Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • November 2019
    M T W T F S S
     123
    45678910
    11121314151617
    18192021222324
    252627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for November 15th, 2019

ጂሃድ በግብጽ | ኮፕት እህታችንን ዋና መንገድ ላይ፡ በጠራራ ፀሐይ “አላህ ዋክባር!” እያሉ ደፈሯት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 15, 2019

ምስኪኗ ኮፕት ለእርዳታ ስትጮህ ትሰማለች። ደፋሪዎቿን ወደ ሲዖል ያውርዳቸው!

ሙስሊሞች የሚኖሩት ለመብላት፣ ወሲብ ለመፈጸም እና ለመግደል ብቻ ነው፤ ልክ እንደ እንስሶች። ይህ ነው መሀመድና ጋኔኑ ጂብሪል የፈጠሩት ትክክለኛው እስልምና፤ ሲደፍሩ “አላህ ዋክበር!” ቤተክርስቲያን ሲያቃጥሉ “አላህ ዋክበር!” ማህተብ ሲበጥሱ “አላህ ዋክበር!” ፣ ሲገድሉ “አላህ ዋክበር!”። አላህ ሰይጣን ነው!

____________Ö______________

Posted in Ethiopia, Faith, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , | 1 Comment »

ኤዲያ! መንግስት አለ ይለኛል ገዳይ ለማኝ ሁላ ፊት ለፊቱ እያየ እጅ እግሩ ተቆርጦ ወገኑ ሲቀላ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 15, 2019

ነፍስሽን በገነት ያኑረው፡ እናትየ!!!

ቀሲስ አስተርአየ ጽጌ ለፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ከላኩት መልዕክት የተወሰደ፦

ብጹዕ ወቅዱስ ሆይ!

ቋሚ ሰው ለሞተ ወገኑ “በረደህ ላልብስህ፡ ዘቀዘቀህ ላንተርስህ፤ ራበህ ላጉርስህ፤ አይልም። የሚሰጠው እንባ ብቻ ነው። በመንበረዎ ተቀምጠው በአረመኔወች ለታረዱ ልጆቼዎ የሰጧቸውን እንባ ተመለከትኩ።

ከቅኔው ቆጠራ ብንን ብየ ራቡ ሲሰማኝ፤ ከደጃፍ ቁሜ በእንተ ስማ ለማርያም ስል ድምጼን ሰምታ ደረቷን እየደቃች እኔን ይራበኝ እያለች ከልጆቿ ሳትለይ ያስተማረችኝ ርኅሪት እናት መታረዷን ስሰማ፤ ከመንደር እስክወጣ ድረስ ተናካሽ ውሻውን እየተከላከለልኝ “ተሜ አይዞህ በርትተህ ተማር” እያለ ያስተማረኝ አባ ወራ ጭንቀቱን መከራውን ከባህር ማዶ ሆኜ ስሰማ እኔም ቅዱስነተዎ ያነቡትን እንባ ተጋራሁ።

ለቅዱስነተዎ አላቃሽም አነጋጋሪም አጽናኝም ብጹአን አቡኖች በአካባቢዎ አሉሉዎ። ከውቅያኖስ ማዶ ላለሁት ለኔ ግን በደስታም ሆነ ይህን በመሰለ አሰቃቂ ዘመን በመጻህፍቶቻቸው አማካይነት የከበቡኝ አማካሪወቼና የሚያጽናኑኝ እነ ቅዱስ ጳውሎስ፤ እነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፤ እነ ቅዱስ ቄርሎስና በዝክረ ሊቃውንት መጽሐፋቸው እነ መላከ ብርሃን አድማሱ ጀንበሬ ብቻ ናቸው።

የገጠመን ጠላት “ብእሲ አብድ ይጠፍዕ እዴሁ ወይትሀሰይ ለርእሱ እንዘ ይትሀበይ ሕቢተ ለዓርኩ፤ መፍቀሬ ጋእዝ ይትፌሳህ በባእስ ወጽኑዕ በቅፈተ ልብ ኢይዳደቅ ሠናየ” (ምሳሌ 1718። ማለትም፦ በኃጢአት ስካር ነፍዞ፤ በሚፈጽመው በደልና ግፍ ደምብዞ፤ በገደለው ሬሳ ላይ ቆሞ የሚያጨበጭብ እጅግ ጨካኝ አረመኔ ነው። ኃጢአት ባደነደነው ልቡ እርሱ በርሱ እየተጔተተ ዋስና ምስክር እየሆነ በመደጋገፍ በግፍ ላይ ግፍ በበደል ላይ በደል በመፈጸም ላይ እስካሁን ባደረገው ተጸጽቶ የማይመለስ የኢትዮጵያን ህዝብ ጨርሶ የሚያጠፋ ነው።

የፈሰሰው ደም ያለፍርድ ተደብስብሶ ቢታለፍ፤ የበለጠ መቅሰፍት አስከትሎ በህዝብ ደም ከዳር እስከዳር ኢትዮጵያን አኬልዳማ ስለሚያደርጋት ለቤተ ክርስቲያን ያላት አማራጭ ቁጭ ብላ በማልቀስ ብቻ ሳትወሰን፤ ድምጿን ከቤተ መቅደስ ውጭ አውጥታ ለአምላክና ለዓለም እያሰማች፤ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በነበረበት ቀውጢ ሰአት ያደረውን ማድረግ ይኖርብናል።

በሕግ አንጻር የቤተ ክርስቲያናችን አቋም

የአብነቱ መምህራን አባቶቻችን ባንድምታው እንዳስተማሩን፤ ያንድ አገር መንግሥት እራሱ በህዝቡ ላይ በሚፈጽመው በደልና ጭቆና ራሱን አይክሰስ እንጅ፤ እያወቀም ሆነ ሳያውቅ በመንግሥቱ ከለላ ያሉትን ወገኖች የሚያስደበድብ የሚያስፈጅ ከሆነ፤ ቤተ ክርስቲያናችን በመበደል ያለውን ወገኗን ወክላ “በህግ ልትፈርድ በመንበር ላይ ተቀምጠህ ሳለህ ያለ ህግ ስላስመታኀኝ የተለሰንክ ግድግዳ ነህ”የሐዋ 233። ብላ መንግሥትን የመፋለም መብት አላት። ግዴታም አለባት።

ክፉ የሚሰሩትን ሰዎች የሚፈራና በክፉ አድራጊዎች የተናቀ መንግሥት በኢትዮጵያ መኖር እንደሌለበት ቤተ ክርስቲያናችን በድፍረት ባትናገር ያመራር ችግር ገጥሟታል ማለት ነው (ሮሜ 133። በደካማ መንግሥት ንዝህላልነትም ሆነ በሸረኝነት በመታረድ ላይ ያለውን ወገኗን ቤተ ክርስቲያናችን ወክላ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ”ሞት የሚገባውን ነገር አድርጌ ከሆነ ከሞት ልዳን አልልም” (የሐዋ 2511እያለች ድምጿን ከፍ አድርጋ መናገር አለባት።

ቅዱስ ጳውሎስ “የቀረበብኝ ክስ ከንቱ እንደሆነ እየታወቀ ለገዳዮች አሳልፎ ይሰጠኝ ዘንድ ማንም አይችልም” ብሎ ወደ ቄሣር ይግባኝ ብያለሁ እንዳለ፤ ጠቅላይ ምንስቴር ዓቢይ በደል የፈጸመውን ጁዋርን ወደ ህግ ለማቅረብ ባንድም ሆነ በብዙ ምክንያት ከፈሩ ወይም አቅም ካነሳቸው፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለዓለም ይግባኝ እንድትል የህግ ምሁሩ የቅዱስ ጳውሎስ መርሆ በምሳሌነቱ ያስገድዳታል።

ጠቅላይ ምንስቴር ዓቢይ ጁዋርን በህግ ፊት ማቅረብ ሲገባቸው፤ የተፈጸመውን ወንጀል አደበስብሰው፤ የገዳዩንና የተገዳዩ ቁጥር በማይታመንና በማይመጥን ቀመር አካክሰውና አወራርደው በማቅረባቸው፤ ለተፈጸመው በደል ተጠያቂ አልባ አድርገውታል። ገዳይንም ተገዳይንም ደርበው በመክሰሳቸው የተፈጸመውን በደል ተጠያቂ አልባ ከማድረጋቸው ባሻገር፤ በህዝብና በህግ ላይ እጽፍ ድርብ ደባ ፈጽመዋል ብላ ቤተ ክርስቲያን ያላንዳች ማቅማማት የመገሰጽና የመክሰስ መብቷን ልትጠቀም ይገባታል።

ጠቅላይ ምንስቴሩ በመንግስታቸው ሰወች መገደላቸውን መስክረዋል፤ ተገዳይ እንዳለ ካመኑ ገዳይና አስገዳይ እንዳለ ግልጽ ነው። የፈሰሰው ንጹህ ደም ያለፍርድ ተደብስብሶ ቢታለፍ፤ የበለጠ መቅሰፍት አስከትሎ በህዝብ ደም ኢትዮጵያ ከዳር እስከዳር አኬልዳማ ከመሆኗ በፊት፤ ቤተ ክርስቲያን ጽፋ ባስቀመጠችው ሕጓ የጠቅላይ ምንስቴር ዓቢይን መንግስት እፋረድሀለሁ እያለች የመፋለም እጽፍ ድርብ ሀላፊነት አለባት።

