህመድ፣ ለእነ ብርሃኑና ስብሐት ነጋ፣ እንዲሁም ለሌሎቹ አቋም–የለሽ ልክስክስ ፓርቲዎች በጭራሽ ድምጽ እንዳይሰጡ ማስጠንቀቅ፤ በተቃራኒው ደግሞ ለእስክንድር ነጋ ድጋፋቸውን እንዲሰጡ ግልጽ የሆነ ቅስቀሳ ማካሄድ አለባቸው።
ሜዲያው ሁሉ በኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ላይ አሉታዊ በሆነ መልክ 24 ሰዓት ቅስቀሳ በሚያደርጉባት ሃገራችን ለሕዝበ ክርስቲያኑ በጣም አመች የሆነው የቅስቀሳ እና የትምህርት መድረክ በቤተክርስቲያን ነው የሚገኘው።
Leave a Reply