Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • November 2019
    M T W T F S S
     123
    45678910
    11121314151617
    18192021222324
    252627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for November 9th, 2019

ይህ ወንድማችን ወደ አዲስ አበባ ገቡ ከተባሉት ስውር አባቶች መካከል አንዱ ቢሆንስ?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 9, 2019

ዮሐንስ ማለት የእግዚአብሔር ጸጋ ነዉ፤ ደስታ ማለት ነዉ።

በቅዱስ ዮሐንስ ዕለት፤ ረፋድ ላይ በቦሌ መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን፤

እንደልብስ አካሉን በካርቶኖች ብቻ የሸፈነው ይህ ወንድማችን የቤተክርስቲያኑ አንድ ደረጃ ላይ ቁጭ ብሎ ይታይ ነበር። በካርቶኖቹም ላይ ኃይለኛ መልዕክት ያዘሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ተጽፈውባቸው ይነበቡ ነበር። ገና ከሩቁ ሳየው መጥምቁ ዮሐንስ መስሎ ነበር የታየኝ። ሁኔታውን ከሩቅ መከታተል ስጀምር፤ ምዕመናኑ ከእርሱ ጋር በደስታ አብረው ፎቶ ይነሱ ነበር፤ አንዳንዶቹ ገንዘብ ነገር ሊሰጡ ሲሞክሩ ለመቀበል ፈቃደኛ አልነበረም። ብዙም ሳይቆይ “በየቤተክርስቲያኑ አስቸጋሪ እየሆኑ የመጡት ዘበኞች” ከቤተክርስቲያኑ ግቢ እንዲወጣ አዘዙት። በጣም አዘንኩ። ቤተክርስቲያኑን ተዘዋውሬ ስመለስ ወደ መውጫው ሲያመራ አየሁትና ራመድ ብዬ፤ “ጤና ይስጥልኝ ወንድሜ፤ እንኳን አደረስህ!” ብዬ ሳቅፈው አፃፋውን ሞቅ ባለ ድምጹ በትህትና ከመለሰለኝ በኋላ “ኧረ አይገባኝም ወንድሜ! ለኢትዮጵያ ፀልይላት!” በማለት ተሰናበተኝ።

ምናልባት እኮ ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ነው ከተባሉት አባቶች አንዱ እርሱ ሊሆን ይችላል፤ ክርስቶስም እኮ ሱፍ በከረባት ለብሶ አይደለም የሚመጣው” አሰኘኝ።

መድኃኔ ዓለም ማለት፦ የአለም መድኃኑት ማለት ነው። በእርሱ አለም ስለዳነ (በሞቱ አለምን ስላዳነ) መድኃኔ ዓለም የአለም መድኃኒት እንለዋለን። [ሉቃስ ፪፥፲፩] ላይ እነሆ ለሕዝብ ሁሉ የምሆን መድኃኒት እንዳለ ሉቃስ፤ [ዮሐ.ወ ፩፥፳፱] ላይ መጥምቁ ዮሐንስ እነሆ የአለምን ኃጢአት የምያስወግድ የእግዚአብሔር በግእንዳለው እንደገና [በሮሜ ፭፥፲፪፡፳፩] ስናነብ በአንድ ሰው በአዳም ምክንያት ሞት ወደ አለም እንደመጣ ሁሉ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትም አለም እንደዳነ ይናገራል።

_________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: