Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • November 2019
  M T W T F S S
   123
  45678910
  11121314151617
  18192021222324
  252627282930  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Archive for November 1st, 2019

በጣም አስቸኳይ! | የግራኝ አብዮት የኦሮሞ ሠራዊት በአሰቦት የሴቶች ገዳም ላይ ጥቃት ለማድረስ ተዘጋጅቷል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 1, 2019

በሐረርጌ ምድርና ሰማይ የጥፋት አንበጦች አንዣብበዋል

ለአሰቦት ገዳም ቅርበት ያላቸው ሰዎች እንደገለፁልን ከሆነ በአሰቦት ገዳም በተለይም ሴት መነኮሳይያት በሚኖሩበት ከተራራው ግርጌ አካባቢ አደጋ እንዳንዣበበ፣ የገዳሙ በሮች መሰባበራቸውን ገዳማውያኑም መኖሪያቸውን ትተው ወደ ተራራው ወደ ቤተ ክርስቲያኑ መሰባሰባቸው ተነግሯል።

በተለያዩ ጊዜአት በመሀመዳውያኑ የግራኝ አህመድ ልጆች የጥቃትት ዒላማ መሆኑ የሚታወቀም የአሰቦት አባ ሳሙኤል ገዳም ከአሰቦት ከተማ ፲፪ ኪሜ ላይ የሚገኝ ሲሆን እናቶች መነኮሳይያት የሚኖሩበት የሴቶች ገዳም ከእግረ ደብር ይገኛል። ድንጋይ በመወርወር እና ግቢው ውስጥ በመግባት ችግር እየተፈጠረበት ያለው ይኸው የሴቶች ገዳም መሆኑ ታውቋል።

እንደሚታወቀው ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት የግራኝ አህመድ አጋንንታዊ ሠራዊት የጥፋት ወረራ እንዲሁም ከ ከሰማኒያ ዓመታት በፊት በፋሺስት ኢጣሊያ ፀረኢትዮጵያ ዘመቻ ጊዜ ጣልያኖችና የግራኝ እርዝራዦች በዚህ ገዳም ላይ አደጋ አድርሰውበት ነበር።

በዚህ ታሪካዊ ገዳም ላይ ዛሬም ያንዣበበውን ከፍተኛ አደጋ ምእመናን ተገንዝበው አስፈላጊውን ጥበቃ እራቸው ያድርጉ። ህገወጥ ከሆነው የአውሬው መንግስት ምንም በጎ ነገር አትጠብቁ! የጸሎት አባቶች አረምመኔውን መንግስት ከስሩ እንዲነቅሉልን አሳውቋቸው!

አባቶችንና እናቶችን ስላሸበሩ በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ድል የተቀዳጁ የሚመስላቸው አራጅ የዲያብሎስ ልጆች ዕድል ፈንታቸውና ዕጣ ተርታቸው ትሉ በማያንቀላፋበትና እሳቱ በማይጠፋበት ዘላለማዊ ሲዖል ውስጥ ነው።

ለደረሰው፣ እየደረሰ ላለውና ለሚደርሰው ግፍና ሰቆቃ የግራኝ አብዮት አህመድ መንግስት፡ እንዲሁም የግብጽን እና የአረቦችን አጀንዳ ለማራመድ ለተጠሩትና ፀረኢትዮጵያ ለሆኑት ኦሮሞዎች ስልጣኑን ያስረከበው ህውሃት ተጠያቂዎች ናቸው!!!

+ መምህር ዘመድኩን የሚከተለውን አቀብሎናል

በወንዶች ገዳም በዋናው በሥላሴ ገዳም የተፈጠረ ነገር የለም። ችግሩ የተፈጠረው በሴቶች ገዳም ነው። ድንጋይ በሴቶች ገዳም የመነኮሳቱ መኖሪያ ቤቶች ላይ ከምሽቱ 2:30 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 4:00 አካባቢ ሲወረወር ነበር ያመሸው። እኛና የገዳሙ ጥበቃዎችም አካባቢውን እየተዟዟርን ለመቃኘት ሙከራ አድርገናል። ነገር ግን በቦታው መብራት ስለሌለና ጨለማ ስለሆነ ድንጋይ ወርዋሪዎቹን ለማግኘት አልቻልንም።

ሲነጋ ሁሉም መነኮሳት ለጸሎተ ኪዳን ተሰብስበናል። አንዲት መነኮስ እናት መኖሪያ ቤታቸው መስኮቱን ለመክፈት እንደመታገል፣ በሩን በእርግጫ ከፍቶ እንደመግባት ያለ ሙከራ ተደርጎብኛል የሚል ቃል ከመስጠታቸው በቀር ሌላ የተለየ የቀረበ ሪፖርት የለም። ቆላው አካባቢ ጥቂት ክርስቲያኖች አሉ። በአካባቢው ያሉ ሙስሊሞችም እስከአሁን በመንገድ ላይ ስንገናኝ ከሰላምታ በቀር ምንም ዓይነት የትንኮሳ ፊት አላሳዩንም። እናም ዘመድኩን ያለው ሁኔታ ይህን ይመስላል። አሁን ከነጋ ህዝቡ ከየቦታው እየደወለ ሲያጽናናን ነው የውጪው ህዝብ መስማቱንም ያወቅነው ብለውኛል።

ችግር ሳይከሰት እንዲህ ፈጥኖ መረጃ ለህዝብ ማድረሱ እንደለ የሚደገፍ ሆኖ ሳለ የተጣራ መረጃ ሳይዙ ነገሮችን ዝም ብሎ በባዶ ሜዳ ማጮሁም የባሰ አደጋም አለው። ጉዳቱም ለምሳሌ በደብረ ወገግ አሰቦት አባ ሳሙኤል ገዳም በዓመት ሁለት ጊዜ ዓመታዊ ክብረ በዓላት አሉ። አንደኛው ከፊታችን በሚመጣው ጥቅምት 29 ቀን የጻድቁ አቡነ ሳሙኤል በዓለ ዕረፍታቸው ሲሆን ሐምሌ ሰባት ደግሞ የቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓላት ናቸው። በእነዚሁ ሁለት በዓላት ነው ብዙ ህዝብ ወደዚህ ጥንታዊ ገዳም በመጓዝ ከገዳማውያኑ በረከት የሚቀበለው። ለገዳማውያኑም የዕለት ጉርስ የዓመት ቀለብ የሚለግሰው።

ምን አልባትም ሰይጣን ከፊታችን ጥቅምት 29 በሚከበረው ዓመታዊው የጻድቁ በዓለ እረፍት ላይ ምእመናን ተገኝተው የበረከቱ ተካፋይ እንዳይሆኑ፣ በዚያም ገዳማውያኑ ተቸግረው ከገዳሙ እንዲለቁ የዘየደው ዘዴም ሊሆን ይችላል። በገዳም ውስጥ መነኮሳትን፣ መናንያንን መረበሽ፣ ገዳማውያንን ማወክ የሰይጣን ልማዱ ነው። እናም ይሄን የሁከት ድርጊት ፈጥሮ በጭለማ ድንጋይ ሲወራወር ካመሸ በኋላ ዜናው በፌስቡክ እንዲወጣ አድርጎ እነዚያ በበረሃ ተቀምጠው በዓመት ሁለት ጊዜ ከሚመጡ ምእመናን እጅ በሚያገኙት አሥራት ለሀገር ለወገን ሲጸልዩ የሚኖሩ ገዳማውያን እንዳይረዱ ምእመናንም ዜናውን ሰምተው ፈርተውና ተደናግጠው ጥቅምት 29 ወደ አሰቦት ከመሄድ ለማስቀረትም ይሆናል ድንጋይ ሲወረወር ያመሸው። እናም ሰይጣንን የማሰፈሩ ነገር ቢታሰብበት መለካም ነው።

አሁን ላይ ወደ ገዳሙ መንኩሰው የሚገቡ ሴት መነኮሳይት ቁጥር እየጨመረ መምጣቱንም በስልክ ያነጋገርኳቸው እማሆይ ነግረውኛል። ገዳሙ ይጠፋል ሲባል ጭራሽ እያበበ እየሄደም እንደሆነም ተነግሮኛል። ደግሞም የሚመጣም መከራ ካለ ለመቀበል ነው ከመላዋ ኢትዮጵያ ወደዚያ በረሃማና በአካባቢው ከእስላሞች በቀር ክርስቲያኖች ወደሌሉበት ጥንታዊ ገዳም የሚጎርፉት። እናም ጥቅምት 29 የተዋሕዶ ልጆች በሰማችሁት ተደናግጣችሁ እንዳትቀሩ በልልኝ ብለዋል ገዳማውያኑ።

እንደ በረኸኞቹ ቃል ወደፊት በአህዛብ የከፋ ጉዳት ከሚደርስባቸው የኢትዮጵያ ተላላቅ ገዳማት ውስጥ የአሰቦት ሥላሴ አንደኛው እንደሚሆን ይነገራል። እንደ ዋልድባ፣ ማኅበረ ሥላሴ፣ ጉንድ ተክለሃይማኖት፣ አክሱም ጽዮንና ደብረ ሊባኖስ የሰማዕትነት አክሊል ከሚቀበሉ ገዳማውያን የመጀመሪያው ረድፍ ላይ የሚገኝ መሆኑም ይነገራል። ሰማዕትነት ደግሞ ለአሰቦት ገዳም መነኮሳት እንግዳ ነገር አይደለም። በዘመናችን እንኳ አሁን በቅርቡ (ነአ) በመለስ ዜናዊና በታምራት ላይኔ ዐዋጅ አሰቦታውያን መታረዳቸው ይታወሳል። እናም ሰማዕትነት ለአሰቦት ገዳማውያን ብርቃቸው አይደለም። ታጥበው፣ ጽድት ብለው እንደ ሙሽራ የሚጠብቁት ነገር ነው።

______________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: