Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • December 2019
    M T W T F S S
     1
    2345678
    9101112131415
    16171819202122
    23242526272829
    3031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

ሲ.አይ.ኤ’ በፕሬዚደንት ትራምፕ ላይ የመንግስት ግልበጣ ለማድረግ እየሞከረ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 19, 2019

ኢትዮጵያ የጎሳ ፖለቲካ እንድትከተል ያደረገችው አሜሪካ እራሷ በፖለቲካ ዘውገኝነት እየተፈረካከሰች ነው። የፖለቲካ ዘውገኝነት የአሜሪካን ውድቀት እያስከተለ ነው። ኢትዮጵያ መውጫና መግቢያ በር እንዳይኖራት ያደረገችውና 361 የባሕር በሮች ያሏት አሜሪካ ከ19 ዓመታት በፊት ስትደግፋቸው የነበሩት መሀመዳውያን ባደረሱባት የሽብር ጥቃት ልክ እንደ ኢትዮጵያ አንድም የባሕር በር እንደሌላት ሃገር ሆና ነበር። ዛሬ ደግሞ ኦሮሞ ሽብር ፈጣሪዎችንና ግብጽን እሹሩሩ በማለት ላይ የምትገኘዋና “አንድ ሕዝብ፣ ሁለት ፓርቲዎች” እያለች የምትመጻደቀው አሜሪካ መቶ ጎሳዎችና መቶ የፖለቲካ ፓርቲዎች ካሏት ኢትዮጵያ በከፋ የፖለቲካ ዘውገኝነት ቀውስ ውስጥ ገብታ ትታያለች።

ፕሬዚደንት ትረምፕ ሥልጣናቸውን ያለአግባብ ተጠቅመዋል በሚል ክስ በዲሞክራት ፓርቲ አባላት የሚመራው የተወካዮች ምክር ቤት / ኮንግረስ ፕሬዚደንት ትራምፕ ከሥልጣን እንዲወርዱ ትዕዛዝ ሰጠ። ትራምፕ በአሜሪካ ኮንግረስ የተከሰሱ ሶስተኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ሆነዋል ማለት ነው።

አሁን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሴኔት ፊት ቀርበው የቀረበባቸውን ክስ እንዲከላከሉ ይገደዳሉ ማለት ነው።

በጣም የሚገርም ነው፤ በፕሬዝደንት ትራምፕ የምትመራዋ አሜሪካ ፕሬዚደንቶች ከሊንተን፣ ቡሽና ኦባማ ካመጡባት በሽታ በማገገም ላይ ነበረች፤ ነገር ግን በሁለት ፓርቲ ብቻ የምትመራዋ አሜሪካ በምርጫ በተሸነፈው በዲሞክራቲክ ፓርቲው በኩል በጣም አሳፋሪ የሆነ የጥላቻ ዘመቻ በፕሬዚደንቱ ላይ ላለፉት ሁለት ዓመታት ካካሄደ በኋላ ሥልጣኑን ያለምርጫ በአቋራጭ በእጁ ለማስገባት ይሞክራል። ይህ አካሄዳቸው አሜሪካ የውድቀቷ ገደል አፋፍ ላይ እንድትገኝ እያደረጋት ነው።

የሚገርመው ደግሞ እነርሱ ወደ እኛ መጥተው የሃገራችን ፈላጭ ቆራጮች ሲሆኑና፡ የእኛዎቹም እየሞተች ያለችውን ሃያል ሃገር ለእርዳታና ድጋፍ ደጅ ሲጠኑ ማየቱ ነው። ሲ.አይ. / ኤፍ..አይ እና ሌሎቹ የድብቁ ሉሲፈራዊ መንግስት ተቋማት ፈራርሰው የሚወድቁበት ጊዜ ተቃርቦ እያለ እኛ ታዲያ በእግዚአብሔር ፈንታ እነርሱን መለማመጥና መፍራት ይገባናልን?

እስኪ ይህን ቅሌት በጥሞና እናነፃፅረው፤ ለሃገራቸው ብዙ በጎ የሆኑ ሥራዎችን በሁለት ዓመታት ብቻ የሠሩትን ሃገር ወዳዱን ፕሬዚደንት ትራምፕን ያለምንም ማስረጃ ከሥልጣናቸው እንዲወገዱ ለማድረግ እየተሞከረ ነው፤ በሃገራችን ኢትዮጵያ በተመሳሳይ ጊዜ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ታይቶ የማይታወቅ ችግርና ሰቆቃ ያመጣው፣ ከሃዲው፣ ሌባው፣ ቀጣፊው፣ ገዳዩ፣ ሥልጣኑን ያላግባብ በመጠቀም ላይ ያለው ወሮበላው አብዮት አህመድ አሊ በቂ ማስረጃዎች እያሉን ከሥልጣን እንዲወገድ በማድረግ ፈንታ ሽልማቶች ይሰጠዋል። የተገለባበጠች ዓለም!

________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: