Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • December 2019
  M T W T F S S
   1
  2345678
  9101112131415
  16171819202122
  23242526272829
  3031  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Archive for December 20th, 2019

የማንቂያ ደወል ከሊቢያ? | የዮሐንስ ራዕይ ሰባቱ መቅረዝ? | የኢትዮጵያ ሰማዕታት?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 20, 2019

+++ ዘመነ ዮሐንስ +++

በሊቢያ ትሪፖሊ እና ቤንጋዚ ከተሞች በትናንትናው ዕለት ታሕሣሥ ፱ – ፪ሺ፲፪ ዓ./ 19 / 2019 ነዋሪዎች ተሰምቶ የማይታወቅ ምስጢራዊ የጩኸት ድምጽ እንደሰሙ “የሊቢያ ኦብዘርቨር” የተሰኘው ሚዲያ ዘግቧል፡፡ ድምጹ ከየት እንደመጣ ማንም አያውቅም ብሏል።

በአሕዛብ የተሰውት ወንድሞቻችን አብዛኞቹ ከአዲስ አበባ ጨርቆስ ክፍለ ከተማ ናቸው፤ በጨርቆስ ዕለት ይህ ምስጢራዊ ድምጽ ተሰማ። በአጋጣሚ?

ባለፈው ዓመት ልክ በዚህ ወቅት የሚከተለውን፡ ይኸው የሊቢያ ኦብዘርቨር ያወጣውን መረጃ አቅርቤ ነበር፦

የሊቢያ ኦብዘርቨር እንዳሳታወቀው ከሆነ በሊቢያዋ ሲርቴ ከሦስት ዓመታት በፊት በሙስሊሞች የታረዱት የ፴፬ ኢትዮጵያውያኖች አካላት ባንድ ላይ ተከማችተው አሁን ተገኝተዋል

የወንድሞቻችን አካላት እስር ቤት በሚገኙት ገዳዮቹ ላይ ምርመራ በሚካሄድበት ወቅት መረጃ ከተሰበሰበ እና መቃብሩ የት እንደሚገኝ ከታወቀ በኋላ ነበር በሰንበት ዕለት በቁፋሮ የተገኙት(ገዳዮቹ እስካሁን በሕይወት አሉ?)

የአገር ውስጥ እና ዓለም አቀፋዊ የህግ ሥነ ሥርዓቶች ሲጠናቀቁ አካላቱ ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉሲል የወንጀል መርማሪው ቡድን አስታውቋል።

እትብታችሁ ለተቀበረበት የእናት አገራችሁ አፈር ቶሎ ያብቃችሁ፤ ወንድሞቼ!

አመት አለፈው፤ ግን የሰማዕታት ወንድሞቻችን ፍልሰተ አጽም ወደ እናት ሃገራቸው ለመመለስና በክብር ለማሳረፍ ምን እየተደረገ ነው? ጉዳዩ የት ደረሰ? ምነው ረሳናቸው? እነዚህ ወንድሞቻችን እኮ በጠላት ሊቢያ በረሃ በታላቅ መንፈሳዊ ተጋድሎ ሰማዕትነትን የተቀበሉ የሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ሰማዕታት ናቸው። ይህ በእኛ ዘመን የተከሰተውን ተዓምር እንዴት ቸል እንለዋለን? እነዚህ ወጣቶች ዛሬም ድረስ እየፈሰሰ ላለው የክርስቲያኖች ሰማዕታት ደም ማሳያ ተምሳሌት ናቸው እኮ!!! እንዴት ነው በአፍቅሮተ ሰልጣን የሰከረው እና በተወዳጅነት ሱስ የተጠመደው ገዳይ አብዮት አህመድ አሊ ለመጭው “ምርጫ” “እኔ አመጣኋቸው” በማለት የመጫወቻ ካርድ እስኪያደርጋቸው ነው የምንጠብቀው? ቤተ ክህነት፣ ማሕበረ ቅዱሳንና የሚመለከታቸው ሁሉ ምነው ዝም አሉ? ማንን ነው የሚጠብቁት? ወዴት እያምራን ነው?

አድሲቱን ምድርና አድሲቱን ሰማይ ሃገርህንም ሰማያዊቷን ኢየሩሳሌምን ለባሏ እንደተዘጋጀች ሙሽራ አምራ ከላይ ወደታች ለአንተ ስትሰጥ ታያለህ። ታላቅም ድምፅ ከሰማይ። እነሆ፥ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው ከእነርሱም ጋር ያድራል፥ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤ እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፥ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፥ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፳፩፥፩፡፬]

+++ በሊቢያ በረሃ በሙስሊሞች የታረዱት 12ቱ የቂርቆስ ሠፈር ሰማዕታት ፡ በሁለት ህገወጥ መስጊዶች መካከል የፈለቀውን እጹብ ድንቅ ጸበል አፍልቀውት ይሆን?+++

+________________________+

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, Infos | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: