ከትናንትና ወዲያ ሙሉ ጨረቃ በታየችበት ኃሙስ/ አርብ፡ በፈረንጆቹ 13 አርብ፤ በዘልማድ ከመጥፎ ዕድል ጋር የተቆራኙ ሁኔታዎች የሚከሰቱበት ዕለት እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል። ስለዚህም በምዕራቡ ዓለም ብዙዎች ከቤታቸው አለመውጣቱን ይመርጣሉ።
ባለፈው አርብ ባቀረክቡት ቪዲዮ ይህን ጽፌ ነበር፦
“እያየን ነው…ጨረቃ አምላኪዎቹ ሙሉ ጨረቃዋን ጠብቀው ሕዝቡን በድጋሚ በተለመደው መተታቸው ሳቡት…በቃ! ሁላችሁም አለቀላቸሁ! ፈረንጆቹ እንኳ፤ “አንዴ ብታሞኘኝ እፍረቱ ባንተ ነዉ፣ ሁለተኛ ብታሞኘኝ እፍረቱ በኔ ነዉ።” (Fool me once, shame on you. Fool me twice, shame on me) ይላሉ። ለአሥረኛ ጊዜ ይህን ያህል መታለል ግን ዘላለማዊ አፍረትን ያለብሳል።”
“ያለምክኒያት በዚሁ ወቅት የዓለም ባንክ ገንዘቡን ሊያጎርፍለት ቃል አልገባለትም፣ ያለምክኒያት በዚሁ ወቅት በዓለ ጥምቀትን አውሬው ዩኔስኮ አልመዘገበውም። ባለፈው ቪዲዮ ላይ፡ አውሬው ዓይኑን በጥምቀት፣ ቍርባንና በተቀሩት ምስጢራተ ቤተክርስቲያን ላይ ማነጣጠሩን አውስቼ ነበር። ያው… እመቤታችንም እየጠቆመችን እኮ ነው...”
ባለፈው ኃሙስ / አርብ ብዙ ትኩረት ልንሰጣቸው የሚገባቸው ሁኔታዎች ተከስተው ነበር። እነዚህ ያለምክኒያት ያልተከሰቱት ሁኔታዎችም፦
- 1ኛ. ሕፃኗ ልጃችን ከእነ ማሕተቧ መወለዷን ሰማን (የጄነራል አሳምነውን የፊት ገፅታ ይዛለች)
- 2ኛ. የጄነራል አሳምነው ገዳይ ቱርኩ ጠቅላይ ሚስትር ግራኝ አብዮት አህመድ የሉሲፈራውያኑን ስጦታ ተቀብሎ ወደ አዲስ አበባ ተመለሰ
- 3ኛ. ቱርክ ቅድመ ዓያት ያለው ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን በብዙ ድምጽ ብልጫ የብሪታኒያን ምርጫ አሸነፈ
- 4ኛ. የአውሬው ዓለም ባንክ ለገዳይ አብይ ሦስት ቢሊየን ዶላር እንደሚሸልም አሳወቀ
- 5ኛ. የአውሬው ሉሲፈር ተቋም ዩኔስኮ በዓለ ጥምቀትን በቅርስነት እንደሚመዘግብ
- 6ኛ. በአውሬው መናኽሪያ በኦሮሚያ ሲዖል በክርስቲያኖች ላይ የአደን ዘመቻ ተከፈተ
…ነጠብጣቦቹን እናገናኝ…
የአርቡን ቪዲዮ እንዳቀረብኩ ቅድስት እመቤታችንና ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል መሄድ ወደ አልተዘጋጀህበት አቅጣጫ መሩኝ። በጨለማማ መንገዱ ሳልፍም ቪዲዮው ላይ የሚታየውና በእግረኛው መንገድ ላይ የተጠራቀመው የዝናብ ውሃ የተለየ ቅርጽ ሠርቶ አገኘሁት። በዓይኔ ወዲያው የመጣልኝ የኢትዮጵያ ካርታና የጥምቀት ፀበል ነው። ብልጭ ያለብኝ “የዮሐንስ ጥምቀት ነው፤ “መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ”[ማቴ ፫፥፩]። መጥምቁ ዮሐንስ ህዝቡን የንስሓ ጥምቀት እያጠመቃቸው ከቆየ በኋላ ጌታ በሚመጣበት ጊዜ ግን እነሆ የእግዚአብሔር በግ በማለት ወደ ጌታ መርቷቸዋል ስለዚህ የዮሐንስ ጥምቀት ምሳሌ ሆኖ ለአማናዊዉ የጌታ ጥምቀት የሚያዘጋጅ መሆኑ ታየኝ።
እናንተስ፤ ምን ይታያችኋል? ከተከስቱት ሁኔታዎች ጋር በተያያዘ ምን ዓይነት መልዕክትስ እያስተላለፈልን ይሆን?