Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • January 2020
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

የኦሮሞ ክርስቲያኖች አስተውሉ ክርስትና ከብሔር በላይ ነውና በክርስቶስ ደም ጽድቅን ላገኛችሁባት ቤተክርስቲያን አለሁልሽ በሉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 8, 2020

እስላሞች ማየት አንፈልግምና ይነሳልን በማለት ብዙ ጊዜ በኃይልም፣ በሕግም ብለው ያቃታቸውን አሁን ከላይ እስከታች የሚገኘውን የሥልጣን እርከን በመቆጣጠር በፈጠሩት ጫና ምክንያት በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትእዛዝ በአርሲ ነገሌ ከተማ የሚገኘውና በባሕረ ጥምቀቱና በመስቀል አደባባዩ ላይ ለዘመናት ተተክሎ ይኖር የነበረውን መስቀለ ክርስቶስ ባለፈው እሁድ በዚህ መልኩ እንዲነሣ ተደርጓል።

በአርሲ ነገሌ ለረጅም ጊዜ የጥምቀት ቦታ ላይ የተተከለው መስቀል እንዲነሳ ተወሰነ

አስቸኳይ መልዕክት †

በመ/ር ታሪኩ አበራ

**ለቅዱስ ሲኖዶስና ለዶ/ር ዓብይ መንግሥት**

**በኦሮሚያ ክልል በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ የሚደረገው ጥቃት በአስቸኳይ ይቁም!!!

**መስቀሉ አይነቀልም፣የጥምቀት ቦታችንም አይደፍርም!!! **

**የኦሮሞ ክርስቲያኖች አስተውሉ ክርስትና ከብሔር በላይ ነውና በክርስቶስ ደም ጽድቅን ላገኛችሁባት ቤተክርስቲያን አለሁልሽ በሉ !!**

**በአርሲ ነጌሌ ከ40 ዓመት በላይ ኦርቶዶክሳውያን በዓለ ጥምቀት የሚያከብሩበትን ቦታ ፀረ ክርስቲያን አቋም ያላቸው የመንግሥት ባለስልጣን ተብዬዎች ለማፍረስ የማስፈራሪያ ትህዛዝ እያስተላለፋ ነውና በአስቸኳይ ይቁም!!**

**በደብረ ዘይት ከተማ የመስቀል ደመራ እንዳይበራ ያደረጉት የሙስሊምና የዋቄፈና እምነት ተከታይ ባለ ሥልጣናት አሁን ደግሞ በጥምቀተ ባህር ላይ ተነስተዋልና ሕዝበ ክርስቲያን ዝም ብለህ አትመልከት።ነውረኛና ኃላፊነት የጎደላቸው ባለ ሥልጣናትን ፊትለፊት ወጥተህ አርፈህ ተቀመጥ ልትል ይገባል!! **

**የሲኖዶስ አባላት ጳጳሳት ሆይ የቤተክርስቲያን ልጆችን በፍቅር አቅርቦ ከማወያየት ይልቅ ለማውገዝ ትፈጥናላቹ ቤተክርስቲያን ስትቃጠልና ስትደፈር ግን ታንቀላፋላቹ እባካችሁን ንቁ!!*

*** ENOUGH IS ENOUGH !! ***

በሃገራችን የመጣውን የመንግሥት ለውጥ ተከትሎ በተለያዩ ክልሎች ፀረ ሠላም የሆኑ የጥፋት ኃይሎች ለዘመናት የተደበቀ የጥላቻ አጀንዳቸውን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ በመክፈት በተለያዩ ጊዜያት እጅግ አስነዋሪና አሳፋሪ ጥፋቶችን በቤተክርስቲያን ላይ እና በሕዝበ ክርስቲያን ላይ ሲፈጽሙ ቆይተዋል።

በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ከ 18 በላይ የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናትን አቃጥለዋል፣ንብረት ዘርፈዋል፣ካህናትና ምዕመናን እጅግ ዘግናኝ በሆነ ጭካኔ ገድለዋል።ይህ ሁሉ ጥቃትና ወንጀል በቤተክርስቲያን ላይ ሲፈጸም መንግስትም የወሰደው አመርቂ እርምጃ የለም። ይህንን የመንግሥት ቸልተኝነትና የምንአገባኝ ስሜት ተመልክተው ፀረ ኦርቶዶክስ አቋም ያላቸው የጥፋት ኃይሎች አሁንም በቤተክርስቲያኒቱ ላይ ከፍተኛ ጥቃት እያደረሱ ይገኛሉ።ቀድሞ በየጫካው እየተደበቁ በሥውር ጥቃታቸውን ይፈጽሙ ነበር፤ አሁን ግን የእነርሱን አጀንዳ እንዲያስፈጽሙ ቃል ባስገቧቸውና የሥልጣን ወንበር እንዲይዙ ባደረጓቸው የኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናት ተብዬ ዎች በግልጽ ቤተክርስቲያን ላይ የጥፋት አዋጃቸውን አስተጋብተዋል።እነኚህ ኃላፊነት የጎደላቸው ግልብ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት ተከባብሮ በሰላም የኖረውን ሕዝብ እርስበርስ ከማጨራረሳቸውና ደም ከማፋሰሳቸው በፊት የፌዴራል መንግሥት በአስቸኳይ ጣልቃ ገብቶ ለችግሩ እልባት ይሰጥ ዘንድ በጥብቅ እናሳስባለን።

በአርሲ ነገሌ በጣም በርካታ ሕዝበ ክርስቲያን ያሉ ሲሆን ኦርቶዶክሳውያኑ ከ40 ዓመታት በላይ በዓለ ጥምቀትን የሚያከብሩበትን የቦታ ይዞታ ለግሪን ኤርያ /ለመናፈሻ/ እንፈልገዋለን በማለት መስቀሉንም እንነቅላለን፣ ጥምቀት ከእንግዲህ በዚህ ቦታ አይከበርም በሚል የማናለብኝነትና የትዕቢት መንፈስ የትህዛዝ ደብዳቤ ለቤተክርስቲያን አስተላልፈዋል ።ይህ አምባገነናዊ አስተዳደርና መመሪያ በቤተክርስቲያን ላይ የታወጀ ግልጽ ጦርነት ስለሆነ በሰላም የኖረውን ሕዝብ ለማወክና ለማበጣበጥ የተንኮል ደባ የሚፈጽሙ የክልሉ ባለ ሥልጣናትን ሕዝበ ክርስቲያንና መንግሥት በጋራ በሕግ አግባብ ሊጠይቋቸው ይገባል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታላቅ የእምነት ተቋም ናት፣ቤተክርስቲያኒቱ የሀገርና የሕዝብ ባለውለታናት ማንም ከመንደር ተነስቶ ቅጥሯን ሊንቀንቅና ድንበሯን ሊገፋ ፈጽሞ አይገባም።

የሲኖዶሱ አባላት የሆናቹ ጳጳሳትና የጠቅላይ ቤተክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች እንዲሁም ፣የሀገረ ስብከቱ ኃላፊዎች በሙሉ ከህዝብ ክርስቲያን ጋር በመሆን የቤተክርስቲያኒቱን ክብር ልታስጠብቁ ይገባል።በተለይ ጳጳሳት ቤተክርስቲያን ስትቃጠልና ስትዘረፍ ተኝታቹ ከርማችሁ ባለቀ ሰዓት እያበነናችሁ እንቃወማለን የምትሉትን ቀልድ አቁሙና በመበለቲቱ ሳንቲም የተንደላቀቀ ኑሯችሁን እየኖራቹ በህዝብ ክርስቲያኑ ላይ የሚደርሰውን ግፍና መከራ በቸልታ ልታዩ አይገባም።በተለይ በአሁን ሰዓት በኦሮሚያ ክልልና በደቡብ ኢትዮጵያ ሆሳዕና ቤተክርስትያን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ ግንባር ቀደም ሆናችሁ ልትታገሉ ይገባል። አንዳንድ ጳጳሳት የእኔ ሀገረ ስብከት አይደለም አይመለከተኝም እያላችሁ እግራችሁን ዘርግታችሁ አትቀመጡ ቤተ ክርስቲያን አንዲት ነች ሁላችንም በአንድነት ቆመን ልንታገልላት ይገባል። ኢጥሙቃን ለሚረባውም ለማይረባውም የቱን ያህል ርቀት በጋራ እንደሚጓዙ አይታችኋል። ለራሳችሁና ለመንጋው አብዝታችሁ ተጠንቀቁ።

+___________________________+

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: