Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • November 2019
    M T W T F S S
     123
    45678910
    11121314151617
    18192021222324
    252627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for November 16th, 2019

ቱርክ ኢትዮጵያን ለመውረር በሱዳን፣ በጂቡቲ እና በሶማሊያ በኩል እየተዘጋጀች ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 16, 2019

በሕዝበ ክርስቲያኑ ላይ እየተካሄደ ያለው የጭፍጨፋና የዘር ማጥፋት ዘመቻው በሐረርጌ መጧጧፉ ሊያስገርመን ይገባልን? ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት እኮ ግራኝ አህመድም የጥፋት ጂሃዱን ከሐረርጌ ነበር የጀመረው።

እኛ እርስበርስ ስንባላ የግራኝ አህመድ አባት ቀንደኛው አውሬ ጠላታችን ሊበላን ተዘጋጅቷል። ከሁሉም አየር መንገዶች ርካሽ የበረራ ቲኬትን የሚሸጠው የቱርክ አየር መንገድ ወደ አዲስ አበባ በየቀኑ በመብረር ላይ ይገኛል። አውሮፕላኖቹ ለክርስቲያን ኢትዮጵያውያኖች መጨፍጨፊያ የጦር መሳሪያዎችን እና መበከያ መርዞችን እንደሚሸከሙ ማን ይቆጣጠራቸዋል? በአሁኑ ሰዓት ማንም!

የሚከተለውን ከወር በፊት በጦማሬ ላይ ይህን ጽፌ ነበር፦

የክርስቶስ ተቃዋሚዋ ሃገር ቱርክ ግራኝ አብዮት አህመድ ለፀረኢትዮጵያና ፀረክርስቶስ ዘመቻው በአርአያነት የመረጣት ሃገር ነች። ቱርክ በአሁኑ ሰዓት በሰሜን ሶርያ የሚኖሩትን የመጨረሻዎቹን ክርስቲያን ወገኖቻችንን በቦምብ በመጨፍጨፍ ላይ ትገኛለች። በዚሁ አካባቢ በኩርዶችና በአሜሪካውያን ታስረው የነበሩት አንድ ሺህ የሚጠጉ የአይ ኤስ እስላማዊ ጅሃዲስቶች ከቱርክ የከለላ ድጋፍ በማግኘት ከእስር ማምለጣቸው ታውቋል። ታዲያ አሁን ግራኝ አብዮት አህመድ እነዚህን ጅሃዲስቶች በተቸገሩ ለማኞች መልክ ወደ አዲስ አበባ በማምጣት ለፀረተዋሕዶ እና ፀረኢትዮጵያ ዘመቻው ሊጠቀምባቸው እንደሚሻ መጠበቅ ይኖርብናል። እንደተለመደው “እኔ አላየሁም አልሰማሁም! እኔ አይደለሁም፤ እኔ ለሰላም እየታገልኩ ነው፤ አታዩም፤ አለም ሁሉ አድንቆኛል፤ የሰላም ሽልማቱንም አበርክቶልኛል፤ ኢትዮጵያን የሚበጠብጡት አልሸባብ፣ አልኬይዳና አይ ኤስ ናቸው” ሊለን ተዘጋጅቷል።

እናስታውስ፡ ገዳይ ግራኝ አብዮት እንደ አርአያና ምሳሌ አድርጎ የወሰዳት ቱርክ ናት፤ ለመሪነት ምሳሌውም አምባገነን ፕሬዚደንቷ ጣይፕ ኤርዶጋን ነው።

ኃያሉ እግዚአብሔር በቱርክ፣ በኤርዶጋን፣ በግራኝ አብዮት እና በሌሎች ጠላቶቻችን እንዲሁም በአራት ኪሎ አህዛብ ቤተመንግስት ላይ እሳቱን ያውርድባቸው!!!


Turkey is Supplying Weapons to Nigeria’s Boko Haram

Turkey is clearly a terrorist state with a broad reach, according to an Egyptian television news program.

Ten.tv reports Turkey is supplying weapons to Boko Haram in Nigeria.

Ten.tv host Nasha’t al-Deyhi reported on a leak confirming an intercepted phone call from a few years back – confirming the action.

He reported in part: “Today’s leak confirms without a doubt that Erdogan, his state, his government, and his party are transferring weapons from Turkey to – this is a shock, to where you may ask – to Nigeria; and to whom? – to the Boko Haram organization.”

Raymond Ibrahim is the Shillman Fellow in Journalism at the David Horowitz Freedom Center and an expert on the Middle East and Islam. During an interview Thursday on CBN’s Newswatch, Ibrahim said he’s not surprised by the Ten.tv report.

“The tape was made in 2014 or 15 and it was reported widely in certain areas, in the US and the west not so much and not much came out of it,” Ibrahim said. “The reason I think is that (Turkish President Recep Tayyip) Erdogan didn’t have his fingers so much in Islamist politics outside of his own nation.”

“But now that we’ve seen Abu Bakr al-Baghdadi, the ISIS Islamic state caliph that was killed recently, and he was found just three miles from the Turkish border, which is, in fact, the last bastion of jihadi-so-called ‘freedom fighters’ attacking the Syrian government,” he told CBN News.

“It has brought it up again, he (Erdogan) is supporting ISIS,” Ibrahim noted. “Now we’re remembering and that was I think the point of the Egyptian show, we’re bringing back to see that there’s some continuity here. He’s involved with some of the worst Islamic terror groups. If you remember, Boko Haram, whose name loosely means ‘western education is forbidden’, (Haram) was basically doing what ISIS was doing and is notorious for – years before ISIS was doing it.

“One of the things international observers have been noticing, especially increasingly, is that their armaments, their weapons are very sophisticated,” he continued. “It’s even spilled into the Fulani tribesmen in Nigeria and other parts of Africa. For example, in Burkina Faso, also in western Africa the attacks on Christians have become horrific in just the last few months.”

As CBN News reported, a senior State Department official said last week that Turkey is backing forces in Syria who have the same radical ideology as ISIS.

“The problem is that the people doing the fighting are these ill-disciplined Arab militias, some of whom we’ve worked within the past when we were arming the opposition, but many of whom are (a) ill-disciplined, and (b) relatively radical, and their ideology is essentially Islamic ideology,” the official said.

A fragile government in northern Syria called the Democratic Autonomous Administration of North and East Syria (DAA) released a statement on Tuesday saying that Erdogan seeks to subjugate them through radical Islam.

“Erdogan plans to turn are free, democratic region back into turmoil under radical Islamic occupation,” the government said.

Critics of Erdogan’s invasion say he is trying to revive the Ottoman Empire and establish a new caliphate.

“Their open intention is to restore the original caliphate which was disbanded in 1924,” said Dalton Thomas of Frontier Alliance International.

Recently Turkey’s defense minister posted a map to his social media that shows portions of Greece, Syria, and Iraq as part of a greater Turkey.

Defense Minister Hulusi Akar posted a message alongside the map: “We have no eyes on anyone’s soil. We will only take what’s ours.”

The map reflects the 1920 Ottoman National Pact that includes lands Turkey believes it deserved at the end of World War I.

Source

________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አቡነ ሰላማ | ኢትዮጵያ የገጠማትን ፈተና ያመጣው ዲያብሎስ ሰይጣን ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 16, 2019

ከምስጋና ጋር፡ መምህር ዘመድኩን ደግሞ የሚከተለውን አካፍሎናል፦

ስደት ወደ አዲስ አበባ ተጀምሯል

ከኢትዮጵያዋ ሶሪያ የአሁኗ ( ኦሮሚያ አሌፖ ) የዐማራ ነገድ በዘራችሁ ያለና ከዐማራ ክልል የመጣችሁ፣ የትምህርት ሚንስትር የመደባችሁ ተማሪዎች ከኦሮሚያ ዩኒቨርሲቲ ለቃችሁ ውጡልን ተብለው ፖሊስ እያየ፣ መከላከያም እየተመለከተ አልሸባብ ቄሮ ያባረረቻቸውን የኢትዮጵያ የዐማራ ስደተኛ ተማሪዎች ወደ አዲስ አበባ አሁን ምሽቱን መግባት ጀምረዋል።

