Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 11, 2019
ለኢትዮጵያውያን ክብራቸው፣ ኩራታቸውና ደስታቸው ማሕተባቸው እንጂ በደም የተቀባው የኖቤል ሜዳሊያና የአይ.ኤም.ኤፍ ዶላር አይደለም። ከእነ ማሕተቡ መወለድ የበለጠ ፀጋ አለን?
ነፍሳቸውን የሸጡት ሜዲያዎችና እንደ እስስት ተለዋዋጪዎቹ የማሕበራዊ ድህረገጽ ተዋንያዮች ስለ እነ ገዳይ አብይ የቱርክ ድራማ ሌት ተቀን ከመለፈፍ ይልቅ ለራሳቸው ሲሉ ስለ ልጃችን የማሕተብ ተዓምር በማውሳት የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ያለማቋረጥ ማወደስ ቢችሉ ይመረጥ ነበር። ግን አለመታደል ሆኖ አብዛኛዎቹ ሜዲያዎች በአውሬው እጅ ውስጥ ገብተዋል። ስለዚህ፡ ምስክራችን ከላይ ብቻ ነው!!!
የዚህች መልአክ የመሰለች ሕፃን የማሕተብ ተዓምር ዜና የበሰረበት ወቅት ልክ ገዳይ አብይ የኖቤል ሰላም ሽልማቱን ከሚቀበልበት ወቅት ጋር መገናኘቱ ያለምክኒያት አይደለም፤ ሰውየው ከክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ አንዱ እንደሆነ 100% እርግጠኛ ነኝ፤ ስለዚህ፡ በተፈጥሯዊው ማሕተብ በኩል እግዚአብሔር እጅግ በጣም ትልቅ የሆነ መልዕክት እያስተላልፍልን ነው። ጆሮ ያለው ይስማ ፣ ዓይን ያለው ይመልከት፣ ላልደረሰው ያድርስ፡ ለ አስራ ሁለት ሩብ ጉዳይ ሆኗል!
+ ማተብሽን ፍች በጥሽው ቢሉኝ+
እኔስ ከነ አንገቴ ውሰዱት አልኩኝ
ፊተኛ ነንና አንዳንሆን ኋላኛ
ህዝቤ ተነቃቃ ተነስ አትተኛ
ጅብ ከሄደ ውሻ እንዳይሆን ጩኽት
የተዋህዶ ልጆች አሁነ ነው ሰዓቱ
አይተን እንዳላየን ስንቱን አሳልፈናል
የእርሱ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም ብለናል
አሁን ግን ይበቃል ዝምታው ይሰበር
+ይገለጥ ይታወጅ የተዋህዶ ሚስጢር+
ክርስቲያን ማለት ኢትዮጵያ ማለት ነው!
+____________________________+
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: 666, ሕፃን, መወለድ, ማህተብ, ማተብ, ተዋሕዶ, ኖቤል ሽልማት, አብይ አህመድ, አውሬው, ኢትዮጵያ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እመነት, የእግዚአብሔር ተዓምር, የክርስቶስ ጠላት, ፀረ-ተዋሕዶ, ፀረ-ክርስቶስ | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 11, 2019
፪ሺ፲፪ ዓ.ም – ዘመነ ዮሐንስ
[፩ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ ፬፥፳]
“ማንም። እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?”
+_________________________________+
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: መስቀለ ክርስቶስ, መከራ, ምጥ, ሰሜን ኢትዮጵያ, ስንብት, አሲምባ ተራራ, አባ ዘ-ወንጌል, ኢትዮጵያ, የመከራ ዘመን, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 11, 2019
ሰሞኑን አባ ዘ–ወንጌልን በተመለከተ አንዳንድ ሕልሞች ይታዮኝ ነበር። ሕልሞቹን ለማስታወስ እየታገልኩ ነው። አባታችን የጠቆሙን ነገሮች ሁሉ አንድ በአንድ በመፈጸም ላይ ናቸው።
አባታችን አባ ዘ–ወንጌል በአንድ ወቅት እንዲህ ብለውን ነበር፦
“ኢትዮጵያን በዚህ ወቅት እያስተዳደሯት ያሉት ጠላቶቿ ናቸው!”
አዎ! አውሬው ጦርነቱን አስቀድሞ በማካሄድ ላይ ያለው የቤተ ክርስቲያን በር በሆኑት በሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ላይ ነው፦
፩. ምሥጢረ ጥምቀት
፪. ምሥጢረ ሜሮን
፫. ምሥጢረ ቁርባን
፬. ምሥጢረ ክህነት
፭. ምሥጢረ ተክሊል
፮. ምሥጢረ ንስሐ
፯. ምሥጢረ ቀንዲል
መጀመሪያ በቁርባን(ሕብስትና ወይን / ስጋውና ደሙ) ፣ ቀጥሎም በጥምቀት ላይ ነው የዘመቱት። በኢትዮጵያ የእንጀራና ዳቦ መጋገር ባሕል ባልተለመደ መልክ የአሕዛብ ዳቦ ቤቶች በብዛት እየተከፍቱና በየትምህርት ቤቱ ለሕፃናቱ ዳቦና ማርማላታ እያጎረሷቸው መሆናቸውን እንዲሁም ዓብያተ ክርስቲያናት ባሕረ ጥምቀትን በመነጠቅ ላይ መሆናቸውን በግልጽ እያየነው ነው። የሰው ልጅ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ እንደማይችል ምቀኛው ጠላታችን ዲያብሎስ አጠንቅቆ ያውቃልና።
________________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: ማህተብ, ባሕረ ጥምቀት, ቦሌ, ተዋሕዶ, አውሬው መንግስት, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ, የረር, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እመነት, የእግዚአብሔር ተዓምር, የክርስቶስ ጠላት, ፀረ-ተዋሕዶ, ፀረ-ክርስቶስ | Leave a Comment »