ክፍል ፪
ሁሉም ከዲያቢሎስ ናቸውና።
የጠፋው ቀጣፊ፣ አታላይ፣ ፌዘኛ፣ አሽቃባጭ፣ ከሃዲና ከዲያብሎስ ጋር የተደመረ ትውልድ ግን፡ እሱም ዘሩም የኢትዮጵያን ትንሣኤ ለማየት እድል አይኖራቸውም።
[፩ኛ የጴጥሮስ መልእክት ምዕራፍ ፪፥፭፡፲]
“እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።
በመጽሐፍ። እነሆ፥ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ ተጽፎአልና።
እንግዲህ ክብሩ ለእናንተ ለምታምኑት ነው፤ ለማያምኑ ግን አናጢዎች የጣሉት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ የዕንቅፋትም ድንጋይ የማሰናከያም ዓለት ሆነ፤
የማያምኑ ስለ ሆኑ በቃሉ ይሰናከሉበታልና፤ ለዚህ ደግሞ የተመደቡ ናቸው።
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤
እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።”
+ የእንግሊዝኛው መልዕክት ለብቻው ተንጥሎ ይቀርባል፤ ወንድማችን ከጠቀሱት የሉሲፈር የምጣኔ ሃብት ተቋማት መካከል አንዱ የሆነው አውሮፕላኖችና የጦር መሣሪያ አምራቹ “ቦይንግ” በዛሬው ዕለት ዋና ሥራ አስኪያጁን ከኃላፊነቱ አስወግዷል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሆራ በሚገኘው የዋቄዮ አላህ ዋሻ ከተከሰከሰበት ዕለት አንስቶ አንጋፋው የቦይንግ ኩባንያ ፕሬዚደንት ትራምፕን ሳይቀር በጣም ያስደነገጠ ኪሳራ ውስጥ ገብቷል። ይህ በአጋጣሚ አይደለም፤ እያንዳንዱ የሉሲፈር ኩባንያ ይወድቃል። በነገራችን ላይ፤ ምንም እንኳን የተከሰከሰው የቦይንግ አውሮፕላን ሞዴል ኮምፒውተር ነክ ችግሮች እንዳሉት ቢታወቅም፤ ግን በዚህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፓላን መከስከስ የአብዮት አህመድ አሊ እጅ አለበት የሚል ዕምነት አለኝ። ረዳት አብራሪውን አህመድ ኑር ሞሃመድን እንያዝ… በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ።