ጽዮን ማርያም | ኢትዮጵያ የከበረችው በመስቀል ነው | መስቀልን የናቁ ተንቀዋል
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 1, 2019
ክርስቶስ ስጋውን የቆረሰውና ደሙን ያፈሰሰው መስቀል ላይ ነው፤ ስለዚህ መስቀሉ ሕይወት የሆነውን ምግብ የተመገብንበት መሶብ ነው፣ መስቀሉ ሕይወት የሆነውን መጠጥ የጠጣንበት ጽዋ ነው።
“ስለ ጽዮን ዝም አልልም” [ኢሳ ፷፪፥፩]
ይህንን የተናገረው ልዑለ ቃል ኢሳይያስ እግዚአብሔር የራቀውን አቅርቦለት የረቀቀውን አጉልቶለት ትንቢት በሚናገርበት ዘመን ሲሆን ጽዮን የሚለው ስም እንደአገባቡ ይፈታል። ጽዮን የሚለው ቃል ኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን መንግስተ ሰማያት ወይም ድንግል ማርያም ቤተመቅደስ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፣ ኢየሩሳሌም ቤተእስራኤል (ቤተ ያዕቆብ) ቤተ መቅደስ ተብሎ የሚፈታበት ጊዜ አለ፣ በሌላ ሥፍራ ደግሞ የቃሉ አገባብ ኢየሩሳሌም ድንግል ማርያም ወይም መስቀል ክርስቶስ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
- ፩ኛ) ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕይው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል
- ፪ኛ) ጽዮን የሚለው ቤተመቅደስን ነው
- ፫ኛ) ጽዮን የሚለው ቃል የሚያመለክተው ክርስቶስ ስለተሰቀለበት ዕፀ መስቀል ነው
- ፬ኛ) የቃል ኪዳኑን ታቦት ጽዮን ይለዋል
- ፭ኛ) “አቤቱ ስለፍርድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት“
- ፮ኛ) ጽዮን የተባለችው ድንግል ማርያም ናት
ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላል በውስጧም ሰው ተወለደ (መዝ ፹፮᎓፭)” እንዲል ቅዱስ ዳዊት የአዳም ዘር ሁሉ እናታችን እመቤታችን እያለ ያመሰግናታል።
፫ኛ) ጽዮን የሚለው ቃል የሚያመለክተው ክርስቶስ ስለተሰቀለበት ዕፀ መስቀል ነው: በመመስገኛው ተራራ በጽዮን እነግሳለሁ ይላልና (መዝ ፪፡፮) መስቀሉን መንግስት አድርጎ በመስቀል ተቅሰሎ ሳለ የመንግስት ሥራ ሠርቷል ጌትነቱን አምላክነቱን አዳኝነቱን ገልጾበታል የመንገስት ሥራ በመስቀል ስለተሠራበት መስቀል ኃይልነ መስቀል ድንዕነ መስቀል ቤዛነ ይባላል መስቀሉንና የተተከለበትን ሥፋራ ደብረ ቀራንዮ ደብረ መቅደሱ የመመስገኛው ተራራ ይላቸው ከዚህ አስቀድሞ ጌታችን ለቤዛ ዓለም ሳይሰቀል በፊት በቀራንዮ ተራራ መላዕክት በቀትር እየመጡ ያመሰግኑ ይቀድሱ ነበር ጌታ በተሰቀለ ጊዜ እንደልማዳቸው ሊያመሰግኑ ቢመጡ ተሰቅሎ ቢያዩት ደንግጠው በመስቀሉ ዙሪያ እነደ ሻሽ ተነጥፈው እንደ ቅጠል ረግፈው “ለከ ኃይል” ኃያል መባል ይገባሀል ኃይል ለአንተ ይሁን “ለከ ጽንእ” ጽኑ ብርቱ መባል ይገባሀል ጽንዓት ብርታት ለአንተ ይሁን እያሉ አመስግነውታል።
እንኳን አደረሰን!
Leave a Reply