Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • December 2019
    M T W T F S S
     1
    2345678
    9101112131415
    16171819202122
    23242526272829
    3031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for December 28th, 2019

ኃያሉ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል የሃገራችንን የውስጥና የውጭ ጠላቶች በሰይፉ ቀጥቅጦ ይጣላቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 28, 2019

አዲስ አበባ፡ የብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን እና ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን። ከብዙ ዓመታት ፈተና በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዚህች ውብ ቤተክርስቲያን ደጅ አበቃኝ፤ እዚያም በጣም ትሑት ከሆኑ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ጋር አገናኘኝ፣ ደመናው ላይም ቅዱስ ገብርኤልን አሳያኝ፤ (በሰተጎን የሚታየው ዓይኑና ቅንድቡ ቁልጭ ብሎ ይታያል) እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።

የቅዱሳኑን የቅዱስ ጴጥሮስንና ቅዱስ ጳውሎስን ፍኖት የተከተሉትን በሃገራችን እና በሊቢያ የተሰውትን ተዋሕዶ ሰማዕታት ሁሌም የምናስባቸው የምንዘክራቸው ናቸው።

ዓለምን ሲያውኩት ያጋንንት ሥራቸው እንዳይተርፈን ለእኛ የእነርሱ ግብራቸው ገብርኤል በሰይፉ ቀጥቅጦ ጣላቸው፤ እናመልክት ለሱ እናስታውስ ጠዋት ማታ እንዲያስተራርቀን ለምኖ ከጌታ

እንኳን ለታህሳስ ገብርኤል አመታዊ በዓል አደረሰን!!!

[የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፲፪:]

ሄሮድስም ሊያወጣው ባሰበ ጊዜ፥ በዚያች ሌሊት ጴጥሮስ በሁለት ሰንሰለት ታስሮ ከሁለት ወታደሮች መካከል ተኝቶ ነበር፤ ጠባቂዎችም በደጁ ፊት ሆነው ወኅኒውን ይጠብቁ ነበር።

እነሆም፥ የጌታ መልአክ ቀረበ በቤትም ውስጥ ብርሃን በራ፤ ጴጥሮስንም ጎድኑን መትቶ አነቃውና። ፈጥነህ ተነሣ አለው። ሰንሰለቶቹም ከእጁ ወደቁ።

መልአኩም። ታጠቅና ጫማህን አግባ አለው፥ እንዲሁም አደረገ።

ልብስህንም ልበስና ተከተለኝ አለው። ወጥቶም ተከተለው፤ ራእይንም የሚያይ ይመስለው ነበር እንጂ በመልአኩ የሚደረገው ነገር እውነት እንደ ሆነ አላወቀም።

______________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: