በእውነት የዚህን ወሮበላ ጂሃዲስት አደጋኘነት ማየት የሚሳነው መንፈሳዊ ዓይኑ የታወረ ብቻ ነው። ጄነራሎቹን እና እነ ኢንጂነር ስመኘውን እርሱ እንደገደላቸው ዛሬ የሚጠራጠር ሰው አለ? ኢትዮጵያን ለግብጽና አረቦች አሳልፎ እየሰጠ እንደሆነ መገመት የማይችል ሰው ይኖር ይሆን? አሁንስ ገባን ለምን ሉሲፈራውያኑ የኖቤል “ሰላም” ሽልማት እንዳበረከቱት!?
ሰውዬው ቶሎ መወግድ ይኖርበታል!
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 3, 2019
በእውነት የዚህን ወሮበላ ጂሃዲስት አደጋኘነት ማየት የሚሳነው መንፈሳዊ ዓይኑ የታወረ ብቻ ነው። ጄነራሎቹን እና እነ ኢንጂነር ስመኘውን እርሱ እንደገደላቸው ዛሬ የሚጠራጠር ሰው አለ? ኢትዮጵያን ለግብጽና አረቦች አሳልፎ እየሰጠ እንደሆነ መገመት የማይችል ሰው ይኖር ይሆን? አሁንስ ገባን ለምን ሉሲፈራውያኑ የኖቤል “ሰላም” ሽልማት እንዳበረከቱት!?
ሰውዬው ቶሎ መወግድ ይኖርበታል!
Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: ሙስሊሞች, ቄሮ, ቅሌታም, አብይ አህመድ, አታላይ, ኢትዮጵያ, ኦሮሞዎች, ወራዳ, ዘር ማጥፋት, ግራኝ, ግራኝ አህመድ, ፀረ-ተዋሕዶ ዘመቻ, ፀረ-ኢትዮጵያ, ፋሺዝም, Genocide | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 3, 2019
ቫቲካን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን አስመልክታ ይህን መሰሉን መልዕክት ስታስተላልፍ አትሰማም፤ ይህ ያልተለመደ ነው። አሕዛብ እና የኦሮሞ ፋሲስቶች የከፈቱት የፍጅት ዘመቻ ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነና ዓለማችንም ቀስበቀስ ወደ ተጨነቁት የኢትዮጵያ ድንኳኖች አይኗን መጣሏን እንደጀመረች ነው የሚጠቁመን።
Pope Francis Asks For Prayer For Persecuted Christians In Ethiopia
Pope Francis Sunday asked for prayer for persecuted Orthodox Christians in Ethiopia, who have been targeted in ongoing ethnic clashes that have left 78 people dead.
“I am saddened by the violence of which Christians of the Tewahedo Orthodox Church of Ethiopia are victims,” Pope Francis said in his Angelus address Nov. 3.
“I express my closeness to this beloved church and her patriarch, dear brother Abune Mathias, and I ask you to pray for all the victims of violence in that land,” he said.
Since violent protests broke out in Ethiopia’s Oromia region Oct. 23, more than 400 people have been arrested and 78 have died, according to the office of Prime Minister Abiy Ahmed.
The Orthodox Christian community has been a target of violence in Oromia. A church official told AFP Africa that 52 Orthodox Ethiopians, including two church officials, have been killed in the violence since the protests began in October.
A hand grenade was thrown in a churchyard in Tsadiku Gebrekristos, and the homes and businesses of Christians were set on fire, according to local Ethiopian Borkena news.
The Patriarch of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church Abune Mathias delivered a speech Oct. 28 calling for peace and grieving the dead.
“I carry a cross in my hand, not a gun. My children, I am tearfully praying to our God about your suffering. I am also continuing to plead with the government,” Mathias said, according to local Ethiopian media.
“Today I am deeply grieved. I have the urge to weep like a child … In the hopes day to day for improvement, we have been asking the government to put a stop to it. However we have seen nothing change,” the patriarch said.
Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed was awarded the 100th Noble Peace Prize in October for leading peacekeeping efforts to end the 20-year conflict with neighboring Eritrea. Violent protests began within Ethiopia less than 2 weeks after.
The protests were sparked by an allegation by political activist Jawar Mohammed that the Ethiopian government had attempted to arrest him.
The Holy Synod of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church met with Ethiopian government officials to Oct. 26 to call for peace and dialogue in the face of the violence. The Ethiopian Orthodox Church also called for three days of prayer and fasting for peace.
“God is with us,” Orthodox priest Markos Gebre-Egziabher said at a memorial service Oct. 26 for Christians killed in Addis Ababa, according to AFP.
“If they come with machetes, we will go with crosses,” Father Markos said.
The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church is the largest of the Oriental Orthodox Churches. These Churches reject the 451 Council of Chalcedon, and its followers were historically considered monophysites – those who believe Christ has only one nature – by Catholics and the Eastern Orthodox.
Pope Francis met with Ethiopian Orthodox Patriarch Abune Mathias in Feb. 2016, and expressed his condolences for the Ethiopian Christians executed by Islamic State militants in Libya in April 2015.
In an emotional speech Oct. 28, Patriarch Mathias told his persecuted community in Ethiopia:
“While I was preaching to you about peace, those that do not know peace have deprived you of peace. My children, do not hold a grudge on me. Do not think I am silent to your plight. I always weep for you. Lord, send your Judgement, or come down to us.”
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: በደል, ቫቲካን, ኦሮሞዎች, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን, ግፍ, ጭፍጨፋ, ጳጳስ ፍራንሲስ, ፀሎት, ፀረ-ተዋሕዶ ዘመቻ, ፀረ-ኢትዮጵያ, ፍራንቸስኮ | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 3, 2019
ከሃዲውና አረመኔው የፋርስ ንጉሥ ግራኝ አህመድ አብዮትን ያሳየናል። ግራኝ አብዮት እንደ በለዓም እና እንደ ይሁዳ ብቻ ሳይሆን ልክ እንደ ጣዖት አምላኬው የፋርስ ንጉሥ እንደ ዱድያኖስም ነው።
የኢትዮጵያ ገበዝ ጊዮርጊስ ና! በፈረስ
የቤሩት ሰዎች እግዚአብሔርን የማያውቁ አረመኔዎች ሲሆኑ ስሙ ደራጎን የሚባል መንፈሰ ሰይጣን
ያደረበት ዘንዶ ያመልኩ ነበር። ደራጎኑም ሲያዩት እጅግ የሚያስፈራ እና እንደ ንስር ሁለት ክንፍ፣ እንደ ፍየል ጢም፣ እንደ አንበሳ ያለ እግርና ጥፍር፣ እንደ ውሻ ጆሮ፣ እንደ ዘንዶ ያለ ጅራት፣ እንደ አዞ ያለ ጥርስ ነበረው።
የቤሩት ሰዎችም ለደራጎኑ ሴቶች ልጆቻቸውን ይገብሩለት ነበር። ከብዙ ዘመን በኋላ የአገሪቱ ሴት ልጆች በአለቁ ጊዜ የአገረ ገዥው ሴት ልጅ ስሟ ቡርክታዊት የምትባል ቤሩታዊት ለደራጎን ምግብ ትሆነው ዘንድ
ጫካ ውስጥ አኖሯት። የተመሰገነው ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ቤሩት ሀገር በደረሰ ጊዜ በጫካ ውስጥ ሲዘዋወር የአገረ ገዥውን ልጅ እያለቀሰች ብቻዋን ተቀምጣ አገኛት፤ ቅዱስ ጊዮርጊስም ከዚህ ምን ትጠብቂያለሽ? አላት። ለደራጎን እንደተሰጠችና ስለ ደራጎን ግብርም አስረድታ ፈጥኖ ከዚያ አካባቢ እንዲሰወር ነገረችው። ኀያሉ ቅዱስ ጊዮርጊስም ሰይጣን ያደረበትን ደራጎን እንደማይፈራውና አማልክትን
ሁሉ የሚገዛ፤ ሰማይ እና ምድርን የፈጠረው አምላኬ አለ፤ ከዚህ ከተረገመ አውሬ እርሱ ያድነኛል አላት። ይህን ሲነጋገሩ ደራጎን ምድሪቱን እያናወጠ መጣና ቅዱስ ጊዮርጊስን ሊበላው ወደደ፤ ምላሱን
አውለብልቦ መርዘኛ ትንፋሹን ሊረጭበት ፈለገ። ነገር ግን ቅዱስ ጊዮርጊስ የእግዚአብሔርን ኃይል መከታ አድርጎ በሥላሴ ስም በትእምርተ መስቀል ቢያማትብበት የደራጎኑ ጉልበት ራደ፣ ኃይሉ ደከመ። መርዙም ጠፋ።
ቅዱስ ጊዮርጊስ ለደራጎን ተሰጥታ የነበረችውን የንጉሡን ልጅ ፈትቶ ደራጎኑን አስሮ እሷ እየጎተተች እሱ በፈረስ ሁኖ ከተማ በደረሱ ጊዜ የአገሩ ህዝብ ደራጎኑን ሲያዩ እጅግ በፍርሃትና በድንጋጤ ተዋጡ።
ሊያስፈጀን ነው ብለው ይሸሹ ጀመር። ቅዱስ ጊዮርጊስን አምላካችንን ስለምን አመጣህብን አሉት፤ ይህ እራሱንም እንኳ ማዳን ያልተቻለው እንደምን ለእናንተ አምላክ ሊሆን ይችላል? አላቸው። አምላካችንን
አንተውም አሉት፤ ካልተዋችሁትስ እንዲጨርሳችሁ ፈትቼ ወደ እናንተ እሰደዋለሁ አላቸው። ይህስ አይሁን ባይሆን ዘንዶውን ልትገድለው ከቻልክ አንተ በምታመልከው አምላክ እናምናለን አሉት። ከከተማ አውጥቶ ዘንዶውን በጦር ወግቶ ገደለው። ህዝቡም ሁሉ ይህን አይተው በእግዚአብሔር ስም አምነው ተጠምቀዋል። ደራጎኑን ከገደለበት ከተማም ሁለት አብያተ ክርስቲያናት ሠርተዋል።
በዚያን ጊዜ በሀገሩ ሁሉ ላይ ሥልጣን ያለው ስሙ ዱድያኖስ የተባለ የፋርስ ንጉሥ ነበር። እጅግ ብርቱ በነገሥታትም ላይ ሥልጣን የነበረው፤ ፈጣሪውን ሳይቀር የካደ እንደ ናቡከደነጾርም ልቡ የደነደነ ነበር።
ክርስቲያኖችንና አብያተ ክርስቲያናትን በጽኑ ይቃወም ነበር። ዱድያኖስም ሰባ ነገሥታትን ሰብስቦ ሰባ ጣኦታት አቁሞ ይሰግድ ያሰግድ ነበረ። በዚያን ጊዜ ቅዱስ ጊዮርጊስም ወደ ንጉሥ ዱዲያኖስ ከተማ በመሄድ ከዓላውያን ነገሥታት የሰማዕትነት ተጋድሎውን ጀመረ።
ቅዱስ ጊዮርጊስ እድሜው ወደ ሃያዎቹ ሲጠጋ አባቱ በልጅነት ሳለ ስላረፈ የአባቱን ሹመት ለመረከብ ወደ ንጉሡ ዱድያኖስ ዘንደ ሄደ፡፡ ንጉሡ ዱድያኖስ ግን ሰባ ከሚሆኑ ነገሥታት ጋር እየበላና እየጠጣ ይጨፍር ለጣዖትም ይሰግድ ነበር፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ንጉሡ ካለበት ሲደርስ ጣዖት አምልኮ ነግሦ ሰው ሁሉ ከእውነተኛይቱ ሃይማኖት ወጥቶ፤ ክርስቲያን ነኝ ማለት ወንጀል እንደሆነ የተነገረውን አዋጅ አይቶና ሰምቶ ተረገመ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ እርሱን ተከትለው የመጡ ባለሟሎችን ካሰናበተ በኋላ የሞቱን መስቀል ተሸክሞ በኋላም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን አይገባውም ነፍሱን ሊያድን የሚወድ የጠፋታል ነፍሱን ስለእኔ የሚያጠፋ ያገኛታል ማቴ 1ዐ፡38 39 በማለት የሕይወት ባለቤት መድኃኔዓለም ክርስቶስ የተናገረውን ቃል መሠረት በማድረግ ኃላፊ ጠፊ የሆነውን ምድራዊ መንግሥት በመተው የማያልፈውን ዘለዓለማዊ ሰማያዊ መንግሥት ተስፋ አድርገው ከጣዖት አምላኪዎች ከአሕዛብ ከመናፍቃን የሚደርሰውን መራራ ሞት ማለትም እሳቱን ስለቱን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ስለ አምላኩ መስክሮ በሰማዕትነት ለማለፍ ወሰነ፡፡ ምድራዊውን ሹመት ተወ፣ ናቀ፡፡ ሰማያዊ ሹመት እንደሚበልጥም አስቦ ሐዋርያዊውአባተ ቅዱስ ፖሊካርፐስ “እኛ የተሻለውን በክፉው አንለውጥም ነገር ግን ክፉውን በመልካሙ እንለውጣለን›› እንዳለ ክፉውን የነዱድያኖስን ኑሮ በመልካሙ ክርስትና ሊለውጥ ተዘጋጀ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለምስክርነተ ቆርጦ መነሳቱን ንጉሡ ሲመለከት አስጠርቶ የሚሰቃይባቸውን መሣሪያዎት አሳየው፡፡ “እነርሱም የብረት አልጋዎች፣ የብረት ምጣዶች፣ መንኩራኩሮች፣ አጥንት ለመስበር የሚችል ከብረት አልጋዎች የእጅ መቁረጫ፣ ምላስ ለመቁረጥ የሚችል ቢለዋ፣ አጥንትን ከጅማት የሚለያይ መውጊያ፣ አእምሮን የሚነሳ ጉጠት፣ አጥንት የሚቀጠቅጡባቸው የተሳሉ መጋዞች፣ አፋቸው እንደ መጋዝ ዋርካ ያለው የብረት ድስት፣ ረዣዥም የብረት በትሮች፣ ጥርስ ያለው የብረት ጐመድ መሣሪያዎች ነበሩ /ገድለ ጊዮርጊስ ምዕራፍ 3 ቁጥር 8/ ነበሩ፡፡
ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን ይህንን አይቶ አልፈራም፡፡ ለሃይማኖቱ ቀናኢ ነውና ከቤተመንግሥቱ ገብቶ በከሃዲያኑ ሥጋውያን ነገሥታት ፊት ክርስቲያን መሆኑን በመመስከር የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት መሰከረ፡፡ ዱድያኖስም ማንነቱን ከተረዳ በኋላ “አንተማ የኛ ነህ በአሥር አህጉር ላይ እሾምሃለሁ የኔን አማልክተት አጰሎንን አምልክ” አለው፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም “ሹመት ሽልማትህ ለአንተ ይሁን እኔ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልከዳውም” አለው፡፡ ክርስትናውንም በአደባባይ ከመመስከር ወደኋላ አላለም፡፡ ጣዖታት የማይረቡ የማይጠቅሙ የአጋንንት ማደሪያዎች መሆናቸውን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከበረ ደሙ ፈሳሽነት መላውን የሰው ዘር ያዳነ እውነተኛ ዘላለማዊ አምላክ መሆኑን አስተማረ፤ ይልቁንም በሚያደርገው አምልኮ ጣዖት ወደ ኩነኔ ወደ ገሃነም እንደሚገባ በግልጽ ነገረው፡፡ ስለዚህ ዱድያኖስ ተቆጥቶ ለሰባት ዓመታታ ለሰሚ የሚደንቅ መከራ አጸናበት ቅዱስ ጊዮርጊስ የደረሰበት እጅግ አሰቃቂ መከራዎች የሰው ኀሊና ሊያስባቸው እንኳን የማይችላቸው ናቸው፡፡ እየፈጩ፣ እየሰነጠቁ፣ በጋለ ብረት እየወጉ አሰቃዩት፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን ጌታችንን “ይህን ከሃዲ እስካሳፍረው
ድረስ ነፍሴን አትውሰዳት። በማለት መከራውን ይታገስ ዘንድ ለመነው፡፡ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰምቶ ፈቃዱን ይፈጽምለት ብዙ በመከራው ሁሉ ጽናትን ሰጥቶታል። በዚህ ጊዜ ሦስት ጊዜ ሞቶ ተነሳ እግዚአብሔር ጠላቶቹን ድል ሳያደርግ እንዳይሞት ፈቅዶልና ከሞት አስነሳው መከራውን ሁሉ ግን ተቀበለ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እየበረታ የሚያደርሱበትን ስቃይ ደስ እያለው ይጠቀበለው ነበር፡፡ ከፈጣሪው ዋጋ የሚያገኝበት ነውና፡፡ [ሉቃስ ፮፥፳፪፡፳፬]
አቤቱ
በእንተ ጊዮርጊስ ሰማዕትከ ምሕላነ ስማዕ በዕዝንከ።
በእንተ ጊዮርጊስ ምዕመንከ ምሕላነ ባርክ በእዴከ።
በእንተ ጊዮርጊስ ቅዱስከ ምሕላነ አፅምዕ በዕዝንከ።
የተዋህዶ ቅዱሳኖች ተንቀሳቃሽ የሚነበቡ ወንጌሎች ናቸው።
የሚበልጠውን ትንሳኤ እንዲያገኙ እስከሞት ድረስ ተደበደቡ ሌሎችም መዘበቻ በመሆንና በመገረፍ ከዚህም በላይ በእስራትና በወይኒ ተፈተኑ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ ተፈተኑ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ ተፈተኑ በመጋዝ ተሠነጠቁ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ። [ዕብ ፲፩፥፴፮]
እነሱም በእምነት ነገስታትን ድል ነሱ። [ዕብ. ፲፩፥፲፫]
የእግዚአብሔር ቸርነት የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳኢነት የእመቤታችን አማላጅነት ከመላው ህዝበ ክርስቲያን ጋር ፀንቶ ይኑር። ቅዱስ ጊዮርጊስ በያለንበት እየባረከ ከበረከቱ እያሳተፈ ክፉ ሚያስቡብንን በየእርምጃችን ወጥመድ የሚያስቀምጡ መናፍስትን ከእግራችን በታች እየቀጠቀጠ በሰላም ያውለንን። ሃገራችን ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ከስጋና ከነፍስ መከራ ይጠብቅልን። አሜን!
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: ሊቀ ሰማዕታት, ሕፃናት, መንግስት, ቅዱስ ጊዮርጊስ, አውሬው, ኢትዮጵያ, ኢትዮጵያውያን, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን | Leave a Comment »