Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 13, 2019
ትክክለኛዋ እምነት በተዓምር፣ በማርያም መቀነት / በቀስተ ደመና የታጀበች እምዬ ኦርቶዶክስ ፥ አድዋ ዘምታ ጊዮርጊስ ድል ያደረገላት፣ መከላከያ ሚንስትሯ ጊዮርጊስ የሆነ፣ ጳጳሳቷ ለአገር የሞቱ፣ አንድነት የምትሰብክ፣ የድኾች መጠጊያ፣ ፀበሏ የሚፈውስ፣ እምነቷ የሚፈውስ፣ ደመራዋ የሚያምር፣ ጥምቀቷ የሚያምር፣ አፅዋማቷ የሚያምሩ፣ ሥርዓቷ፣ መጻሕፍቷ፣ ገዳማቷ፣ ውቅር ዓብያተክርስቲያናቷ፣ የካህናቱ ዝማሬው፣ ቅኔው፣ ማሕሌቱ፣ ቅዳሴው፣ አለባበሳችን ፥ ሁሉ ነገራችን እንደ ኦርቶዶክሶች የሚያምር የለም።
ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡ ወንድማችን!
+______________________________+
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: 666, ሕፃን, መምህር ምህረተአብ, መወለድ, ማህተብ, ማተብ, ተዋሕዶ, ኖቤል ሽልማት, አብይ አህመድ, አውሬው, ኢትዮጵያ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እመነት, የእግዚአብሔር ተዓምር, የክርስቶስ ጠላት, ፀረ-ተዋሕዶ, ፀረ-ክርስቶስ | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 13, 2019
ይህ የተነሳው ከምድራችን በሦስት መቶ ሃምሳ ኪሎሜትር ከፍታ ላይ ከሚገኘውና ዓለማችንን በመዞር ላይ ካለው ከአለም አቀፉ የጠፈር ምርምር መእከል (ISS) ነው። ይህን ቪዲዮ በአጋጣሚ ማታ ላይ ማየቴ ነበር። አስገራሚ ነው…እንዴት እንደገባሁ እንኳን አላውቅም።
ጥሩ ዓይን ያለው/ያላት ወገናችን “ልቡን” ስለጠቆሙኝ፡ ከምስጋና ጋር፡ ተሻሽሎ የቀረበ።
በፈርንጁ ዓለም ዘንድ ሙሉዋ ጨረቃና 13 የሚያርፍበት ዕለተ አርብ ብዙ ፈተና እና መዘዝ ያለው ነው። ያለምክኒያት በዚህ ወቅት የኢትዮጵያን ጠላት ገዳይ አብዮትን አልሸለሙትም፣ ያለምክኒያት በዚሁ ወቅት የዓለም ባንክ ገንዘቡን ሊያጎርፍለት ቃል አልገባለትም፣ ያለምክኒያት በዚሁ ወቅት በዓለ ጥምቀትን አውሬው ዩኔስኮ አልመዘገበውም።
ባለፈው ቪዲዮ ላይ፡ አውሬው ዓይኑን በጥምቀት፣ ቍርባንና በተቀሩት ምስጢራተ ቤተክርስቲያን ላይ ማነጣጠሩን አውስቼ ነበር። ያው… እመቤታችንም እየጠቆመችን እኮ ነው…
በዓታ ለማርያም | መልአኩ ቅዱስ ፋኑኤል ኅብስትና ሰማያዊ ጽዋዕ ይዞ ከሰማይ ወረደ
እንኳን አደረሰን
ቅድስት ድንግል ማርያም በ፶፻፬፻፹፭ ዓመተ ዓለም ከሐና እና ከኢያቄም በፈቃደ እግዚአብሔር ተወልዳ እስከ ሦስት ዓመት ድረስ የኖረችው በወላጆቿ ቤት ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ ኢያቄምና ሐና የተሳሉትን ስእለታቸውን አስታውሰው ወስደው ለቤተ እግዚአብሔር ሰጧት፤ ካህኑ ዘካርያስም ስለምግቧ በመጨነቁ ሕዝቡን ሰብስቦ ሳለ መልአኩ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ይዞ ከሰማይ ወረደ፤ ዘካርያስ ለእርሱ የመጣ ሀብት መስሎት ታጥቆ እጅ ነስቶ ቢቆም ወደ ላይ ራቀበት፡፡ ከስምዖን ጀምሮ በዚያ የተሰበሰቡት ሰዎችም በተራ ቢሞክሩ በተመሳሳይ ወደ ላይ ራቀባቸው፡፡ ምን አልባት ለእንግዶች የመጣ ሀብት እንደሆነ ብለው ሐና እና ኢያቄም እንዲቀርቡ አደረጓቸው፤ ለእነርሱም ራቀባቸው፤ ዘካርያስም ሐናን ‹‹እግዚአብሔር የሚያደርገውን የሚያውቅ የለምና ልጅቷን ትተሸ ወደዚህ ነይ›› ባላት ጊዜ ቅድስት ማርያም ድክ ድክ እያለች እናቷን ስትከተል መልአኩ ፋኑኤል ወደ እርሷ ቀርቦ አንድ ክንፉን አንጥፎ አንድ ክንፉን ጋርዶ መግቧት ዐረገ፤ ሊቀ ካህናቱም ሕዝቡም የምግቧ ነገር ከተያዘልን በቤት እግዚአብሔር ትኑር ብለው አስገብተዋታል፡፡
ድንግል ማርያምም ሰማያዊ ኅብስትና መጠጥ እየተመገበች ፲፪ ዓመት በቤተ መቅደስ ኖረች፡፡ ፲፭ ዓመት ሲሞላት ግን ለአቅመ ሔዋን በመድረሷ ከቤተ መቅደስ ትውጣልን በማለት አይሁድ በጠላትነት ተነሱባት፡፡ ካህኑ ዘካርያስም ይህን ሰምቶ እመቤታችንን ጠየቃት «ኦ ወለተ እስራኤል እፎ ትፈቅዲ ትንበሪ፤ ልጄ እንደምን ሆነሽ ልትኖሪ ትወጂያለሽ?» አላት፡፡ እርሷም «ከእግዚአብሐር በታች ያለኸኝ አባት አንተ ነህ፤ በዚያውም ላይ እናት አባቴ አደራ ያሉህ አንተን ነው፤ ወደ እግዚአብሔር አመልክትልኝ፤» አለችው፡፡ ዘካርያስም ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ከነገደ ይሁዳ ሚስቶቻቸው የሞቱባቸውን በትራቸውን ሰብስበህ በቀዳማይ ሰዓተ ሌሊት ከቤተ መቅደስ አግብተህ ስትጸልይ አድረህ በቀዳማይ ሰዓተ መዓልት አውጣው ብሎ ምልክትም እሳይህአለው ብሎ ነገረው፡፡ እርሱም እንዳለው አድርጎ በማግሥቱ በትሮቹን አውጥተው ቢያዩ የዮሴፍ በትር አብባና አፍርታ ተገኘች፡፡ ከበትሩ ጫፍ ላይ «ኦ ዮሴፍ ወልደ ዳዊት ዕቀባ ለማርያም ፍኅርትከ፤ ዮሴፍ ሆይ እጮኛህ ማርያምን ጠብቃት፤» የሚል ጽሑፍ አገኙ፤ርግብም መጥታ በራሱ ላይ አርፋለች፤ ስለሆነም ዮሴፍ እንዲጠብቃት ተወሰነ፡፡
የኢትዮጵያ ቀለማት / የማርያም መቀነት
የማርያም መቀነት ወርደሽ ንገሪያቸው
ወራሪና ባንዶች ካለ ባህሪያቸው
አይቶ ለመረዳት የታወሩ ናቸው
የኢትዮጵያ ሰንደቅ እኔ ነኝ በያቸው
በሠማዩ ላይ ሲታይ ቀለም
የሷ ነው እንጂ ሌላ አይደለም
+__________________________+
Like this:
Like Loading...
Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል, ሐና, መንኮራኵር, ምድራችን, ቀስተ ደመና, ቅድስት ማርያም, በዓታ ለማርያም, ቤተ መቅደስ, ኢያቄም, ዘካርያስ, የማርያም መቀነት, የኢትዮጵያ ቀለማት, ዮሴፍ, ጠፈር | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 13, 2019
ኢትዮጵያን በቅርቡና በጽኑ የሚመለከት ታሪካዊ ውሳኔ… ከስንት ዓመታት ውጣ ውረድ በኋላ…ይህ ለመጥፎ ዜናዋ ቱርክ መጥፎ ዜና ነው።
በአርመናውያንና በሌሎች ክርስቲያኖች ላይ በጎርጎሮሳዊው 1915 እና 1916 ዓ.ም የተፈፀመው “የዘር ማጥፋት መታሰቢያ” በሚል ያዘጋጁት የውሳኔ ሃሳብ ለአሜሪካ ምክር ቤት/ሰኔት ቀርቦ ውሳኔ እንዲሰጥበት ሲደረግ ይህ የአራተኛው ጊዜ ነበር። አሁን ውሳኔው ጸድቋል።
በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በክርስቶስ ተቃዋሚዋ ቱርክ በተካሄደው የጅምላ ጭፍጨፋ ሁለት ሚሊየን ክርስቲያን አርመኖች ስልታዊ በሆነ መንገድ ተፈጅተዋል። ይህ በተደራጀ ዘመቻ የተካሄደው ጭፍጨፋ የዘር ማጥፋት እንደሆነ አሜሪካ አሁን በይፋ ተቀብለዋለች። ንስሐ መግባት የማትሻዋ ቱርክ ይህን እስካሁን አልተቀበለችውም፤ ሌላ ዕልቂት መፈጸም ትሻለቻና፤ ለምሳሌ በሶርያ፣ በኢራቅ፣ በቱርክ…አዎ! በሃገራችን ኢትዮጵያ።
ከዛሬ አንድ መቶ ዓመት በፊት የተካሄደው የጅምላ ጭፍጨፋ “የዘር ማጥፋት፡ ነው ሲሉ ከ20 በላይ ሃገራት እውቅና ሰጥተዋል። የአርሜኒያ ታሪካዊ ወዳጅ ኢትዮጵያስ? አይይ…አሁን ያለው አውሬ መንግስትማ በክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ላይ ለተመሳሳይ የግፍ ጭፍጨፋ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል፤ ያውም ልክ ቱርክ የተከተለችውን ዓይነት ስልታዊ የሆነ መንገድ በመከተል፤ አርሜኒያ 2.0። ያለምክኒያት አይደለም በዚህ ሳምንት በቂ ኦክስጅን በመሳብ ላይ የሚገኘው ገዳይ አብይ የቱርኩን ፕሬዚደንት ኤርዶጋንን እንደ ምሳሌው አድርጎ የወሰደው።
የኢትዮጵያና አርሜኒያ ታሪካዊ ወንድማማችነት ይለምልም፣ የኢትዮጵያና ሕዝቧ ጠላቶች ይቃጠሉ!
ቀደም ሲል የቀረበ፦
+ “የጂኒው ጃዋር እህት | ቱርኮች ሚሊዮን ክርስቲያን አርመናውያንን መጨፍጨፋቸውን አላወግዝም“+
+ የክርስቲያን ወገኖቻችን እልቂት መታሰቢያ | በቱርኮች ፈንታ አርመኖችና ግሪኮች ወደ አገራችን ይግቡ+
_________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: Antichrist, Armenian Genocide, ቱርክ, አርሜኒያ, አርሜኒያ ጀነሳይድ, ኢትዮጵያ, ኦርቶዶክስ ክርስትና, የአሜሪካ ተወካዮች ምክር ቤት, የክርስቶስ ተቃዋሚ, የክርስቶስ ጠላቶች, ግድያ, ጥላቻ, ጭፍጨፋ, Christian Massacre, Ottoman Turkey | Leave a Comment »