Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • December 2019
    M T W T F S S
     1
    2345678
    9101112131415
    16171819202122
    23242526272829
    3031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for December 27th, 2019

Ethiopia Warns the World | The Days of Punishment are Coming, the Days of Reckoning are at Hand

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 27, 2019

The current year according to the Ethiopian calendar is 2012.

Judgment Day Coming Soon…

Starting at 1 Minute and 22 Seconds – God’s Just punishment on the Luciferian Nations of the Orient and the Occident, their Military Industrial Complex and Multinational Companies.

+________________________+

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ፈተና በኦርቶዶክሱ ዓለም | የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከእስክንድርያ ፓትርያርክ ጋር የነበራትን ግንኙነት አቋረጠች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 27, 2019

የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የዩክሬን አዲስ ገለልተኛ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እውቅና ለመስጠት ውሳኔዋን ተከትሎ በአፍሪካ ከምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መሪ ጋር ግንኙነቱን አቋርጣለች።

በምስራቁ ግሪክ ኦርቶዶክስ የግብጽና መላው አፍሪቃ ፓትሪያርክ ለዩክሬን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እውቅና መስጠታቸውን ተከትሎ ነው የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ግንኙነትን ለማቋረጥ የወሰነችው።

የ የሞስኮና መላው ሩስያ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በትናንትናው ሐሙስ መገባደጃ ላይ በግብጽ የእስክንድርያውና መላው አፍሪቃ ጳጳስ ከቴዎድሮስ ፪ኛ ጋር ያሉትን ሁሉንም ግንኙነቶች ለማቋረጥ ወስናለች፡

ሆኖም ውሳኔውን ከማይደግፉት የግብጽ ቤተክርስቲያን ቀሳውስት ጋር በህብረት እንደምትቆይ ገልጻለች፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስም በአፍሪቃ የሚገኙ የአኅጉር ስብከት አገልግሎቶች ከእስክንድርያ ፓትርያርክ መስተደዳደር እንዲወገድ እና በቀጥታ በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ኪሪል አመራር ሥር እንዲሆኑ ወስኗል፡፡

እርምጃው የጥር ወር ውሳኔን ተከትሎ ከሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጋር ለዘመናት የኖረችውን የዩክሬን አዲሱ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ከመላው ሩሲያ ኦሮቶዶክስ ቤተክርስቲያን እንድትገነጠልና ነፃነትም እንዲሰጣት ለማድረግ የቁስጥንጥንያውን ፓትርያርኩ ባቶሎሜው የመጀመሪያውን ውሳኔ ተከትሎ ነው፡፡

ወገኖቼ፡ ይህ የክፍፍል ወረርሽኝ ቀላል ነገር እንዳይመስለን። ሁላችንንም የሚመለከት ጉዳይ ነውና። ምንም እንኳን በእስክንድርያ ተቀማጭነት ያላት የምስራቁ ግሪክ ኦርቶዶክስ የግብጽና መላው አፍሪቃ ቤተክርስቲያን ከኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የተለየች ብትሆንም የግብጽም ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አንዳንድ ደስ የማያሰኙ አካሄዶችን ስትራመድ ትታያለች። በአረብ ሙስሊሞች ተጽእኖ ሥር የወደቀችው ይህች ታሪካዊት ቤተክርስቲያን በጣም ብዙ ፈተናዎችን በመጋፈጥ ላይ ነች።

የግብጻውያን ትንኮሳ የቆየና የኖረ ነው። ኢትዮጵያ መንግሥቷ የደከመ ሲመስላቸው አጋጣሚውን እየተጠቀሙ የግል ንብረቶቻችንና ይዞታዎቻችንን በሙሉ ሲነጥቁን፣ አባቶቻችንን ሲያንገላቱና ሲደበድቡ (አቡነ ማትያስ ያውቁታል)የኖሩ መሆናቸው የሚታወቅ ነው።

በኢትዮጵያውያን ዘንድ በተለየ ቅድስና የሚታዩት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳይቀር የኢትዮጵያን ገዳማት “ለመንጠቅ”ቅሽሽ ሳይላቸው አልፈዋል። አንዳንዴ ግብጻውያን በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ላይ የሚፈጽሙትን ግፍ (አር ሱልጣን)ለሚያይ ሰው የግብጻውያን ክርስትና በአፍንጫዬ ይውጣ ነው የሚያሰኘው። በአህዛብ ተጽእኖ ሥር እንደወደቁ ነው የሚያሳየው። ከአህያ ጋር የዋለችእንዲሉ። ከዱር አህያው ከእስማኤል ጋር አብሮ መኖር እንዲህ ያደርጋልና።

እኔ በግሌ በጣም የማከብራቸው የቀድሞው የግብጽ ፓትርያርክ አቡነ ሴኑዳ አማላኪቶቹን ፍልስጤማውያንንና አረብ ሙስሊሞችን ለማስደስት ሲሉ ኮፕት ግብጻውያን ወደ እስራኤል እንዳይጓዙ በአዋጅ መከልከላቸውን ስሰማ በጣም ነበር ያዘንኩባቸው፤ ብዙ ክርስቲያን ግብጻውያንም በኋላ ላይ “አይ ባባ” እያሉ ያዝኑባቸው ነበር። በሳቸው ጊዜ የአረብ ፖለቲከኞቹ በምዕራባውያኑ እርዳታ ኤርትራን ከገነጠሉ በኋላ “የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን” ከእናት ቤተክርስቲያኗ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እንድትገነጠል ያደረገችው የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ነበረች። እንደተገነጠለችም እውቅና ሰጥታ በሥሯ ያደረገቻት ይህችው ቤተክርስቲያን ነበረች። የግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በግብጽ መንግሥት የዲፕሎማሲ ዕርዳታ የሚደገፍ ነው። በመካከለኛው ምስራቅ ላለው ፖለቲካ እስራኤል የአረብ ሙስሊሙን ዓለም ተፅዕኖ ለመቋቋም ይረዳት ዘንድ ግብጽን በአረቦች ዘንድ ተደማጭ ናት የምትባለዋን ግብፅን በእጅጉ ትፈልጋታለች። ግብፅም ለእስራኤል ድጋፏን በሰጠች ቁጥር አሜሪካ ለግብጽ የፖለቲካ፣ የውትድርና እና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ፍላጎቷን ታሟላላታለች።

ዛሬ ሩሲያና ዩክሬንን በተመለከተ ግብጽና ቤተክርስቲያኗ እየወሰደችው ያለው እርምጃ ተመሳሳይ ነው። በአንድ በኩል ግብጽ ከሩሲያም ከአሜሪካም የጦር መሣሪያዎችን በብዛት ትሸምታለች። በቅርቡ እንኳን አባይን አስመልክቶ ፕሬዚደንት አልሲሲ በሩሲያው ሶቺ ከኢትዮጵያ ህገወጥ መሪዎች ጋር ከተገናኘ በኋላ በጥቂት ቀናት ውስጥ ተመሳሳይ ስብሰባ በአሜሪካ ለማድረግ በቅቷል። እስኪ እናነጻጽረው፦ የግብጽ መንግስት፣ የግብጽ ቤተክርስቲያንና የግብጽ ሙስሊሞች ሁሉም በአንድነት ለሃገራቸው ግብጽ የቆሙ ናቸው ፥ በተቃራኒው የኢትዮጵያ መንግስትና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ኢትዮጵያን እየከዱ ነው፤ በግብጽና በኢትዮጵያ መካከል ጦርነት ቢቀሰቀስ ከግብጽ ጎን እንደሚሰለፉ አያጠራጥርም፤ ታሪክም የሚያስተምረን ይህ ነው።

አሁን ደግሞ፤ በሃገሩ የምትገኘው የምስራቅ ግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በቀጥታ ለማይመለከታት ለዩክሬይን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እውቅና መስጠቷ ከአባይ ወንዝ ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል። የግብጹ ፕሬዚደንት አልሲሲ በአባይ ጉዳይ የአሜሪካን ድጋፍ ለማግኘት አሜሪካ በዩክሬይን በምትከተለው የፀረሩሲያ መስመር ላይ መሰለፍ ይሻል፤ የኮፕት ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ቴዎድሮስም ከግብጽ መንግስት በኩል አስፈላጊውን ድጋፍ ለማግኘት ሲል ፀረሩሲያ እና ፀረኢትዮጵያ የሆነ አቋም መያዝ ይኖርባቸዋል። እነዚህ ብልሹ ባለሥልጣናት “የኦሮሚያ ቤተክህነት” የተሰኘውን የዲያብሎስ ህልምም ከማሟላት ወደኋላ እንደማይሉ ማወቅ ይኖርብናል።

በክርስቶስ ተቃዋሚዋ ቱርክ መንጋጋ ውስጥ የገባቸው የቁስጥንጥንያ ቤተክርስቲያንም እንዲሁ ከሉሲፈራውያኑ ምዕራባውያን ጋር ከተደመረች ቆይታለች፡፡ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንም ለዩክሪየን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እውቅናዋን ሰጥታለች። ለረጅም ጊዜ፡ በሶቪየት ሕብረት ዘመን ሳይቀር በዘውገኝነት ጋኔን የተያዘችው ዩክሬንም ብዙ ውለታ የዋለችላትን እህቷን ኦርቶዶክስ ሩሲያን ለመተናኮል በሉሲፈራውያኑ ተመርጣለች። ከዝብግኒው ብረዥንስኪ እስከ ጆን ማኬንና ጆርጅ ሶሮስ ድርሰ ሁሉም ቤተክርስትያን ነፃነትን ለመስጠት የተሰጠው ውሳኔ የኦርቶዶክስ ዓለምን ለሁለት ከፍሎ የነበረ ሲሆን አንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት የሚደግፉ ሲሆን ሌሎችም እንቅስቃሴውን የሚተቹ ናቸው።

የኦርቶዶክስ ሰርቢያን ዋና ከተማን ቤልግራድን በትንሣኤ ሰንበት በቦንብ ጣይ አውሮፕላኖች የደበደበው የሉሲፈራውያን ኔቶ ድርጅት በኦርቶዶክስ ክርስቲያኑ ዓለም፡ በተለይ በተራራማዋ ተዋሕዶ ኢትዮጵያ ላይ ጦሩን ለማዝመት ያው ላለፉት ሃያ ዓመታት በተራራማው አፍጋኒስታን በመለማመድ ላይ ይገኛል። ይህን ሁሉ ጊዜ በአፍጋኒስታን ምን ይሠራሉ? ብለን እንጠይቅ።

ከሁለት ዓመታት በፊት፤ የሉሲፈራውያኑ ተቋም ሲ.አይ.ኤ በግራኝ አብዮት አህመድ የሚመራውን መፈንቅለ መንግስት ገና ከማካሄዱ በፊት የሚከተለውን ጽሑፍ አቅርቤ ነበር፦

ቅዱስ ሚካኤል + ኢየሩሳሌም + ያልተባበሩት መንግሥታት + የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ልጆች ይህችን የ ቅ/ ሚካኤል ዕለት እናስታውስ፤

ወንድሞቻችንን በባርነት ከምሸጡት፣ እህቶቻችንን ከፎቅ እየወረወሩ ከሚገድሉት አርቦች ጋር ከአርቦች ጋር በማበር የኢትዮጵያን የድጋፍ ድምጽ በተባበሩት መንግሥታት እንድንሰጥ ተደርገናል። ዓጼ ኃ/ ሥላሴም ተምሳሳይ ድርጊት ከፈጸሙ በኋላ ነበር፤ ኢትዮጵያችን በጣም አስከፊ በሆነ መልክ እንድትራቆትና እንድትደቅ ሁለት ትውልድ እንዲጠፋ የተደረገው።

