በእንባ የራሰው ፊታችን ሳይደርቅ ገዳይ አብይ በሉሲፈራውያኑ ተሸለመ ብሎ አሸሼ ገዳሜ ማለት በጣም ያሳፍራል
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 12, 2019
የእህታችን የእርቀ ሰላም ሞገስን ፎቶ ሳይ የብዙው ወገናችን ቸልተኝነትና ፍትህ–አልባነት ፊቴ ላይ ድቅን ስለሚል ደሜ ይፈላል።
[መጽሐፈ ኢዮብ ምዕራፍ ፳፮]
፩ ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፤
፪ “ኀይል የሌለውን ምንኛ ረዳኸው!
ደካማውንስ ምንኛ አዳንኸው!
፫ ጥበብ የሌለውን ምንኛ መከርኸው!
ታላቅ ዕውቀትንስ ምንኛ ገለጥህለት!
፬ ይህን ቃል እንድትናገር የረዳህ ማን ነው?
የማንስ መንፈስ በአንደበትህ ተጠቀመ?
፭ “ከውሆችና በውስጣቸው ከሚኖሩ በታች ያሉ፣
የሙታን መንፈስ በጭንቅ ላይ ናቸው።
፮ ሲኦል በእግዚአብሔር ፊት ዕራቍቷን ናት፤
የጥፋትንም ስፍራ የሚጋርድ የለም።
፯ የሰሜንን ሰማይ በሕዋው ላይ ዘረጋው፤
ምድርንም እንዲያው በባዶው ላይ አንጠለጠላት።
፰ ውሆችን በደመናዎቹ ይጠቀልላል፤
ክብደታቸውም ደመናዎቹን አይሸነቍርም።
፱ ደመናዎቹን በላዩ ዘርግቶ፣
የሙሉውን ጨረቃ ፊት ይጋርዳል።
፲ ለብርሃንና ለጨለማ ድንበር ይሆን ዘንድ፣
በውሆች ላይ የአድማስ ክበብ አበጀ።
፲፩ የሰማይ ምሰሶዎች ይንቀጠቀጣሉ፤
በተግሣጹም ይደነግጣሉ።
፲፪ በኀይሉ ባሕርን ያናውጣል፤
በጥበቡም ረዓብን ይቈራርጣል።
፲፫ በእስትንፋሱ ሰማያትን አጠራ፤
እጁም ተወርዋሪውን እባብ ወጋች።
፲፬ እነዚህ የሥራው ዳር ዳር ናቸው፤
ስለ እርሱ የሰማነው ምንኛ አነስተኛ ነው!
የኀይሉንስ ነጐድጓድ ማን ሊያስተውል ይችላል?”
የትዕግስት አባት ፃድቁ ኢዮብ እንደ ጨረቃ ያሉ የሰማይ አካላትን ሲመለከት ልቡ ሸፍቶ ቢሆን ኖሮ፡ እንዲሁም ‘በአፉ እጁን ስሞ’ በሌላ አባባል የጣዖት አምላኪዎች እንደሚያደርጉት እጁን ከሳመ በኋላ ወደ ሰማይ ዘርግቶ ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔርን የካደ ጣዖት አምላኪ ይሆን ነበር።
እያየን ነው…ጨረቃ አምላኪዎቹ የዛሬዋን ሙሉ ጨረቃ ጠብቀው ሕዝቡን ለአሥረኛ ጊዜ በተለመደው መተታቸው ሳቡት…በቃ! ሁላችሁም አለቀላቸሁ! ፈረንጆቹ እንኳ፤ “አንዴ ብታሞኘኝ እፍረቱ ባንተ ነዉ፣ ሁለተኛ ብታሞኘኝ እፍረቱ በኔ ነዉ።” (Fool me once, shame on you. Fool me twice, shame on me) ይላሉ። ለአሥረኛ ጊዜ ይህን ያህል መታለል ግን ዘላለማዊ አፍረትን ያለብሳል።
ታዲያ አሁን አንበጣና በረሮ፣ ረሃብና ጥይት፣ ድርቅና ቸነፈር፣ ዝናቡና በረዶው ቢፈራረቁብን ብሎም እሳት ከላይ ቢወርድብን ያስገርማልን?
የሚከተለው ከመምህር ዘመድኩን በቀለ ገጽ የተወሰደ፦
የአቢቹ ሽልማት ለራሱ ነው። ለአንተ ዳቦ አይሆንህም። ዳቦም አይገዛልህም። የቤት ኪራይም አይከፍልህም። ከታክሲ ወረፋም አያወጣህም። ሰላምም አይሰጥህም። መረጋጋትም አያመጣልህም። ከመታረድም አያድንህም። ከመፈናቀል፣ ከዩኒቨርሲቲ ከመባረርም አያድንህም። እናም ወዳጄ ኳስ በመሬት። አረጋጋው፣ ተረጋጋ። ንስሐ መግባቱንም እንዳትረሳ።
አሁን እሱ ተሸለመ ብሎ አሸሼ ገዳሜ ማለቱ ያሳፍራል፡፡ በአገሬ ደም እየፈሰሰ ሰው እየታረደ ዛሬም አስረሽ ምችው ሆኗል እርግጠኛ ነኝ በኖህ ግዜ እንደዚ የሆነ አይመስለኝም። ሰው እንደከብት ሲታረድ ጡት ሲቆረጥ ቆይ ያስጥመን ግዜ አለን ይመስለኛል እንኳን ጨፍረን ማቅ ለብሰንም የመጣው ባለፈን ብቻ አይናችን እያየ ወደመጠረጉ ልንገባ ነው ሀቁ ይህ ነው። የደማው ልባችን ሳይጠግግለት፣ በሐዘን የተጎሳቆለው ልባችን ሳይበረታ፣ በእንባ የራሰው ፊታችን ሳይደርቅ፣ የወንደሞቻችን እና የእህቶቻችን መኖሪያ ቤቶች እንደፈረሱ ሳይታደሱ፣ ከመኖሪያ ቀዬያቸው ተፈናቅለው በየጥሻው እንደወደቁን፣ በግፍ የታረዱት ወገኖቻችን ምድራዊ ፍትህ ሳያገኙ 86 ነፍሳት እንደዋዛ ተቀጥፈው መንገድ እንደቀሩ፣ ከዛሬ ነገ ይከፋል ብለን በሰቀቀን ሳለን፣ የፈረሰችው መጠለያ ታዛችን አምሳለ እየሩሳሌም ቤተክርስቲያናችን ምላሽ ሳታገኝ፣ በዚህ የሀዘናችን ወቅት ሰላም ነው ስለሰላም ተሸለመ እያሉ ዳንኪራ ይረግጣሉ፤ በየዩኒቨርስቲዮቻችን ጭንቀት መቼ ጋፕ አለናነው ተሸለመ ተብሎ የሚዘለለው፣ አሁንም ሀዘናችን ጽኑ ነውና ቢያንስ ዳንኪራችሁን እዛው በፀበላችሁ በሉልን ቢያንስ እኛ እንዘንበት።
Leave a Reply