በፍትሐ ነገሥቷ “ወለዘሂ አገበርወ ከመ ይቅትል ለእመ ኮነ ዘአገበሮ መኮንን ውእቱ ላዕለ አልቦ ዕዳ በላዕሌሁ። ወለእመ ኮነ ካልእ አዛዚ ሥሉጠ ላእለ ተአዛዚ ይደሉ ኩነኔሁ ላዕለ አዛዚሁ። ወእመሰ ኢኮነ ሥሉጠ በላዕሌሁ ወኢይፈርህ እምኔሁ ይደሉ ከነኔሁ ላእለ ተአዛዚ”(አንቀጽ 471678) የሚል አንቀጽ አለ። ይህም ማለት፦ “አንድ ሰው በሌላ ሰው ተገፍቶ ሰው ቢገድልና ተገፋፍቶ የሚፈጽመው ግድያ የሚያስከትለውን ፍርድ የመገመት አቅሙ ከገፋፋው ሰው እውቀት በታች ከሆነ ግድያውን ያስፈጸመው አካል ፍርዱን ይቀበላል። ነገር ግን ገዳዩ የሚያስከተልውን ፍርድ ለመገመት የእውቀት አቅሙ እንዲገድል ካዘዘው በላይ ከሆነ ራሱ ገዳዩ ፍርዱን ይቀበላል” ይላል።

ሕጔን ከዓለሙ ህግ ጋራ አቆራኝተውና አጣጥመው በህዝቧና በነዋየ ቅድስቷ ላይ የደረሰውን ጥቃት ለዓለም ማቅረብ የሚችሉትን የህግ ሊቃውንት ልጇችን መሰብሰብና ሃይላቸውን አጠናክረው ከጎኗ እንዲሰለፉ ብታደርግ ከወቀሳና ከከሰሳ ያድናታል።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያነብ ሁሉ ሊረዳው የሚችለው በሀዲስ ኪዳን ውስጥ ሌላም አንቀጽ አለ “ሞት የሚገባው በደል በፈጸመ ሰው ላይ፤ በአድልዎ ሞት ቢፈረደበት ቤተ ክርስቲያን ጠበቃ ሆና እንድትፋለም ሃላፊነት እንዳለባት ሁሉ፤ ሞት የሚገባውን በደል በፈጸመ ሰው ላይ የሞት ፍርድ ተበይኖበት የክሱ ፋይል እንዲዘጋ በመንግሥት ላይ ተጽእኖ ታሳድራለች1ኛ ዮሐንስ 516። በደለኛው በሕግ ስር ወድቆ ሞት ከተበየነበት በኋላ እንደሞተ ይገመታል። የሞቱ ፍርድ ተበይኖ የክሱ ፋይል ከተዘጋ በኋላ፤ በተበየነበት ሰው ላይ ሞቱ ተግባራዊ እንዳይሆን፤ ወደ ምህረት እንዲለወጥ ቤተ ክርስቲያናችን ለምህረት የመታገል ግዴታ አለባት።

ጠቅላይ ምንስቴር ዓቢይም፡ ፍትህን ለመደበቅ በውስጣቸው የሸመቀ ሸፍጥ ከሌለባቸው፤ በአገራችን የተፈጸመውን ጭፍጨፋ አቻ ላቻ አድርገው የደም ድምጽ ክስ እንዲቀጥል ከማድረግ ይልቅ ፤ ራሳቸው “ስንሳሳት ገስጹን” እንዳሉ ስህተታቸውን ተገንዝበው፤ ቤተ ክርስቲያናችን ፍትህ እንዲፈጸም በምታደርገው ጥረት ቢተባበሩ ለራሳቸው መንግሥት ቢጠቅም እንጅ የሚጎዳ አይደለም።

የግላቸውን ጥቅምና ክብር ጤንነትና ድሎት ሳይመርጡ “የፍትህ ያለህ” እያሉ የሚጮኹትንና፤ “የግድያው ጀማሪና ትእዛዝ ሰጭው ማን እንደሆነ ሳይገልጹ የሟቾች መንደር መጥቀሱ ከአስፈላጊነቱ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን እየገለጹ፤ ለብሄሩ ለመንደሩ ብቻ የሚያስብና የሚያዘነብል የሚያዳላ ከአውሬ እንደማይሻል እየተናገሩ፤ ከእንግዲህ ወዲህ በጠቅላይ ምንስቴሩ ብቻ መተማመን ጠቃሚ አይደለም ብለው የተናገሩትን ወገኖች በዚህ አጋጣሚ ሳላመሰገን አላልፍም።

የድሮ አባቶች ይህን የመሰለ መከራ ሲገጥማቸው እንዴት ተሻገሩትብለን ታሪካቸውን ስንቃኘው በሰላሙ ጊዜ ቆመውም ተቀምጠውም ተኝተውም “ወደፈተና አታግባን” የሚለውን ቁጭ ብለው እያለቅሱ እንዳላሳለፉት መረዳት እንችላለን። በፈተናው ከገቡ በኋላ የመለያየትን የጸብ ግድግዳ ለማፈረስ ክርስቶስ ኃይሉን የገለጸበትን በልባቸው የተሳለውን የመስቀል አርማ በእጃቸው ጨብጠው “እለ ይትመነደቡ ታድህን፤ ወለእለ በመዋቅህት ጽኑአን ዘምስሌሆሙ ትሄሉ” የሚለውን ጸሎት ተግባራዊ ለማድረግ በሚገደሉትና በሚገድሉት ወገኖች መካከል በመገኘት እኛን ሳትገድሉና ሳታርዱ ህዝባችንን ልታርዱ አትችሉም በማለት ክህነታዊትና ወገናዊነት ሀላፊነታቸውን እየተወጡ አለፉ።

በውስጥም በውጭ ለተበተነው ሁሉ ኢትዮጵያዊ ወገኗም እንደ ነቢዩ ኢሳይያስ “የደከሙት እጆች ይበርቱ የላሉትንም ጉልበቶች ይጽኑ ። ፈሪ ልብ ያላችሁም፤ አምላካችሁ በበቀል ብድራትን ለመክፈል መጥቶ ያድናችኋልና በርቱ አትፍሩ”ኢሳ 354) እያለች መበርታትና ማጠነካከር አለብን።

መሰብሰብን መነቃቃትንና መመካከርን አጥብቆ የሚጠይቅ ከዚህ ዘመን የከፋ ስለሌለ እርስ በርሳችን እየተያየን እንድንቃቃ እንድንመካከር በዓለም ለተበተን ልጆቿ መንፈሳውያን ካህናትም ከነ ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ ጋራ እንድንሰበሰብ እንድንነቃቃ እንድንመካከር ቅዱስ ፓትርያርኩ ሊጎተጉተን ይገባል።

በዚህ ዘመን ያለን ካህናት ቤተ ክርስቲያናችን የገጠማትን ፈተና፤ ከክርስትናችን ጋራ ባልተጋጨ መንገድ ለመወጣት እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከመፋለም ይልቅ፤ በየአጥቢያችን ተከልለን ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጣውን ህዝብ በሰላም ጊዜ እንደምናደርገው “ንስሀ ግቡ አልቅሱ” እያልን መሸኘት በዚህ ወቅት ያለችው ቤተ ክርስቲያናችን የምትቀበለው አይደለም።

ዛሬ ቤተ ክርስቲያናችን ከገባችበት ፈተና እንድትወጣ የሚጠበቅብንን ሳንወጣ ይህ እድል ቢያመልጠን፤ የሰውነቱን ገበና የሚሸፍንበት አጥቶ ነጠላ የሚለምነውን ሰው፤ ነጠላ ሳይሰጥ ሂድ ልበስ ይሙቅህ፤ የሚጎርሰው አጥቶ የሚለምንንም ምንም ነገር ሳይሰጥ ሂድ ብላ ጥገብ ከሚል ግብዝ የተለየን ልንሆን አንችልም። ይህ ባህርይ ህዝበ ክርስቲያንን ከሚያርደውና ቤተ ክርስቲያን ከሚያቃጥለው አረመኔ የተለየ አለመሆኑን ቅዱስ ያዕቆብ “አንተ ግብዝ በተግባር የማይገለጥ እምነት ነፍስ የተለየችው በድን እንደሆነ አታውቅም? (ያዕ 216᎗20ብሎ ገልጾታል።

በተረፈ “ደምረነ ምስለ እለ ይድህኑ” አጥፍተው ከሚጠፉ ሸፍጠኞች ንክኪ ጠብቀህ፤ ራሳቸው ድነው ሌላውን ለማዳን ከሚጥሩት የእምነትና የተግባር ከሆኑት ወገኖች ጋራ ደምረን“ በሚለው በሊጦኑ ጸሎታችን ይህችን ጦማር እደመድማለሁ።

____________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: