የክርስትና አርበኛው ቦብ የሚከተሉትን ተናግሮ ነበር፦
የአፍሪቃ ጣዖታዊ አምልኮን (ዋቀፌና) ከ ጥቁር ሕዝብ ማንነት ጋር ለማጣመር የምትሞክሩ፤ (እራሳቸውን “ኩሽ” ወይም ሄብሪው እስራኤላይትስ” ብለው የሚጠሩት ግብዞች) ኢትዮጵያና ግብጽ (ኮፕት) የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች መሆናቸውን ልታውቁት ይገባል።
አረብ–ሙስሊሞች የሙስሊሞች ያልሆኑትን አፍሪቃውያን ሃገራት በመውረርና ሕዝቦቹም እስልምናን በግድ እንዲቀበሉ በማስገደድ የአፍሪቃ ቤተክርስቲያን በሰሜን አፍሪቃ አጥፍተዋታ
በግብጽና በኢትዮጵያ ብቻ ነው ክርስትናን ሊያሸነፉ ያልቻሉት። በተለይ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያናዊ ማንነታቸውን ለመጠበቅ ሲሉ ብዙ የእስልምና ጂሃዳዊ ወረራዎችን ለመመከት በቅተዋል።
ዛሬ አዲስ እስላማዊ ጂሃድ በኢትዮጵያ ላይ ተጀመሯል፤ ስለዚህ ጉዳይ መላው ዓለም ማወቅና መመከት ይኖርበታል።
እስላማዊ የባርነት ንግድ በአፍሪቃ ዛሬም እየተካሄደ ነው፤ ጥቁር ሕፃናት በባርነት እየተሸጡ ነው፤
ይህንንም ጉዳይ መላው ዓለም ማወቅና መከልከል ይኖርበታል።
እኔ እንደ አንድ ፈረንጅ፡ ክርስትና የአውሮፓም የአፍሪቃም ነው ብዬ በእርገጠኝነት ቆሜ ልመሰክር እችላለሁ።
ክርስትና እንደ አውሮፓውያን ሃይማኖት ተደርጎ የሚታይበት ምክኒያት፤ አውሮፓውያን ኃይል ስለነበራቸው የእስልምናን ወረራ በመመከት ክርስትናን ሊከላከሉ በመቻላቸው ነው። አብዛኞች አፍሪቃውያን ግን ይህ አልተቻላቸውም።
በአውሮፓ ክርስትና የዳበረው ከኃይል ቦታ ሲሆን በግብጽ ግን ከአድሎ ወይም ከበደል በመነሳት ነው።
ነገር ግን በኢትዮጵያ ክርስትና ተለይቶ ለመዳበርና ለመጠንከር የበቃው የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ኃያል ስለነበሩ ነው።
የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች ለ፪ሺ ዓመታት ያህል የሕዝባቸውን ዕጣ ፈንታና ሕይወት በራሳቸው
አመራር ለመወሰን የበቁ ብቸኛ አፍሪቃውያን ናቸው።
የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች የእስልምናን የወረራ ጂሃድና የቅኝ ገዢዎችን ሠራዊት ለመቋቋም የበቁ ብቸኛ አፍሪቃውያን ናቸው።
በ፲፭ ኛው ክፍለዘመን የፖርቱጋሎች ክርስቲያን ሠራዊት ከኢትዮጵያ ክርስቲያን ወገኖቹ ጋር በመሰለፍ ወራሪ እስላሞችን ድል ነስተዋቸዋል።
ፖርቱጋሎቹ ከኢትዮጵያ ወንድሞቹ እና እህቶቹ ጋር አብሮ ሲሰለፍ በክርስቲያናዊ ወንድማማችነት መንፈስ ነበር። በዚያ ዘመን በክርስቲያኖች ዘንድ ዘርና የቆዳ ቀለም ምንም ዓይነት ሚና አልተጫወቱም።
ጥቁርና ነጭ ክርስቲያን ሕዝቦች በአንድ ላይ አብረው የአረብ ኢምፔሪያሊዝምን፣ የአረብ ባርነት ቀንበርን እና እስልምናን አሸንፈዋል።
ክርስትና የአፍሪቃ እምነት ነው!!!