የግድ አሜሪካንና እስራኤልን መደገፍ የለብንም፡ ለዚህም እንደነ ቤኒን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኡጋንዳ፣ ኬንያ፣ ሌሶቱ፣ ማላዊ፣ ጊኒ ኤኳተሪያል፣ ፊሊፒንስ፣ ኮሎምቢያ፣ ፓናማ፣ አውስትራሊያ፣ አርጀንቲና፣ ቦስኒያ፣ ፖላንድ፣ ሮማኒያ ወዘተ የመሳሰሉት 15 አገሮች በገልተኝነት ድምጽ ከመስጠት መቆጠብ ነበረብን።

የሚያሳዝነው እስራኤልን ወይም አሜሪካን አለመደገፋችን ሳይሆን አረቦችን መደገፋችን ነው! አገራችን ከፍየል አገራት ጋር አብራ መሰለፍ አልነበረባትም። ያልተባበሩት መንግሥታት በሊቢያ ስለሚካሄደው የባርነት ንግድና በእስላም አገሮች የሚታየው የክርስቲያኖች ጭፍጨፋን ልክ እንደዚህ በደንብ መውገዝ ነበረበት እንጂ ኢምባሲ ተዛወረ አልተዛወረ እንደ ትልቅ ነገር ተቆጥሮ የተለየ ሤራ መጠንሰስ አልነበረበትም። ወስላቶች!

እስራኤላውያን ለክፉም ሆነ ለበጎ በተለይ በኢትዮጵያውያን ላይ ልዩ የሆነ አትኩሮት ነው ያላቸው። ግብጽም፡ ልክ እንደ ቀድሞው በደስታ ጮቤ ትረግጣለች፤ ፍርሀት የተጫነው የመረጋጋት መመሪያ ሠርቶ አያውቅም።

800 ዓመታት በፊት በመሀመዳውያን ላይ ቅስም የሚሰብር ድል የተቀዳጀቸው ስፔይን (በዚህም፤ ኢትዮጵያ፡ ስፔይንና ፖርቱጋልን በመርዳት በይፋ የማይታወቅ ከፍተኛ ሚና ተጫውታለች፤ ሌላ ጊዜ..) ያው በካታላንውያን በኩል ኃይለኛ ፈተና ገጥሟታል፤ በዛሬው ዕለት በካታሎኒያም የተካሄደው ምርጫ ብዙ መዘዝ አለው። ካታሉኒያ + ቫሎኒያ + ባቫሪያ + ኤርትራ + ኦሮሚያ + ክሮአስያ + ስኮትላንድ + ቱርክ + ዩክሬየን + ኩቤክ + እነዚህ ግዛቶች የአመጸኞቹ አለቃ ሰይጣን በክርስቲያን ሕዝቦች ላይ እንዲያምጹ ያዘጋጃቸው ግዛቶች ናቸው። በጌታችን ልደት ዋዜማም ይህ ሁሉ መከሰቱ ያለምክኒያት አይደለም።

የድምጽ ሰጪ አገሮች ሰንጠረዡም በኢትዮጵያ ሦስት ቀለሞች፤ አረንጓዴቢጫቀይ ያሸበረቀ ነው። አረንጓዴ፤ አረቦች የሰረቁት የእስላም ቀለም ሆኗል፤ ቢጫ ገለልተኞች፣ ቀይ ደግሞ አመሪካና እስራኤል የደገፉት ናቸው። በጣም አስገራሚ ነው! የ ሄጌል ThesisAntithesisSynthesis ሞዴል

ይህን የታህሳስ ፲፪ ፥ ፪ሺ፲ ዓ.ም ዕለትን በደንብ እናስታውስ።

________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: