ተዓምር በዕለተ ጽዮን | ሰማዩ በኢትዮጵያ የማርያም መቀነት ህብረ ቀለማት ተቀባ
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 1, 2019
ድንቅ ነው፤ አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀለማቱ ወደ ሙሉ ቀይ ከመለወጣቸው በፊት በደንብ ቁልጭ ብለው ይታዩ ነበር፤ ልክ ፀሐይ ስትወጣ ነበር ይህ የታየኝ፤ ካሜራየን እስካወጣ ትንሽ ድብዝዝ አለ ሆኖም ቀለማቱ ይታያሉ፤ ብርሃኑም አለ። ፀሐይ ስትወጣ ነጋ ፥ ጨለማው ጠፋ!
ነቢያት የአምላክን ማዳን ከጠበቁባቸው እና ከገለጡባቸው መንገዶች አንዱ ብርሃን ነው፡፡ ዘመነ ብሉይ መከራ ሥጋ፣ መከራ ነፍስ የፀናበት፣ ሁሉ ነገር አስጨናቂ የሆነበት፣ ሰው ብርሃን ከሆነው አምላክ ጋር የተራራቀበት ስለነበር ያሉበትን ዘመን «ጨለማ» ብለው በመግለጥ ይህንን ጨለማ የሚያስወግድና ወደ ትክክለኛው መንገድ የሚመራ ብርሃን እንዲመጣ እንዲህ እያሉ ይፀልዩ ነበር፡፡ “ብርሃንህንና ጽድቅህን ላክ፤ እነርሱም ይምሩኝ፡፡ አቤቱ ወደ መቅደስህ ተራራና ወደ ማደራያህ ይውሰዱኝ፤” [መዝ. ፵፪፥፫]፡፡ ጌታችንም ወደዚህ ዓለም በመጣ ጊዜ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ” በማለት ለዚህ ጸሎት ምላሽ ሰጥቷል (ዮሐ. ፰፥፲፪)፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ስለ ብርሃንነቱ መስክረዋል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ስለ ጌታችን ሰው መኾን (ምሥጢረ ሥጋዌ) በተናገረበት በወንጌሉ የመጀመሪያ ክፍል ጌታችንን ብርሃን ብሎታል፡፡ ‹‹ሕይወት በእርሱ ነበረ፤ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረ፡፡ ብርሃንም በጨለማ ያበራል፤ ጨለማም አላሰነፈውም፤” [ዮሐ. ፩፥፬–፭]፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ ጌታችን በሚያንጸባርቅ ብርሃን አምሳል እንደ ተገለጠበት ተናግሯል፡፡ “እኩል ቀን በኾነ ጊዜ በመንገድ በሔደ ከፀሐይ ይልቅ የሚበራ መብረቅ በእኔና ከእኔ ጋር ይሔዱ በነበሩት ላይ ከሰማይ ሲያንጸባርቅ አየሁ … አንተ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ አለኝ፤” [ሐዋ. ፳፮፥፲፫]፡፡
በፈርንጆቹ ዘንድ ዛሬ የወሩ መጀመሪያ ታህሣሥ ፩ ነው፤ እነርሱ ከሚያከብሩት የልደት በዓል በፊት ባሉት ሦስቱ የጾመ ነቢያት ሳምንታት የመጀመሪያ ሰንበትና በጨለማማው የክረምት ወር ሻማ የሚያበሩበት ዕለት የሚጀምረው ዛሬ ነው።
ያው እንግዲህ፤ ጌታችን የዓለም ብርሃኑ ምልክቱን እያሳያቸው/ እያሳየን ነው። በማርያም መቀነት ላይ፣ በኢትዮጵያ ቀለማት ላይ ግልጽ የሆነ ጦርነት እየተካሄደ ነው፤ የዚህ ጦርነት ቀስቃሾችም የዲያብሎስ የግብር ልጆች የሆኑት ዔሳውያን (ምዕራባውያን) እና እስማኤላውያን (ምስራቃውያን) ናቸው።
ለሃገራችን ለኢትዮጵያ ሰላምን ለህዝባችን ፍቅር በረከትን ያዉርድልን፡፡ ጽዮን በምልጃዋ ለሁላችንም ትድረስልን!!!
Leave a Reply