Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 1, 2019
ድንቅ ነው፤ አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀለማቱ ወደ ሙሉ ቀይ ከመለወጣቸው በፊት በደንብ ቁልጭ ብለው ይታዩ ነበር፤ ልክ ፀሐይ ስትወጣ ነበር ይህ የታየኝ፤ ካሜራየን እስካወጣ ትንሽ ድብዝዝ አለ ሆኖም ቀለማቱ ይታያሉ፤ ብርሃኑም አለ። ፀሐይ ስትወጣ ነጋ ፥ ጨለማው ጠፋ!
ነቢያት የአምላክን ማዳን ከጠበቁባቸው እና ከገለጡባቸው መንገዶች አንዱ ብርሃን ነው፡፡ ዘመነ ብሉይ መከራ ሥጋ፣ መከራ ነፍስ የፀናበት፣ ሁሉ ነገር አስጨናቂ የሆነበት፣ ሰው ብርሃን ከሆነው አምላክ ጋር የተራራቀበት ስለነበር ያሉበትን ዘመን «ጨለማ» ብለው በመግለጥ ይህንን ጨለማ የሚያስወግድና ወደ ትክክለኛው መንገድ የሚመራ ብርሃን እንዲመጣ እንዲህ እያሉ ይፀልዩ ነበር፡፡ “ብርሃንህንና ጽድቅህን ላክ፤ እነርሱም ይምሩኝ፡፡ አቤቱ ወደ መቅደስህ ተራራና ወደ ማደራያህ ይውሰዱኝ፤” [መዝ. ፵፪፥፫]፡፡ ጌታችንም ወደዚህ ዓለም በመጣ ጊዜ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ” በማለት ለዚህ ጸሎት ምላሽ ሰጥቷል (ዮሐ. ፰፥፲፪)፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ስለ ብርሃንነቱ መስክረዋል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ስለ ጌታችን ሰው መኾን (ምሥጢረ ሥጋዌ) በተናገረበት በወንጌሉ የመጀመሪያ ክፍል ጌታችንን ብርሃን ብሎታል፡፡ ‹‹ሕይወት በእርሱ ነበረ፤ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረ፡፡ ብርሃንም በጨለማ ያበራል፤ ጨለማም አላሰነፈውም፤” [ዮሐ. ፩፥፬–፭]፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ ጌታችን በሚያንጸባርቅ ብርሃን አምሳል እንደ ተገለጠበት ተናግሯል፡፡ “እኩል ቀን በኾነ ጊዜ በመንገድ በሔደ ከፀሐይ ይልቅ የሚበራ መብረቅ በእኔና ከእኔ ጋር ይሔዱ በነበሩት ላይ ከሰማይ ሲያንጸባርቅ አየሁ … አንተ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ አለኝ፤” [ሐዋ. ፳፮፥፲፫]፡፡
በፈርንጆቹ ዘንድ ዛሬ የወሩ መጀመሪያ ታህሣሥ ፩ ነው፤ እነርሱ ከሚያከብሩት የልደት በዓል በፊት ባሉት ሦስቱ የጾመ ነቢያት ሳምንታት የመጀመሪያ ሰንበትና በጨለማማው የክረምት ወር ሻማ የሚያበሩበት ዕለት የሚጀምረው ዛሬ ነው።
ያው እንግዲህ፤ ጌታችን የዓለም ብርሃኑ ምልክቱን እያሳያቸው/ እያሳየን ነው። በማርያም መቀነት ላይ፣ በኢትዮጵያ ቀለማት ላይ ግልጽ የሆነ ጦርነት እየተካሄደ ነው፤ የዚህ ጦርነት ቀስቃሾችም የዲያብሎስ የግብር ልጆች የሆኑት ዔሳውያን (ምዕራባውያን) እና እስማኤላውያን (ምስራቃውያን) ናቸው።
ለሃገራችን ለኢትዮጵያ ሰላምን ለህዝባችን ፍቅር በረከትን ያዉርድልን፡፡ ጽዮን በምልጃዋ ለሁላችንም ትድረስልን!!!
________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: መስቀል, ሰማይ, ቅድስት ማርያም, ብርሃን, ኢትዮጵያ, ኢየሱስ ክርስቶስ, የማርያም መቀነት, የኢትዮጵያ ቀለማት, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, የጌታ ልደት, ገዳም, ጽዮን ማርያም, ጾመ ነብያት, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 1, 2019
ክርስቶስ ስጋውን የቆረሰውና ደሙን ያፈሰሰው መስቀል ላይ ነው፤ ስለዚህ መስቀሉ ሕይወት የሆነውን ምግብ የተመገብንበት መሶብ ነው፣ መስቀሉ ሕይወት የሆነውን መጠጥ የጠጣንበት ጽዋ ነው።
“ስለ ጽዮን ዝም አልልም” [ኢሳ ፷፪፥፩]
ይህንን የተናገረው ልዑለ ቃል ኢሳይያስ እግዚአብሔር የራቀውን አቅርቦለት የረቀቀውን አጉልቶለት ትንቢት በሚናገርበት ዘመን ሲሆን ጽዮን የሚለው ስም እንደአገባቡ ይፈታል። ጽዮን የሚለው ቃል ኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን መንግስተ ሰማያት ወይም ድንግል ማርያም ቤተመቅደስ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፣ ኢየሩሳሌም ቤተእስራኤል (ቤተ ያዕቆብ) ቤተ መቅደስ ተብሎ የሚፈታበት ጊዜ አለ፣ በሌላ ሥፍራ ደግሞ የቃሉ አገባብ ኢየሩሳሌም ድንግል ማርያም ወይም መስቀል ክርስቶስ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።
- ፩ኛ) ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕይው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል
- ፪ኛ) ጽዮን የሚለው ቤተመቅደስን ነው
- ፫ኛ) ጽዮን የሚለው ቃል የሚያመለክተው ክርስቶስ ስለተሰቀለበት ዕፀ መስቀል ነው
- ፬ኛ) የቃል ኪዳኑን ታቦት ጽዮን ይለዋል
- ፭ኛ) “አቤቱ ስለፍርድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት“
- ፮ኛ) ጽዮን የተባለችው ድንግል ማርያም ናት
ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላል በውስጧም ሰው ተወለደ (መዝ ፹፮᎓፭)” እንዲል ቅዱስ ዳዊት የአዳም ዘር ሁሉ እናታችን እመቤታችን እያለ ያመሰግናታል።
፫ኛ) ጽዮን የሚለው ቃል የሚያመለክተው ክርስቶስ ስለተሰቀለበት ዕፀ መስቀል ነው: በመመስገኛው ተራራ በጽዮን እነግሳለሁ ይላልና (መዝ ፪፡፮) መስቀሉን መንግስት አድርጎ በመስቀል ተቅሰሎ ሳለ የመንግስት ሥራ ሠርቷል ጌትነቱን አምላክነቱን አዳኝነቱን ገልጾበታል የመንገስት ሥራ በመስቀል ስለተሠራበት መስቀል ኃይልነ መስቀል ድንዕነ መስቀል ቤዛነ ይባላል መስቀሉንና የተተከለበትን ሥፋራ ደብረ ቀራንዮ ደብረ መቅደሱ የመመስገኛው ተራራ ይላቸው ከዚህ አስቀድሞ ጌታችን ለቤዛ ዓለም ሳይሰቀል በፊት በቀራንዮ ተራራ መላዕክት በቀትር እየመጡ ያመሰግኑ ይቀድሱ ነበር ጌታ በተሰቀለ ጊዜ እንደልማዳቸው ሊያመሰግኑ ቢመጡ ተሰቅሎ ቢያዩት ደንግጠው በመስቀሉ ዙሪያ እነደ ሻሽ ተነጥፈው እንደ ቅጠል ረግፈው “ለከ ኃይል” ኃያል መባል ይገባሀል ኃይል ለአንተ ይሁን “ለከ ጽንእ” ጽኑ ብርቱ መባል ይገባሀል ጽንዓት ብርታት ለአንተ ይሁን እያሉ አመስግነውታል።
እንኳን አደረሰን!
______________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: መስቀል, ቅድስት ማርያም, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ, ኢየሱስ ክርስቶስ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ገዳም, ጽዮን ማርያም, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith | Leave a Comment »