Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • December 2019
    M T W T F S S
     1
    2345678
    9101112131415
    16171819202122
    23242526272829
    3031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for December 26th, 2019

የፀሐይ ግርዶሽ ፥ ጋኔን ፀሐይን በላት | የዋቄዮ አላህ እና የሰው አጋንንት አሁን ለማጥፋትና ለማሳት ተዘጋጅተዋል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 26, 2019

ተጠንቀቁ!!! ዲያብሎስ ሰይጣን ብርሃንን እየተዋጋ ነው።

ባለፈው ጊዜ ሊሲፈራውያኑ አሽከራቸውን ግራኝ አብዮት አህመድ አሊን የሸለሙት ሙሉ ጨረቃ እስክትወጣ ድረስ በመጠበቅ ነበር፤ አሁን ደግሞ የፀሐይ ግርዶሽ ተከስቶ ጨለማ በሚሰፍንበት ወቅት በህዝበ ክርስቲያን ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ከአጋንንት መናኸሪያ ከሳውዲ መካ ትዕዛዝ ተላልፏል። በትናንትናው ዕለት የአክሱም ኃውልትን የሚመለከት ቪዲዮ ያቀረብኩት በምክኒያት ነበር ማለት ነው፤ በጊዜው አላወቅኩትም ነበር። እንደሚታወቀው ጣዖት አምላኪዎቹ፡ የአክሱም ኃውልትን ጫፍ/ራስ ለሳባውያን አምላክ አልማቃህየግማሽ ጨረቃ ቅርጽ እንዲኖረው ተደርጓል። ይላሉ። እንግዲህ የጨረቃ አምላክ “አልማቃህ” የሙስሊሞች አምላክ ነው ማለት ነው። በአክሱም መስጊድ የመሥራት ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸው አንዱ ምክኒያት ይህ ነው።

[፩ኛ የጴጥሮስ መልእክት ምዕራፍ ፭፥፰፡፱]

በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤ በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።

[፪ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፲፪፥፯፡፰]

ስለዚህም በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመኝ የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ፤ ይኸውም እንዳልታበይ ነው። ስለዚህ ነገር ከእኔ እንዲለይ ሦስት ጊዜ ጌታን ለመንሁ።

[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፲፪፥ ፩፡ ፱]

ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች።

እርስዋም ፀንሳ ነበር፥ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጭንቃ ጮኸች።

ሌላም ምልክት በሰማይ ታየ፤ እነሆም ታላቅ ቀይ ዘንዶ፤ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ነበሩት በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች ነበሩ፥

ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ።

አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጅዋም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ።

ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቡአት በእግዚአብሔር ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ በረሀ ሸሸች።

በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ። ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፥ አልቻላቸውምም፥ ከዚያም ወዲያ በሰማይ ስፍራ አልተገኘላቸውም።

ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።

________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የዘመናችን ፈርዖኖች ኢትዮጵያን፣ ተዋሕዶነትን፣ ሃገረ ርስተ ድንግልን፣ ሰንደቅ ዓላማዋን በዋናነት ዒላማቸው አድርገዋል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 26, 2019

[መጽሐፈ መክብብ ፲፥፭]

ከፀሐይ በታች ያየሁት ክፉ ነገር አለ፥ እርሱም ከገዢ የሚወጣ ስሕተት ነው

ታዲያ የዛሬዎቹ ገዥዎች ፋሺስት ጣሊያን ከሠራው የከፋ ወንጀል በመፈጸም ላይ ናቸው። ወገኔ፡ የዛሪዎቹ ገዢዎች፦

  • + አገርህን አላፈረሱም?!
  • + በዘር አላፋጁም?!
  • + ሰንደቅህን አላጠፉም?!
  • + እምነትህን ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንህን አላቃጠሉም?!
  • + የክርስቶስ ልጆችን የድንግል ልጆችን አልገደሉም?! አላረዱም?! አላቃጠሉም?!

እነዚህ ገዢዎች እስኪ ከፋሺስት ጣልያን በምን ይለያሉ?! ካልከፉ በስተቀር!

ዛሬ ወገን ንስሐ ከመግባት ይልቅ የዘመኑን ዳታኖች ገዢዎች፣ አጭበርባሪዎች፣ ትዕቢተኞች፣ ዘረኞች፣ ጨፍጫፊዎች የሚነዙልህን ውሸትና ዲስኩር እያደመጥክ፣ ሆድህን በወሬ እየሞላህ በሙሉ ልትጠረግ ደርሰሃል፤ እየሞትክም የእነርሱን የተቀመመ ፕሮፓጋንዳ አሁንም ታዳምጣለህ፤ ሁለት እግር አለኝ ብለህ ሁለት ዛፍ ላይ ለመውጣት ትታገላለህ፤ ወዲህ አንዳንዴም የእግዚአብሔርን ቃል ልትሰማ ትፈልጋለህ ፥ ወዲያ ደግሞ ሕይወትህንም ኑሮህንም እነርሱ ናቸው ብለህ አምነህ የዘመኑን ፈርዖኖች፣ የዘመኑን ዳታኖች፣ የዘመኑን ሆድአደሮች፣ የዘመኑን ጨካኞች ዘረኞች ታምነህ ትሠማራለሁ፣ ትውጣለህ ትወርዳለህ።

ሕዝቡ በፈቃዱ ታሳሪ ሆኗል ፥ ከፈጣሪው የተጋጨ፣ የረከሰ፣ በምንዝርና፣ በሰዶምነት፣ በጠጭነት የተበከለ፣ ሰውነቱ ሁሉ የተልፈሰፈሰ ትውልድ ፈጥረው እንዳሻቸው እየፈጩት፣ እየነዱት ይገኛል፤ ልብ ላለው ሰው ይህ የሚያየው የየዕለቱ ተግባር ነው። የዛሬው ትውልድ የሆንከው ወገኔ ለምን የገዢዎች ፕሮፓጋንዳ ቀለብተኛ ትሆናለህ?! ለምንስ እራስህን ለሞት አሳልፈህ ትሰጣለህ?! በምድርም ውዳቂ፣ በሰማይም የሲዖል እራት፤ የገሃነም ወራሽ ለምን ትሆናለህ?! ለምን የፈጣሪህን ቃል ሰምተህ ተፀፅተህ ከጠፋህበት ተመልሰህ ወደ ፈጣሪ ጉያ አትሰበሰብም?!

የዘመናችን ደግሞ አባቶች፣ መምህራን ነን የሚሉ ሁሉ ሕዝቡን በወኔ አያስታጥቁትም፣ በእግዚአብሔር ቃል አያስታጥቁትም፣ ስለ ሃገር፣ ስለ ወገን፣ ስለ እምነት፣ ስለ ባንዲራ፣ ስለ እርስተ ድንግል፣ ስለ እውነት መዋጋት ወንጀል አድርገው ይሰብካሉ ያስተምራሉ፤ ያ ደግሞ ለጠላት ከፍተኛ መሣሪያ ሆኖ አገልግሏል፤ ይህ ግን ስህተት ነው። ወገኔ፤ እንግዲያውስ ሃጢዓቱ ያለመዋጋቱ፣ ሃገር ሲጠፋ፣ ሃይማኖት ሲፈርስ፣ ሃገር ሲቆራረስ ሰንደቅ ሲረክስ ሲናቅ ዝም ብሎ ማየት ነው፤ የሚያስጠይቅ፡ አባቶቻችን የሄዱበት እውነት ላይ አለመሄድ ነው። ይህ ደግሞ ትልቁ ጥፋታችን ነው።

________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: