Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • October 2019
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    28293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

“ከነፍጠኛና ከዶርዜ” ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ማድረግ የሚከለክል አዋጅ በባሌ ሮቤ ታውጇል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 27, 2019

ዘገባው የቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ ነው። (መምሕር ዘመድኩን እንዳቀበለን)

ከባሌ አቦቲ ገዳ፣ ቄሮ፣ አቦቲ አመንታ፣ ማንጉዶማለትም ከአባ ገዳዎች፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከቄሮ እና ከሽማግሌዎች የተላለፈ ነው የተባለ አዋጅ በባሌ ሮቤ መታወጁን የደረሰን የቪዲዮ ማስረጃ ያመለክታል።

ዐዋጁ የታወጀው በድብቅ ወይም በቤት ውስጥ ሳይሆን በይፋ እና ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበት በአደባባይ ላይ ነው። በዚሁ በተነበበው ባለ አሥር ነጥብ መግለጫ ላይ ሕዝቡ ዶርዜ እና ነፍጠኛካሏቸው ሰዎች ጋር፦

ምንም ዓይነት ግንኙነት እንዳያደርግ፣

ምንም ነገር እንዳይሸጥላቸው ምንም ነገርም እንዳይገዛቸው፣

ቤቱን እንዳያከራያቸው፣

ያከራየም እንዲያባርራቸው፣

ቤት ንብረት እንዳይሸጥላቸው፣

ቤታቸውን ከሚሸጡት ላይም እንዳይገዛቸው በእርግማን ጭምር መታዘዙን ቪዲዮው ይገልጻል። ይህንን

እርግማን ተላልፎ ዶርዜ እና ነፍጠኛከሚሏቸው ሰዎች ጋር ምንም ዓይነት የንግድ ግብይት አድርጎ የተገኘ በሙሉ ፈጣሪ መአት እንዲያወርድበት በሼኮች የተረገመ መሆኑን እንዲሁም ከነፍጠኛና ከጠላት ተለይቶ የማይታይ መሆኑ በንባብ ተሰምቷል።

በቪዲዮው ላይ የሚሰሙት ከአሥሩ ነጥቦች ስድስቱ ብቻ ሲሆኑ ዋና ዋና ሐሳባቸውም እንደሚከተለው ቀርቧል።

1. ንግድን በተመለከተ:- ከነፍጠኛ ወይም ከዶርዜ ጋር ሲገበያይ የተገኘ ሰው የተረገመ ነው። በሃይማኖት አባቶች ወይም በሼኮች የተወገዘ ነው።

2 ለነፍጠኛ መኖሪያ ቤት ወይም በረንዳ (የንግድ ቦታ) ያከራያችሁ ዛሬ ከዚህ ሰዓት ጀምራችሁ እንድትነጥቋቸው ለወደፊቱም እንዳታከራዩአቸው።

3. የመኖሪያ ቤትም ሆነ የመኖሪያ ቦታ ለእነርሱ እንዳትሸጡላቸው። ለመሸጥ ከፈለጉም እንዳትገዟቸው። ቤቱ የእናንተ ነው።

4. ወፍጮ ቤት እንዲሁም የመኪና አገልግሎት ከእነርሱ እንዳትጠቀሙ። የእናንተንም እንዲጠቀሙ እንዳታደርጉ።

5. ዛሬ ሰልፍ የወጣነው ጀግናችን የቄሮዎች አባት አቶ ጃዋር መሐመድ ላይ የተቃጣውን የመግደል ሙከራ በመቃወም ነው። ጀዋርን የሚቃወም የባሌ ሕዝብ ጠላት ነው።

6. መንግሥትን በተመለከተ:- ልጆቻችንን የገደሉ ለፍርድ ይቅረቡልን ይላል።

መግለጫው የዘር ፍጅት በተካሄደባቸው በሌሎች ሀገሮች ከነበረው ሁኔታ ጋር የተመሳሰለ ነው። በናዚ ጀርመንና በሩዋንዳ የተፈጸመው ጭፍጨፋ ድንገት የተከሰተ ሳይሆን ምልክቶች የታዩበት መሆኑ ይታወቃል። የጅምላ ጭፍጨፋ መቅድም የሚመስል ድርጊት በይፋ በሚካሄድበት የባሌ ሮቤ ከተማ የክልሉ ፖሊስ እና አስተዳደር ምን እያደረገ እንደሆነ የሚያጠያይቅ ሆኗል።

ፌዴራል መንግሥት እና ዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ ይህንን ድርጊት እንዲመለከተው፣ ሚዲያዎችም እያዩ እንዳላዩ እየሰሙ እንዴሰሙ መሆናቸውን ትተው ከዕለትዕለት እየባሰ የመጣውን አደጋ በመዘገብ ጉዳዩ ትኩረት እንዲያገኝ እንዲያደርጉ ማሳሰብ ያስፈልጋል።

በብሔረሰን ደረጃ ኦሮሞ የሆናችሁ ወንድም እህቶች ይህንን የምናደርገው የኦሮውን ሕዝብ ስም ለማጥፋት ሳይሆን ጥቂት አክራሪዎችና ዘረኞች በኦሮሞ ሕዝብ ስም ወንጀል እየሠሩ መሆናቸውን በማጋለጥ ሰላማዊውን ከሕዝብ ከጥፋት ለመታደግ መሆኑን እንድትረዱልን ለማስታወስ እንፈልጋለን።

የባሌ አባ ገዳዎች ወይም የሀገር ሽማግሌዎች እንዲህ ዓይነት መግለጫ ይሰጣሉ ብለን አናምንም። ታዲያ ሕዝብ ሰብስቦ በእነርሱ ስም ይህንን የጅምላ ፍጅት መቅድም በንባብ የሚያሰማው ክፍል ማን ነው? ክልሉስ የሚወስደው መፍትሔ ምንድነው? በማለት ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ ዘገባውን ይቋጯል።

_________________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: