ይሄ እንዴት ሊሆን ቻለ? የቄሳርን ለቄሣር?
ይህ በጣም ከሚያሳዝኑኝና ከሚያንገበግቡኝ ጉዳዮች መካከል አንዱ ነው። የአዲስ አበባን ሕፃናት በመመረዝ ላይ ላለው ለታከለ ኡማ መመረዣ ዳቦውን እና ማርመላታውን ይገዛበት ዘንድ ቤተክህነት አስር ሚሊየን ብር መለገሷን ሰምተናል፤ በቤተክርስቲያን ሥር የሚገኙ ሕፃናት ግን በመራብ ላይ ናቸው። እንዴት?
በርካታ ቀዳሚ የኢትዮጵያ ምሁራን መነሻቸው ከአብነት ትምህርት ቤት ነው። የአብነት ትምህርት ከዘመናዊ ትምህርት መስፋፋት ጋር ተያይዞ የወትሮ ሚናውን ማጣቱ ቢስተዋልም፤ አሁንም ጥቂት ለማይባሉ ወጣቶች ምርጫ መሆኑ አልቀረም።
የዕውቀት በርን የሚከፍትላቸውን የቅኔ ትምህርትን በንባብ ቤት፣ ዜማ ቤት፣ አቋቋም ቤት፣ ቅኔ ቤት፣ ቅዳሴ ቤት እና መፃሕፍት ቤት ለመከታተል ሦስት መቶ የቅኔ ተማሪዎች በድንቁ የአቡነ ሀብተ ማርያም ገዳም ይገኛሉ። ይሁንና የትምህርት ቤቶቹ ህልውና ከሚያስተዳድሯቸው ገዳማትና አብያተ ክርስትያናት መድከምና መጠንከር ጋር የተሳሰረ በመሆኑ ለፈተና ሲዳረጉ ይስተዋላሉ። ተተኪ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች በቂ የመተዳደሪያ የገቢ ምንጭ ስለሌላቸውና ከቤተክህነትም እንኳን ምፅዋት ስለማያገኙ አሁን በመቸገር እና በመራብ ላይ ናቸው። አዎ! በአዲስ አበባ፣ ያውም በጣም ሰላማዊና ገነታማ ከሆኑት የከተማዋ ክፍሎች መካከል በአንዱ።