5 አውቶቡስ የተሳፈሩ በቁጥር 250 የሚሆኑ

ከጅማና ከአምቦ እንዲወጡ የተደረጉ የመጀመሪያዎቹ የዐማራ ስደተኛ ተማሪዎች ዛሬ ምሽት 2:00 ሰዓት ላይ አዲስ አበባ ከተማ ገብተዋል። በመርካቶ አውቶቡስ ተራ በሚገኘው አዲሱ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያንም ተጠልለዋል። የአጥቢያው ምዕመናን፣ የደብሩ ካህናትና ዲያቆናት እንዲሁም የሰንበት ተማሪዎችም ስደተኛ የዐማራ ተማሪዎችን ተቀብለው ራት አብልተው በደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ አሳድረዋቸዋል።

የአዲሱ ሚካኤል ምእመናን ለስደተኞቹ ምግቡን፣ እንጀራውን ከየቤታቸው በማዋጣት፣ በርበሬና ጨው ሽሮም በማምጣት እዚያው በቤተ ክርስቲያኑ ጊቢ ውስጥ እያዘጋጁና እየሠሩ ነው ስደተኞቹን ተማሪዎችን እየመገቡዋቸው የሚገኙት። የአዲሱ ሚካኤል አጥቢያ የተዋሕዶ ልጆች ስደተኛ ተማሪዎቹን ተራ ገብተው በመጠበቅም ላይም ይገኛሉ።

እነዚህ ዛሬ ከጅማና ከአምቦ የመጡት ተማሪዎች ኢንተርቪያቸውን እንደሰማሁት ከሆነ የአምቦ ከተማ ህዝብ ምንም ዓይነት በደል እንዳላደረሰባቸው፣ የሸዋ ኦሮሞ አቅፎ እንደያዛቸው፣ ነገር ግን እስላም ኦሮሞዎቹ፣ የባሌ፣ የአሩሲና የጅማዎቹ ዐማራ ሲያዩ እንደ አበደ ውሻ እንደሚያደርጋቸው፣ የወለጋዎቹ ደግሞ ፌሮና ድንጋይ አጣና ይዘው ተማሪ ብቻ ሳይሆን እረፉ የሚሏቸውን የመከላከያ ሠራዊት አባላት ካልደበደብን እያሉ እንደሚገለገሉ ነው የሚናገሩት።

አስገድዶ መድፈርና ጠለፋውም ለጉድ ነው ይላሉ ተማሪዎቹ። መዳ ወላቡ፣ ድሬደዋና ናዝሬት በጭንቅ ላይ ናቸው። ድሬደዋ አንዷን ተማሪ አስገድደው ከደፈሯት በኋላ የዩኒቨርሲቲው ኃላፊ ምስጢር እንዳይወጣ ይዟት ወጥቶ የት እንዳደረሳት አይታወቅም ይላሉ ተማሪዎቹ። ሐረር ሆስፒታል የገቡ ተማሪዎች አሉ። ደምቢዶሎ የዐማራ ተማሪ መግደል እንደ ጽድቅ ይቆጠራል። የዛሬዋ ኢትዮጵያ ለኦርቶዶክስና መታወቂያው ዐማራ ለሆነ ሙስሊም ይሁን ጴንጤ ኦሮሚያ የምድር ሲዖል ሆናበታለች።

እንደኔ እንደኔ ዘንድሮ የዩኒቨርሲቲ ትምህርት ቢቀር ይሻላል ባይ ነኝ። ጠቅላይ ሚንስትሩ በሪፐብሊካን ጋርድ እየተጠበቀ አራት ኪሎ ተቀምጦ አንደሞዴል ተቀባብቶ፣ እንደ አክተር የሚያነበንበውን መነባንብ ወደ ጎን ትቶ የተማሪዎች ህይወት ሳይጠፋ በሰላም ሀገሪቷ መንግሥት እስኪኖራት ቢዘጋ መልካም ነው። እንዲያ ቢሆን የሰላም ኖቤል ሽልማቱም ትክክለኛውን ስፍራ ያገኝ ነበር።

የሚገርመው ነገር ኦሮሚኛ የሚናገሩ ነገር ግን መታወቂያቸው ዐማራ የሆኑ በሙሉ ናቸው የተባረሩት። አባራሪው እኮ ዩኒቨርሲቲው አይደለም። አባራሪው ወታደሩ አይደለም። አባራሪው የኦነግ ቄሮ ነው። መከላከያውማ የወለጋው ኦነግ ኦቦ ለማ መገርሳ አርፈህ ተቀመጥ ስላለው ከተማሪው ጋር አብሮ ያለቅሳል። ትእዛዝ አልተሰጠን ምን እንርዳችሁ ይላቸዋል። ሲያሳዝን መከላከያ።

በዐማራ ክልል የተመደቡ የኦሮሞ ተማሪዎች ይውጡልን ነው የሚሉት አሉ እነዚህ የአህመዲን ጀበልና የጃዋር አህመድ ቡችሎች። በዐማራ ክልል የተመደቡ የኦሮሞ ልጆች ደግሞ በጎንደር ጸሎት ላይ ናቸው። በባህርዳር ጣና ሀይቅ ዳር ዘና፣ ፈታ ብለው እያጠኑ ነው። ማርቆስ ደብረታቦር ዓለማቸውን እየቀጩ ነው። ወልድያም ፀቡ ህዝቡን የሚመለከት አይደለም። ደሴ ኮምቦልቻም የከሚሴ ኦነግና የወለጋ ቄሮ ለመበጥበጥ ቢሞክሩም እስከ አሁን አልተሳካም። ዐማራ ክልል ያሉ ኦሮሞዎች እንውጣ፣ ተበድለናል ሳይሉ የኦሮሚያ ቀሬናቄሮ በግድ ካልወጡ ማለት የጤና አይመስልም። ይሄ ምቀኝነት ነው። የዐማራ ህዝብ ግን አንዲት ነገር በደጅህ ኮሽ እንዳትል። ኬላዎችን፣ መግቢያ መውጪያ በሮችን በዐይነቁራኛ ጠብቅ። ጠብቅ ነቅተህ። ተንከባክበህ ያዝ ። አንድም ተማሪ እንዳታስከፋ። ወዳጄ ፍቅር ያሸንፋልን በተግባር አሳይ። ያኔ ታሸንፋለህ። ምክሬ ነው።

ለማንኛውም አዲስ አበባ ስደተኞችን ተቀብለሽ አስተናግጂ፣ አብዛኛዎቹ ሻወር ያልወሰዱ፣ ልብስ የሌላቸው፣ የተራቡም ጭምር ናቸው። እናም ነግ በእኔ ነውና አስተናግዷቸው። የሴቶችን ገመና ለመሸፈን ከሴቶች በላይ የሚያውቅ የለምና ጎብኟቸው። የትራንስፖርት አዋጥታችሁ ሸኟቸው። አደራ፣ አደራ፣ አደራ፣

አቢቹ ቅድም ሲበጠረቅ ሰምቼው በሳቅ ስፈርስ ነበር። ያለ በቂ ጥናት አጥር እንኳን የሌላቸውን በገጠር የሚገኙ የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎችን ኮምፒዩተራይዝድ የአሻራ መለያ ቴክኖሎጂ መግቢያ በራቸው ላይ እንዲገጠምላቸው ይደረጋል፡፡አለልኛ አባ መበጥረቅ፣ የእኔ ቀዳዳ። ጉድ እኮ ነው። ዩኒቨርሲቲዎቹ መጀመሪያ በር ሲኖራቸው አይደል እንዴ ፓስተርዬ። ወይስ አጠገባችን ያለውን ነካ አድርገን በቃ ከነገ ጀምሮ ዩኒቨርሲቲዎቻችን አጥር በአጥር ይሆናሉ እንበል? አንተን ቶሎሳን ሳይሆን አንተን ነበር “ አፍራሽ ” ማለት። አፍራሽ !! ሃሌሉያ !!

አቡነ ሰላማ – ርግብ – በሃገር ስደት

[ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፵፰፥፳፰]

እናንተ በሞዓብ የምትኖሩ ሆይ፥ ከተሞችን ትታችሁ በዓለት ውስጥ ተቀመጡ፥ በገደል አፋፍም ቤትዋን እንደምትሠራ እንደ ርግብ ሁኑ።”

________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | 1 Comment »

 
%d bloggers like this: