ጀግናው ክርስቲያን (ቦብ) | ክርስቲያን ኢትዮጵያ ለመሀመዳውያን ጥገኝነት መስጠቷ ታሪካዊ ስሕተት ነበር
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 19, 2019
ልብ በሉ፦ በደቡብ ሱዳን ሙስሊም አረቦች ነበሩ 2ሚሊየን አፍሪካውያን ክርስቲያኖችን የጨፈጨፉት፤ ክርስቲያኖችን አረብ ለማድረግ በ18ዓመት ብቻ ሁለት ሚሊየን ደቡብ ሱዳናውያን ተገድለዋል።
አፍሪቃውያን ክርስቲያኖች አረብ መሆን አንፈልግም በማለታቸው ደቡብ ሱዳን ተገንጥላ ነፃ ሃገር ልትሆን በቅታለች።
ሁለት ሚሊየን ክርስቲያኖች በመሀመዳውያን መጨፍጨፋቸውን እናንት ለአፍሪካ እንታገላለን የምትሉ ግብዞች እኮ አታውቁትም፤ አይደል!? እነዚህ ክርስቲያኖች እንዲጨፈጨፉ የእስልምና አስተምህሮና ልምድ በግልጽ ይናገራሉ።
ነጮች ከመቶ ዓመታት በፊት በሠሩት ግፍ ዛሬም ትወቅሷችዋላችሁ፤ አረቦች በአፍሪቃውያን ላይ ዛሬም እየፈጸሙት ስላለው አሰቃቂ ግፍ ግን ጸጥ ብላችኋል፤ ቦኮ ሃራምና የሙስሊም ፉላኒ ነገድ የናይጄሪያ ክርስቲያኖችን እየጨፈጨፏቸው ነው፤ ግን ስለዚህ ጉዳይ ምንም አትናገሩም።
እነዚህ ሙስሊሞች አፍሪካውያን ክርስቲያኖችን እየገደሏቸው ነው እኮ! ስለዚህ በኢትዮጵያና በመላው አፍሪካ ያላችሁ ክርስቲያኖች ተባበሩ፤ በአንድ ላይ ሥሩ።
እስልምና እና መሀመዳውያን ሙስሊም ባልሆኑ ማህበረሰቦችን ላይ የሚፈጽሙትን ግፍ የሚያሳዩ በቂ እስላማዊ ምንጮች አሉ (ቁርአን፣ አሃዲት፣ ታፍሲር ወዘተ)።
ክርስትና ከእስልምና በጣም ይለያል፤ ክርስትና አንድን ሰውና ማሕበረሰብ የተሻለ ሰውና ማሕበረሰብ እንዲሆኑ ስለሚያደርጋቸው፤ ኢትዮጵያዊውን ወይም ፉላኒውን አረብ ማድረግ ሳይሆን የተሻለ ኢትዮጵያዊ ወይም ፉላኒ እንዲሆን ይረዳቸዋል፤ በጎውን ማንነታቸውን በይበልጥ እንዲያዳብሩ ይረዳቸዋል።
ክርስትና ባሕሎችንና ቋንቋዎችን የማጥፋት ተልዕኮ የለውም ስለዚህ ወንጌልን በመቀበል ክርስቲያን የሆኑ ማሕበረሰቦች ቋንቋቸውን እና ባሕላቸውን ጠብቀውና አዳብረው ይኖራሉ።
ክርስትና ጨለማውን የሚያጋልጥ ብርሃን ነው፣ ክርስትና የአንድን ባሕል ጎጂ ክፍል በማስወገድ ጥሩውና በጎው ጎን ጎልቶ እንዲወጣ ያደርጋል። ምክኒያቱም የክርስትና እምነት የሕግ ሥርዓት የለውምና ነው፤ የክርስትና እምነት የሰውን ልብ የሚቀይር የእሴቶች ሥርዓት ስላለው፡ በአካባቢው ባህል ውስጥ በቀላሉ ይገለጻል።
አረብ ሙስሊሞች በተቃራኒው መሀመድን ሙሉ በሙሉ መኮረጅ ስለሚጠበቅባቸው፤ ወደ ሌላ ሃገር ሲጓዙ የመሀመድን ነገሮች ሁሉ የማንጸባረቅ ግዴታ አለባቸው።
ስለዚህ እስልምና የበላይነቱን በያዘባቸው ሃገራት፤ አረብ ያልሆኑ ሕዝቦች ባሕላቸውን፣ ቋንቋቸውን፣ ሃይማኖታቸውንና ሁለመናቸውን እንዲያጡ ይገደዳሉ።
አሹሮች፣ ኮፕቶች፣ ኑቢያውያን፣ ለዚህ ምሳሌዎች ናቸው አረቦች በግብጽና ሱዳን ኑቢያውያን በሚኖሩበት አካባቢ ግድቦችን በመስራት የኑቢያውያን ስልጣኔ ተጠራርጎ እንዲጠፋ ለማድረግ በቅተዋል።
ለኑቢያውያን ማንነትና መብት የምትታገለዋ ሱዳናዊት ለመሰደድ ተገዳለች፤ ምክኒያቱም አረብ መሆን ስላልፈለገች ነው፤ እስልምና እና አረብ መሆን አብረው ነው የሚጓዙት።
በግብጽና በኢትዮጵያ የአገሬው ተወላጅ ቤተክርስቲያን መዳበሯ ለዚህ በቂ ማስረጃ ነው፤ በግብጽና ኢትዮጵያ አፍሪቃውያን ፓትርያርኮች፣ ጳጳሳትና የቤተክርስቲያን ምሁራን አሉ፤ በኒቂያ ጉባኤ ኦሮቶዶክስን በመከላከልና የአርዮስን ክህደት ለመቃወም ተጠርተው የነበሩ ብዙ አፍሪቃውያን ነበሩ።
መነኩሴነት ከአፍሪቃ/ ከግብጽ ነው የጀመረው እኛ አውሮፓውያን መንኩሴነትንና መንፈሳዊነትን የተቀበልነው ከአፍሪቃ ነው፤ ይህም ጥሩ ነገር ነው። ምክኒያቱም በቤተክርስቲያን የጋራ መግባባት ስለማምን ነው፣ ክርስትና ሁሉንም ብሔር የሚያቅፍ እምነት ስለሆነ ነው፤ የትኛውንም ሕዝብ ርስት ለመጋራት ፈቃደኞች ስለሆንን ነው፤ ክርስቲያን ሲኮን ሁሉም በጌታ አንድ ነውና ነው፤ ክርስቲያኖች ይህን እውነታ እንደገና ማግኘት ይኖርባቸዋል።
የአንግሎ–ሳክሰን ክርስቲያኖች ከሌሎች ብሔሮች ጋር ለሺህ ዓመታት አብረው ይሠሩ ነበር፤ ስለዚህ ነጭ ዘውገኞች እኔን በነጭነቴ ከጥቁር ወይም እስያውያን ክርስቲያኖች የመነጠል መብት የላችሁም።
ዘረኛ ከሆነ ብሔርተኛ ነጭ አፍሪቃዊውን ወይም እስያዊውን ክርስቲያን እመርጣለሁ። ከነጭ ብሔርተኛ ይልቅ ለኢትዮጵያዊው ክርስቲያን የሰላምታ እጄን መስጠት እወዳለሁ።
ክርስትና የአንድን ማሕበረሰብ መጥፎ ጎን በማስወገድ ጥሩውና በጎው ጎን ጎልቶ እንዲወጣ ስለሚያደርግ ለአፍሪቃ የሚበጀው ክርስትና ብቻ ነው።
እስልምና ግን ሕዝብን አረብ የማድረጊያ መሳሪያ ነው፤ እስኪ ይታያችሁ፤ አንዲት ሴት ኒቃብ ለብሳ የአፍሪቃ ጫካ ውስጥ ስትንጎራደድ፤ ክርስትና ግን ይህን አያስገድድም።
በእስላም ካሊፋት የግብጽ ክርስቲያኖች ክፉኛ ተሰቃይተው ነበር፤ ዓብያተ ክርስቲያናቱን ያፈራርሱባቸውና ያበላሹባቸው ነበር፣ ክርስቲያኖች ክብረ በዓላቸውን መንገድ ላይ ማክበር ይከለከሉ ነበር፣ የቤተክርስቲያን ደወል መደወል ክልክል ነበር፣ ከመስጊድ ጎን ቤተክርስቲያን መስራት አይፈቀድላቸውም ነበር፣ ቤተክርስቲያን
ለማደስ እንኳን የካሊፉን ፈቃድ መጠየቅ ነበረባቸው፤ በዚህም ብዙ ዓብያተ ክርስቲያናት ፈራርሰው እንዲጠፉ ተደርጓል። ክርስቲያኖች ከከተማ ውጭ ቤተ ክርስቲያን እንዲሠሩ ተገድደዋል። ዓብያተ ክርስቲያናቱ በሮቻቸውን በዋና ዋና መንገዶች በኩል እንዳይከፍቱ ተደርገዋል። ፀሎት እና ቅዳሴአቸው በሙስሊሞች ዘንድ እንዳይሰሙ።
ሙስሊሞች ክርስቲያኖችን መንገድ ላይ ካገኟቸው ወደ ጠባቡ መንገድና ወደ ገደል እንዲሄዱ ይገፏቸው ነበር፤ መለዮ እንዲለብሱና ቢጫ ቀበቶም እንዲያስሩ አዘዋቸው ነበር። ክርስቲያኖች ፈረስ ላይ መውጣት ሰልማይፈቀድላቸው አህያ ብቻ ነበር የሚጋልቡት፣ ጎራዴ ነገር መያዝም አይፈቀድላቸውም ነበር።
በዚህ መልክ ነበር አረብ ሙስሊሞች ክርስትናን በሰሜን አፍሪቃ ለማጥፋትና የግብጽን ክርስትናም ለመጉዳት የበቁት።
እናንተ ጥቁር ብሔርተኞች ሙስሊም ወንበዴዎችን ፈርታችሁ ስለዚህ አስከፊ ታሪክ ከማውራት ተቆጥባችኋል፤ አፍሪቃዊ ማንነታችሁን እንደገና ማግኘት ከፈለጋችሁ ስለዚህ ታሪክ ማውራት ይገባችኋል፤ መጤ ስላልሆነውና አፍሪቃዊ ስለሆነው ክርስቲያን ታሪክ ማወቅ ይኖርባችኋል።
ከአርሜኒያ ጎን በአለም የመጀመሪያው ክርስቲያን መንግስት የተመሠረተው በኢትዮጵያ ነበር። ጥቁር ኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ነበሩ በክርስቲያናዊ ደግነታቸው፣ እንግዳ ተቀባይነታቸውና ፍትህ አፍቃሪነታቸው ለመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች ጥገኝነት የሰጧቸው። ነገር ግን ይህ ትልቅ ታሪካዊ ስህተት ነበር።
አዎ! መሀመድ ተከታዮቹን ወደ ኢትዮጵያ ነበር የላካቸው፤ ከመሀመድ አጋሮች አንዱ (የመሀመድ የአክስቱ ልጅና የሚስቱ ወንድም ኡቤይዱላህ ኢብንጃሽ) በኢትዮጵያ ተጠምቆ ክርስትናን ተቀብሏል።
ጠያቂው፦ “የኢትዮጵያ ንጉሥ እስልምናን ተቀብሏል” የሚል ነገር ሰምቼ ነበር፤ ምን ያህል እውነት ነው?
ቦብ፦ ይህ ውሸት ነው፤ ሙስሊሞች ሁልጊዜ ስለ ታሪክ መቅጠፍ ይወዳሉ፤ ይህ ውሸት እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ። ሃቁ ግን ሙስሊሞች ብዙ ጊዜ ታሪክን ከልሰው ይጽፋሉ። (ልክ እንደ ዋቄዮ–አላህ ልጆች)
ሙስሊሞች 300 ዓመት ስለቆየው ስለ አውሮፓውያን የባርነት ንግድ (ይህ ትክክል ተገቢ አለመሆኑን እቀበላለሁ) ብዙ ይለፍፋሉ፤ እስልምና ለ1400 ዓመታት እያካሄደ ስላለው የባርነት ንግድ ግን ጸጥ ያላሉ። በዚህ ዘመን እንኳን ባሪያ ህፃን ለመግዛት ወደ ሙስሊሞቹ ካርቱም ሱዳን፣ ቻድና፣ ማውሪታኒያ ይጓዛሉ።
ሰዎች፣ ታሪካችሁን አጥኑ፤ ሂዱና ኮፕቶችና ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን ስለ ታሪካቸውና እንዴት እንደሚኖሩ አነጋግሯቸው፤ የነጮችን ክርስትና እንድትክተል አልሻም፤ የጥቁር ኢትዮጵያውያንን ክርስትና እና የያዙትን እውነት ተከተሉ።
በ፲፭ ኛው ክፍለዘመን የፖርቱጋሎች ክርስቲያን ሠራዊት ከኢትዮጵያ ክርስቲያን ወገኖቹ ጋር በመሰለፍ ወራሪ እስላሞችን ድል ነስተዋቸዋል። ለአፍሪቃውያን እውነተኛው የክርስቲያን መንፈሳዊነት ያለው እዚያ ነው።
Leave a Reply