ሶማሌዎችና ሳውዲዎች አንበጣን መመገብ ጀምረዋል
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 30, 2019
የአንበጣው መንጋ በኢትዮጵያ የማስጠንቀቂያውን ደወል ደውሎ ካለፈ በኋላ አሁን ወደ ሶማሊያ እና ሳውዲ አረቢያ አምርቷል። ሶማሌዎች“ከአሳ የበለጠ ጣፋጭ ምግብ”“ልጆቻችን ከአንበጣ በቀር የሚበሉት ሌላ ነገር የለም” በማለት አንበጣውን ጠብሰው በመቆርጠም ላይ ናቸው።
በሳውዲ አረቢያ ደግሞ “አንበጣው አላህ የሰጠን ምግብ” ነው በማለት የአንበጣ መሸጫ የገበያ ቦታዎች ተከፍተዋል። ምግብ ቤት ውስጥ አንድ የአንበጣ ጥብስ እስከ ሁለት መቶ ሃምሳ የአሜሪካ ዶላር እንደሚያወጣ ተገልጿል።
Leave a Reply